UMMA TOKEN INVESTOR

mame kassaw shared a
Translation is not possible.

#ሰበር

አልቃሳም ብርጌድ የጦር ኃይል አባላቱ የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስካሁን አለመራዘሙን አስመልክቶ የስምምነቱ መጨረሻ ሰአት በመቃረቡ ሁሉም አባላቱ ለውጊያ በከፍተኛ ሁኔታ ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ ጠየቀ፡፡ ጦሩ አክሎም ስምምነቱ መራዘሙን የሚያረጋግጥ ኦፊሴላዊ መግለጫ እስካልተሰጠ ድረስ በዚሁ ላይ እንዲቆዩ አሳስቧል፡፡

كتائب القسام تطلب من قواتها العاملة البقاء على جاهزية قتالية عالية في الساعات الأخيرة من التهدئة تحسباً لتجدد القتال في حال عدم تجديدها والبقاء على ذلك ما لم يصدر بيان رسمي يؤكد تمديد التهدئة

#palestine #فلسطين #freepalestine #غزة #hamas #qassam #yemen #lebannon #iran

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
mame kassaw shared a
Translation is not possible.

ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተጋጩ ጊዜ ሁለት ኢስላማዊ ስረወ መንግስት ተመሰረተ የሮሙ ንጉስ ይህን ሰምቶ እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ ፦

" ከሮም ንጉሰ ነገስት ለሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!! 

ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭትሰምተናል ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት 

ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ "

ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም :-

" ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ 

እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ "

#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው‼️

============================

ኻሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈለት፦

"ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ 

እመጣለሁ።" 

ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት። የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት። 

"ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ 

ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።"

# ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ ‼️

============================

በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር። 

#ያኔ_ጀግና_ሳለን‼️

============================

በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዱ ቤት ደጅ ላይ ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነውና በሩን ሊከፍት 

የሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች። 

በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ 

እዚያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር። 

#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር ‼️

============================

ጊዜው ሰላሀዱን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው ሰላሀዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ። 

ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ጊዜ ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች 

ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ። 

#ማንተኛበት_ዘመን‼️ 

___ 

ቀደምት ዑለማዎች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር። 

1.ሰውዬው በሱ እና በአሏህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል። 

2.ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አሏህ ይፋዊ ተግባሩን ያሳምርለታል። 

3፦ሰውዬው የአኺራው ጉዳይ ካስጨነቀው አሏህ የዱንያውንም የአኺራውንም ጉዳይ ያግራራለታል። 

============================

#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው‼️ 

ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።  አዎ ትልቁ ኪሳራ ይህ ነው!!

በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ይህም ትልቅ ኪሳራ ነው። 

ይህን ፅሁፍ በማሰራጨት ጓደኛህን/ሽን እንድታነቃው ይከጀላል!

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

Send as a message
Share on my page
Share in the group
mame kassaw shared a
Translation is not possible.

ሰበካ ሳይሆን የሰዎችን መብትና ነፃነት መጋፋት ነው‼

==============================

✍ ባለፈ ጦር ኃይሎች አካባቢ የተወሰኑ ወጣቶች የማንንም መብት ሳይጋፉ የመንገድ ላይ ዳዕዋ ጀምረው ነበር። ግን ወዲያው ለእስር ተዳረጉና በዛውም ማሸማቀቂያና ማስፈራሪያ ተደረገባቸው።

በየታክሲው ሰልፍና በመስጂዶች ዙሪያና በሙስሊሞች ሰፈር ሳይቀር እየዞሩ ከባድ የድምፅ ማጉያና ሞንታሪቦ ተጠቅመው ሰዎችን ማደንቆራቸው አንሷቸው፤

ይሄው እንደ ሐድያ ሆሳና ባሉ አካባቢዎች በህብረት የተደራጁ ሰባኪ ተብዬ ወንበደዎች እኚህን በእድሚያቸው የገፉ ሙስሊም አባታችንን ከበው በግድ እስልምናን ለቀህ የእኛን እምነት ካልተከተልክ እያሏቸው ነው።

ነውር ነው! እጅግ ሲበዛ ዓይን ያወጣ ስግጥና!

እነዚያ ሰላማዊ ሙስሊምን ከመንገድ ላይ አፍሰው የሚያስሩ የጸጥታ አካል ተብዬዎች እንዲህ አይነቶቹን ወንበዴዎች ተጠያቂ ያደርጉ ይሆን?

በተለይም ደቡብ አካባቢ እንደዛ የሚያደርጉ አይመስለኝም። እንዳውም አብረው ሲያጅቡና አዳራሽ ገብተው ሲደንሱ ነው የምናውቀው። ይሄ ነገር ገደብ ካልተበጀለትና ከወዲሁ በቃ ካልተባለ ቀስ በቀስ ከዚህ በከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል።

የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ተብዬው የአንድ እምነት ተቋም፤ ሙስሊሞች ዳዕዋ ሲጀምሩ እንደሚንጨረጨረው ሁሉ እንዲህ አይነት ጋጠ ወጦችን ያወግዝ ይሆን?

የምናየው ይሆናል! ይህንን እምነትን በአደባባይ አስገድዶ የማስለቀቅ ተግባር ሁሉም ሰው ሊኮንነው ይገባል።

የሚመለከተው አካል በነዚህና መሰል አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ ሊወስድ ይገባል። የዚያ አካባቢ እስልምና ጉዳዮችም ተነጋግራችሁ ጉዳዩን ወደ ፍርድ አቅርቡትና ፍትሕ ካለ መቀጣጫና ለሌሎችም ማረሚያ እንዲሆኑ ይደረግ።

||

t.me/MuradTadesse

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
mame kassaw Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group