Darul hijreteyin Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Тарҷума мумкин нест.

በመሀል ከተማ እና በአጎራባች ከከተሞች ህዝብን ያማረረው እገታ በአማራ ክልልም በሙስሊሞች ላይ ተበራክቷል

በአማራ ክልል ሙስሊም ነጋዴዎችን ኢላማ ያደረገ እገታ እየተፈፀመ መሆኑን መረጃዎች እየወጡ ነው::

ይህን እገታ እየፈፀሙ የሚገኙት በሀይማኖት ሽፋን የተጠለሉ ፅንፈኛ ታጣቂዎች መሆናቸው ታውቋል::

ታጣቂዎቹ ያገቱትን ሙስሊም ነጋዴዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ካልከፈሉ እንደሚገድሏቸው በመዛት ብሩን የከፈለውን እየለቀቁ ያልከፈለውን እስካሁን አግኝተው እንደያዙ ናቸው:: ይህን እገታ በመሸሽ በርካታ ወንድሞቻችን ወደ አዲስ አበባ እየሸሹ ይገኛሉ::

ለኢትዮጵያ የሚበጀው የቀድሞ የአንድ እምነት የአንድ ማንነት የበላይነት የሰፈነበት ክርስቲያናዊ መንግስት ብቻ ነው እያሉ ይህን ለመመለስም እየታገሉ እንደሚገኙ በይፋ በሚዲያ እየተናገሩ የሚገኙት እነዚህ ፅንፈኛ ታጣቂዎች ሙስሊሞችን እየለዩ ማገት እና መዝረፍ ስራዬ አድርገው ይዘውታል::

ከ1.5-እስከ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቁ በርካታ ሙስሊሞች አሁንም በታጣቂዎቹ ታግተው ይገኛሉ:: ቤተሰቦቻቸው በከባድ ጭንቀት ውስጥ ናቸው::

በአማራ ህዝብ ላይ በደል እና ግፍ እየተፈፀመ ነው በሚል ለፍትህ እና እኩልነት የሚታገሉ እንዳሉ ሁሉ በዚህ ትግል ሽፋን ሁሌም ውስጣቸው የተቀበረውን የኢስላም እና የሙስሊሞ ጥላቻ በማውጣት የክልሉ ሙስሊሞችን ማጥቃት የቀጠሉ ፅንፈኞች ሞልተዋል::

ይህን እምነት እየለዩ የሚፈፅሙትን ግፍ እና በደል ሲጋለጥ "የአማራን ህዝብ ትግል በሀይማኖት ለመከፋፈል እና ለማዳከም የሚፈልጉ ሀይሎች የሚያሰራጩት መረጃ እንጂ የክልሉ ሙስሊሞች ማንም እያጠቃቸው አይደለም" የሚል ሰፊ ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት እና የዋህ ሙስሊሞችን በመጠቀም የነሱን ድምፅ በማስተጋባት በጥቃት ላይ ያለውን የክልሉን ሙስሊም ድምፅ በማፈን በዝምታ ለእርድ እንደሚጓዝ በሬ እንዳሻቸው እያደረጉት ይገኛሉ::

በደል እና ግፍን እቃወማለው የሚል የትኛውም ብሄር ይሁን እምነት ተከታይ እምነት እና ብሄር እየተለየ መሰል ጥቃት ሲፈፀም ሊያወግዘው እና ሊያስቆም ይገባል::

የአማራ ክልል ሙስሊም በኦሮሚያ ነፍጠኛ በሚል ይገደላል፣ ይጠቃል፣ በአማራ ክልል ደግሞ መጤ፣አክራሪ እስላም እና ኦነግ እየተባለ ይገደላል:ይዘረፋል::

ህብረ ብሄራዊነትን እና ብዝሀነትን የማይቀበለው ይህ ነውረኛ ፅንፈኛ ኃይል በህዝብ ትግል ስር ተወሽቆ የህዝብን የፍትህ እና የእኩልነትን ጥያቄ በመድፈቅ የህዝቡን ሰቆቃ እያበዛው ይገኛል::

