UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

አጭር የኪታብ ዳሰሳ (ፈትሑል ዐላም እና ሚንሐቱል ዐላም)

~

ቡሉጉል መራም በፊቅህ አሕካም ላይ እጅግ ወሳኝ ኪታብ ነው። መጨረሻ ላይ ደግሞ ኣዳብና አዝካር ላይ የሚያጠነጥኑ ጠቃሚ የሐዲሥ ስብሰቦችን ይዟል። ይህንን ኪታብ ብጥር ልቅም አድርጎ ለያዘው ሰው በጣም ትልቅ መሰረት ይሆነዋልና የሚችል ሰው ተገቢ ትኩረት ቢሰጠው መልካም ነው።

ኪታቡን ልጅ እያለሁ እንደነገሩ ካንቧተርኩት ውጭ ከዚያ በኋላ በአጥጋቢ ሁኔታ አይቼው አላውቅም። ዛሬ ነገ እያልኩ ከቆየሁ በኋላ ከወራት በፊት ጀመርኩት። በመሀል በተለያዩ ምክንያቶች እየተቋረጠ ሲመቸኝ ስቀጥል ትናንት በአምስት ወሩ ተጠናቀቀ። ሁለት ሰፋ ያሉ አጋዥ ስራዎችን ተጠቅሜያለሁ። የኢብኑ ሒዛም "ፈትሑል ዐላም" እና የዐብደላህ አልፈውዛን "ሚንሐቱል ዐላም"። (የዐብዱል ሐሚድ አልሐጁሪን ባለ 10 ጥራዝ "ሂበቱሰላም" ሸርሕ ገረፍረፍ አድርጌ አቀራረቡ ስላልሳበኝ አልቀጠልኩበትም።)

1ኛ፦ "ፈትሑል ዐላም"

በግርድፉ ሸርሕ እንለዋለን እንጂ በጣም አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ለሚቀርቡት ሐዲሦች የቃላት መፍቻ፣ የሃሳብ ማፍታቻ የለውም። ባጭሩ ሸርሕ አይደለም። ይህንን ጉዳይ ራሳቸው አዘጋጁ ኢብኑ ሒዛም መግቢያው ላይ ገልፀዋል። የኪታቡ ትኩረት ከሐዲሡ የሚወሰዱ ቁም ነገሮችንና ተያያዥ ወይም ተቀራራቢ ነጥቦችን በማስረጃ የተጀበ ሑክም ላይ ያነጣጠረ ዳሰሳ ማድረግ ነው።

ፈትሑል ዐላምን አምስት ጥራዝ እያለ እንዲሁ በሩጫ ሙሉውን አይቼው ነበር። አሁን አስር ሙጀለድ ሆኗል። በርከት ያሉ ክፍሎቹን ከዚህ በፊት ደጋግሜ አይቻቸዋለሁ። ግን ብዙው ነገር ስለተዘነጋ አብዛኛው ክፍል አዲስ ሆኖ ነው ያገኘሁት።

2ኛ፦ "ሚንሐቱል ዐላም"

(ከ10 አመት በፊት ከገዛሁት ከሳምንት በኋላ በሆነ ምክንያት መልሼው ዛሬ pdf ፋይል ልጠቀም ተገድጃለሁ።)

ከያንዳንዱ ሐዲሥ በማስቀጠል ዘጋቢ ሶሐቢዮችን ባጭር ያስተዋውቁና እንግዳ ቃላትን ይፈታሉ። ማብራሪያ የሚሻ ነጥብ ካለ እሱን ያፍታታሉ። ከሰፈረበት ርእስ ጋር ባይያያዙ እንኳ ከሐዲሡ የሚወሰዱ ቁም ነገሮች አጠር አድርገው ይነካካሉ። አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት የቡሉግ አዘጋጅ ኢብኑ ሐጀር ሐዲሡን ወይም ዘገባውን ለምን በተጠቀሰው ርእስ ስር እንዳሰፈሩት ያስረዳሉ።

