Translation is not possible.

#አላህን_ለማስታወስ_አዘውትሮ #መሰባሰብ_ተወዳጅ_ተግባር #ስለ_መሆኑና #ካለ_ምክንያት #አላህን_ከማስታወስ_ስብስቦች #መልለየት_ስለመከልከሉ

#ክፍል_3

#ሐዲሥ 247 / 1449

አቢ ዋቂድ ሐሪሥ ኢብኑ ዐውፍ እንዳስተላለፉት፥ የአላህ መልዕክተኛ መስጊድ ውስጥ ከሰዎች ጋር ተቀምጠው እያለ ሦስት ሰዎች መጡ። ሁለቱ ወደ አላህ መልዕክተኛ በመምጣት ከርሳቸው ዘንድ ቆሙ። አንደኛው ሔደ። አንደኛው ከስብስቡ መሐል ክፍት ቦታ አየና ተቀመጠ። ሌላኛው ደግሞ ከስብስቡ በኋላ ተቀመጠ። ሦስተኛው ግን ተመልሶ ሔደ። የአላህ መልዕክተኛ ጉዳያቸውን ሲያጠናቅቁ እንዲህ አሉ፦ "ስለነዚህ ሦስት ሰዎች ሁኔታ ልንገራችሁን? አንደኛው ወደ አላህ ተጠጋ፤ አላህም አስጠጋው፤ ሁለተኛው ትሁት ሆነ፤ አላህም ለርሱ ትሁት ሆነለት፤ ሦስተኛው ሸሸ፤ አላህም ከርሱ ሸሸ።" (ቡኻሪና ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ የዲን እውቀት ከሚሰጥባቸው ስብስቦች መቀመጥ ይወደዳል።

2/ ክፍት ቦታ ካገኙ እዚያ መቀመጥ፥ ካልሆነ ሰዎችን አለማጣበብና አለመጨናነቅ።

3/ የትሕትና (ሐያእ) ልቅናና ጠቀሜታ።

4/ ከእውቀት ቦታዎች መሸሽ የተወገዘ ተግባር ነው። ያለምክንያት የእውቀት ማዕዶችን የሸሸ ለአላህ ቁጣ ራሱን አጋልጧል።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group