UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 1

───────────

ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - ኢብኑ ተይሚያህ አንድ ጊዜ እንዲህ ሲሉ መከሩኝ —

«ቀልብህን የፈሰሰበትን ሁሉ እንደሚመጠውና ሲጨምቁትም ያንኑ እንደሚተፋው እስፖንጅ አታድርገው። ይልቁንስ እንደ መስታወት አድርገው። ብዥታዎች በገፅታው ላይ ያልፋሉንጂ ወደ ውስጡ አይገቡም። አጥርቶ ይመለከታቸዋል፣ በጠጣርነቱ ደግሞ ይመልሳቸዋል። አንተም ባንተ ላይ የመጣውን ብዥታ ሁሉ ለልብህ ካጠጣኸው የብዥታዎች መኖሪያ ይሆናል።»

📚 ۞ مفتاح دار السعادة【1/443】۞

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Zeynu Nuri shared a
Translation is not possible.

ትኩረት የነፈግናቸው የሃሜት ሰበቦች

~

ሃሜት ፀያፍ እንደሆነ የምናምንበት ግን በተግባር መራቁ የሚያቅተን ክፉ ባህሪ ነው። ለሃሜት የሚዳርጉን ሰበቦች ብዙ ናቸው። ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው:-

1- የተቅዋ ማነስ፦

አንድ ሰው በልቡ ውስጥ አላህን መፍራት ሲቀንስ የሚናገረውን መመዘን ይቀራል። በንግግሩ ሳቢያ የሚመጣበትን ጣጣ ከማሰብ ይልቅ የሚሰማውን ሁሉ መናገር ደስታ ይሰጠዋል። ስለዚህ በዚህ በሽታ የተጠቃ ሰው (ያልተጠቃ አለ ግን?) ህክምና የሚፈልግ ከሆነ ልቡን ከማከም ይጀምር። ተቅዋውን ይፈትሽ።

2- ምቀኝነት፦

ሌላኛው የሃሜት ሰበብ በሌሎች ላይ የሚኖረን የምቀኝነት ስሜት ነው። "እኔ ከዚህ በሽታ ንፁህ ነኝ" እያልክ ራስህን አትሸንግል። ምቀኞች ምቀኝነታቸውን አያምኑም። የራስ እንትን አይገማም ይባላል። ስለዚህ ሃሜተኝነት የሌላ በሽታ ማለትም በምቀኝነት የመጠቃት ምልክት ሊሆን ስለሚችል ደጋግመህ ልብህን አዳምጥ። ከዚያም በተቅዋ ታከመው።

3- ውሎ:-

ሌላኛው የሃሜት ሰበብ ጓደኛ ነው። ሰው ብቻውን በሃሜት አይለፈልፍም። ሃሜት ላይ አድማጭ፣ አጃቢ፣ አጋዥ፣ ... ትልቅ ሚና አላቸው። ሃሜት ላይ የምትወድቀው ከማን ጋር ስትሆን እንደሆነ አንዴ በአይነ ህሊናህ ተመልከት። ከማን ጋር ሆነው ሰው የምታማው? ከዚያም ችግሩን ለመፍታት ከልብህ አስብበት። ተነጋግሮ ችግሩን ለመፍታት መፍትሄው ከራቀ ለሰበቡ ያለህን ቅርበት ቀንስ። ያን ካላደረግክ ከነ ህመምህ ልትኖር ወስነሃል።

4- ራስን ማጉላት:-

ሌላኛው የሃሜት መንስኤ ሌሎችን በማሳነስ ወይም በማጠልሸት ራስን የማጉላት ድብቅ ፍላጎት ነው። ይሄ ከሃሜቱ ልክፍት በፊት ልንታከመው የሚገባ ሌላ በሽታ ነው። አዎ ብዙ የሃሜት ገፊ ምክንያቶች ውስጥ ከጀርባ ያደፈጡ ራስን በሆነ ነገር ልዩ የማድረግ ወይም የመስቀል አባዜ ስለሚኖር ነፍሲያችንን ምን ፈልጋ ከሃሜት ሰፈር እየተልከሰከሰች እንደሆነ ቀስ ብለን እንከታተላት። ምናልባት እጅ ከፍንጅ ልንይዛት እንችላለን።

5- ቀልድና ቧልት:-

ብዙ ጨዋታዎች የሞቁ የደመቁ የሃሜት ድግሶች ናቸው። በቀልድ እያዋዛን የምንዘለዝለው የሃሜት ቁርጥ ለጊዜው ጣእሙ ልዩ ሊሆን ይችላል። ሰው ሳያውቅ የሰውን ስጋ አጣጥሞ ቢበላ ላይደንቅ ይችላል። የሚገርመው እያወቅን ደጋግመን መቀጠላችን ነው። ሃሜት የሰው ስጋ መብላት ነው። ያውም የሞተን ሰው አካል! ምን ስሜት ይሰጣል?

{وَلَا یَغۡتَب بَّعۡضُكُم بَعۡضًاۚ أَیُحِبُّ أَحَدُكُمۡ أَن یَأۡكُلَ لَحۡمَ أَخِیهِ مَیۡتࣰا فَكَرِهۡتُمُوهُۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ}

"ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ። አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ሆኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት)። አላህንም ፍሩ።" [አልሁጁራት፡ 12]

Ibnu Munewor

=

የቴሌግራም ቻናል፡-

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Zeynu Nuri shared a
Translation is not possible.

✅ የጁምዓ ቀን ሱናዎች

❶ኛ ገላን መታጠብ።🚿

➋ኛ ሽቶን መቀባባት እና መዋብ።💨

❸ኛ ሲዋክን መጠቀም።🌴

❹ኛ የክት ልብስ መልበስ።⚪

❺ኛ በጊዜ መስጂድ መጓዝ።🕒

❻ኛ በእግር እየተጓዙ ወደ መስጅድ መሄድ።🚶

❼ኛ መስጂድ ከደረሱ በኋላ የሰዎችን ትከሻ በመረማመድ ሰዉን አለማስቸገር።🧎‍♂️

❽ኛ ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ቢሆንም ተህየቱ መስጂድ መስገድ።👂👂

❾ኛ ኹጥባ ወደ የሚያደርገው ኢማም መዞር እሱን እያዩ ኹጥባ ማድመጥ።👀

❿ኛ ኹጥባ በሚደረግበት ሰዓት ፀጥታን መላበስ።🤐

⓫ኛ ሰደቃን ማብዛት።💵💵

⓬ኛ ከሀሙስ ማታ ጀምሮ እሰከ ጁምዓ ዐስር ድረስ ሱረቱ ከሕፍ መቅራት።

⓭ኛ ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሰዓትን መጠባበቅ።

⓮ኛ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን በብዛት ማውረድ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐

“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”

📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል: 1531

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከዘይድ ቢን አርቀም (رضيﷲ عنه)ተይዞ ረሱል (ﷺ) ይህን ዱዓ ያደርጉ ነበር፡‐

”اللَّهمَّ آتِ نفسي تقواها وزكِّها أنت خيرُ من زكّاها أنت وليُّها ومولاها“

“አላህ ሆይ! ለነፍሴ ተቅዋን ለግሳት:: አጽዳትም። ከአንተ የትሻለ የሚያፀዳት የለምና፡፡ አንተ አስዋቢዋም አምላኳም ነህ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2722

Send as a message
Share on my page
Share in the group