በሰላሙ ጊዜም በስጋት የሚኖረውን የክልሉን ሙስሊም ነዋሪ አሁን ላይ የሰላም እጦቱን ተገን በማድረግ ሙስሊሙን ማገት ፣ መዝረፍ እና ቤት እየፈተሹ የግል መሳርያውን መንጠቅ ተያይዘውታል::

ጥሩ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያደርገውን በመለየት እና በማገትም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ካልከፈልክ እንገድልሀለን በማለት እያሰቃዩ ይገኛሉ::

ይህን እውነታ በተለይ በባህርዳር እና ዙሪያው ካሉ ሙስሊሞች እውነታውን ማረጋገጥ ይቻላል:: ሚዲያዎች በተለይም የሙስሊም ሚዲያዎች ይህን እውነታ ታግተው የተለቀቁትን እንዲሁም የጥቃቱ ሰለባዎችን በማነጋገር እውነታውን ለህዝብ ልታቀርቡ ይገባል::

ለፍትህ እንታገላለን የሚል አካል ሃይማኖትን እየለየ ሙስሊሞችን ብቻ ሊያጠቃ አይችልም::

ይህን እየፈፀሙ ያሉ ነውረኞችን ከማንም በፊት ለአማራ ህዝብ እታገላለው የሚል ሁሉ ሊያወግዛቸው እና ሊያስቆማቸው ይገባል::

የእምነት ወንድሞቼ ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ ታግተው ጥቃት እየተፈፀመባቸው በመሆኑ ይህ ይቆም ዘንድ ድምፄን አሰማላቸዋለው::

ዛሬ በጉልበት የዘረፍከውን ነገ በእንብርክክ እየሄድክ የዘራኸውን ማጨድህ አይቀርም::

ፍትህ በአማራ ክልል በእምነታቸው ተለይተው በፅንፈኞች ለታገቱ ሙስሊሞች!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Тарҷума мумкин нест.

#ጥበባዊ ንግግር

ከጠቢባን አንዱ እንዲህ አለ፡-

“ሁሉንም ጣፋጭ ነገሮች ቀምሻለሁ። ነገር ግን ከጤና የበለጠ ጣፋጭ ነገር አላገኘሁም።

መራራ ነገራትን ሁሉ ቀመሻለሁ..ነገር ግን ከሰዎች ከመፈለግ (ከመከጀል) በላይ ምንም መራራ ነገር አላጋጠመኝም!"

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Тарҷума мумкин нест.

"ሁኔታህን (ተጨባጭህን) ብታሰላስል አላህ በርካታ ነገሮችን ሳትለምነውና ሳትጠይቀው እንደሰጠህ ትመለከታለህ ።

ስለዚህ አንተ የማታውቀውን መልካም ነገር ሊሰጥህና ሊተካህ ካልሆነ በስተቀር የምትፈልገውንና የምትመኘውን ነገር አላህ እንዳልከለከለህ እርግጠኛ ሁን። ”

ኢብኑል ቀይም

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Тарҷума мумкин нест.

"ቆንጆ ለመሆን መልከኛ (ውብ) ወይም ለመወደድ ማመስገን (አመስጋኝ ) ወይም ደስተኛ ለመሆን ሀብታም መሆን አያስፈልግህም።

የእርካታን (የሪዷን) ምንነት ማወቅ እና እርሱን በህይወትህ ውስጥ መተግበር በቂ ነው!

እራስህን ገምግም አሻሽል።”

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Тарҷума мумкин нест.

#ጥበባዊ ንግግር

ከጠቢባን አንዱ እንዲህ አለ፡-

“ሁሉንም ጣፋጭ ነገሮች ቀምሻለሁ። ነገር ግን ከጤና የበለጠ ጣፋጭ ነገር አላገኘሁም።

መራራ ነገራትን ሁሉ ቀመሻለሁ..ነገር ግን ከሰዎች ከመፈለግ (ከመከጀል) በላይ ምንም መራራ ነገር አላጋጠመኝም!"

Send as a message
Share on my page
Share in the group