የጋራ ነገር፦

* ሁለቱም ኪታቦች የሐዲሦቹን ደረጃዎች ፈትሸው መረምረው ያሰፍራሉ።

* ሁለቱም ኪታቦች አስር ፣ አስር ጥራዞች ናቸው፣ በድምሩ ሃያ ሙጀለድ ኪታብ። "ሚንሓቱል ዐላም" ማውጫ ብቻ የያዘ ተጨማሪ 11ኛ ሙጀለድ አለው። የእያንዳንዱ ጥራዝ መጠን ከ400 ምናምን እስከ 7ዐዐ ምርምን ገፆች ይደርሳል።

ቡሉግን ጥሩ በሆነ ደረጃ ለመገንዘብ የሚሻ እነዚህን ሁለት አጋዥ ስራዎች ነካ ነካ ሳይሆን በትኩረት ቢመለከት በእጅጉ ይጠቀማል ብዬ አስባለሁ። ወይም ሌላ የተመቸውን። የቻለና ጊዜ ያለው ሰው ደግሞ በተጨማሪ አንድ የድምፅ ሸርሕ ጎን በጎን ቢከታተል የበለጠ ቆንጆ ነው። እኔ የሸይኽ ዐብዱልከሪም አልኹዶይርን የተቀዳ የድምፅ ትምህርት መከታተል ጀምሬ ነበር። ካለኝ ጊዜ ጋር ስላልሄደልኝ አልገፋሁበትም።

ለሚችሉ ሰዎች ቡሉግን ከመማራቸው ወይም ከማስተማራቸው በፊት ሁለት ርእሶችን ቢያስቀድሙ ጥሩ ነው።

1ኛ፦ መሰረታዊ የሙስጠለሐል ሐዲሥ ኪታብ መከታተል። ለምሳሌ የኹዶይር የኑከት ሸርሕ ወይም የዐብደላህ አልቡኻሪይ የበይቁኒያህ ሸርሕ  በጣም ቆንጆ ናቸው።

2ኛ፦ መሰረታዊ የቀዋዒደል ፊቅህ ኪታብ መከታተል። ለምሳሌ የዑሶይሚን የወረቃት ማብራሪያ ሊሆን ይችላል። (አጭር ናት።)

ማሳሰቢያ፦

* እነዚህን ሁለት ሰፋፊ አጋዥ ስራዎች ስመለከት ያስተዋልኩት መትኑ እንደ ኑስኻው ልዩነት ጥቂት የጎደሉት ሐዲሦች አሉ። በዚህ የተነሳ አንዱ "ሸርሕ" ላይ የሚገኝ ሌላኛው ላይ ግን የሌለ ሐዲሥ በጣም አንዳንዴ ያጋጥማል።

* እነዚህን ሁለት ሸርሖች ስመለከት የገጠመኝ ሰፊው ዳሰሳ የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሐጅ አፈፃፀም የሚዘክረው ታዋቂው የጃቢር ሐዲሥ ላይ የተደረገው የኢብኑ ሒዛም ዳሰሳ ሲሆን ፈትሑል ዐላም ላይ 185 ገፅ አካባቢ የሚሆን ዘለግ ያለ ዳሰሳ በዚህ ሐዲሥ ላይ ብቻ አድርገውበታል።

* የቻላችሁ ሁለቱንም ኪታቦች ብትይዙ። ከሁለቱ አንዱን መግዛት ለምትፈልጉ፣ በተለይም ደግሞ ለማስተማሪያነት ለምትፈልጉ የዐብደላህ አልፈውዛንን "ሚንሐቱል ዐላም" ብታስቀድሙ የተሻለ እንደሆነ ነው የተረዳሁት።

* ሶፍት ኮፒ ለሚፈልግ ሁለቱም ኪታቦች በ pdf ይገኛሉ። ግን እንዲሁ አልፎ አልፎ ለማየት ካልሆነ በስተቀር ይህንን ሁሉ መጠን ሶፍት ኮፒ ላይ መቆየት ለአይን ይፈትናል።

Ibnu Munewor

=

የቴሌግራም ቻናል፡-

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ትኩረት የነፈግናቸው የሃሜት ሰበቦች

~

ሃሜት ፀያፍ እንደሆነ የምናምንበት ግን በተግባር መራቁ የሚያቅተን ክፉ ባህሪ ነው። ለሃሜት የሚዳርጉን ሰበቦች ብዙ ናቸው። ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው:-

1- የተቅዋ ማነስ፦

አንድ ሰው በልቡ ውስጥ አላህን መፍራት ሲቀንስ የሚናገረውን መመዘን ይቀራል። በንግግሩ ሳቢያ የሚመጣበትን ጣጣ ከማሰብ ይልቅ የሚሰማውን ሁሉ መናገር ደስታ ይሰጠዋል። ስለዚህ በዚህ በሽታ የተጠቃ ሰው (ያልተጠቃ አለ ግን?) ህክምና የሚፈልግ ከሆነ ልቡን ከማከም ይጀምር። ተቅዋውን ይፈትሽ።

2- ምቀኝነት፦

ሌላኛው የሃሜት ሰበብ በሌሎች ላይ የሚኖረን የምቀኝነት ስሜት ነው። "እኔ ከዚህ በሽታ ንፁህ ነኝ" እያልክ ራስህን አትሸንግል። ምቀኞች ምቀኝነታቸውን አያምኑም። የራስ እንትን አይገማም ይባላል። ስለዚህ ሃሜተኝነት የሌላ በሽታ ማለትም በምቀኝነት የመጠቃት ምልክት ሊሆን ስለሚችል ደጋግመህ ልብህን አዳምጥ። ከዚያም በተቅዋ ታከመው።

3- ውሎ:-

ሌላኛው የሃሜት ሰበብ ጓደኛ ነው። ሰው ብቻውን በሃሜት አይለፈልፍም። ሃሜት ላይ አድማጭ፣ አጃቢ፣ አጋዥ፣ ... ትልቅ ሚና አላቸው። ሃሜት ላይ የምትወድቀው ከማን ጋር ስትሆን እንደሆነ አንዴ በአይነ ህሊናህ ተመልከት። ከማን ጋር ሆነው ሰው የምታማው? ከዚያም ችግሩን ለመፍታት ከልብህ አስብበት። ተነጋግሮ ችግሩን ለመፍታት መፍትሄው ከራቀ ለሰበቡ ያለህን ቅርበት ቀንስ። ያን ካላደረግክ ከነ ህመምህ ልትኖር ወስነሃል።

4- ራስን ማጉላት:-

ሌላኛው የሃሜት መንስኤ ሌሎችን በማሳነስ ወይም በማጠልሸት ራስን የማጉላት ድብቅ ፍላጎት ነው። ይሄ ከሃሜቱ ልክፍት በፊት ልንታከመው የሚገባ ሌላ በሽታ ነው። አዎ ብዙ የሃሜት ገፊ ምክንያቶች ውስጥ ከጀርባ ያደፈጡ ራስን በሆነ ነገር ልዩ የማድረግ ወይም የመስቀል አባዜ ስለሚኖር ነፍሲያችንን ምን ፈልጋ ከሃሜት ሰፈር እየተልከሰከሰች እንደሆነ ቀስ ብለን እንከታተላት። ምናልባት እጅ ከፍንጅ ልንይዛት እንችላለን።

5- ቀልድና ቧልት:-

ብዙ ጨዋታዎች የሞቁ የደመቁ የሃሜት ድግሶች ናቸው። በቀልድ እያዋዛን የምንዘለዝለው የሃሜት ቁርጥ ለጊዜው ጣእሙ ልዩ ሊሆን ይችላል። ሰው ሳያውቅ የሰውን ስጋ አጣጥሞ ቢበላ ላይደንቅ ይችላል። የሚገርመው እያወቅን ደጋግመን መቀጠላችን ነው። ሃሜት የሰው ስጋ መብላት ነው። ያውም የሞተን ሰው አካል! ምን ስሜት ይሰጣል?

{وَلَا یَغۡتَب بَّعۡضُكُم بَعۡضًاۚ أَیُحِبُّ أَحَدُكُمۡ أَن یَأۡكُلَ لَحۡمَ أَخِیهِ مَیۡتࣰا فَكَرِهۡتُمُوهُۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ}

"ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ። አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ሆኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት)። አላህንም ፍሩ።" [አልሁጁራት፡ 12]

Ibnu Munewor

=

የቴሌግራም ቻናል፡-

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group