UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

እንጠንቀቅ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እንጠንቀቅ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ብትኖር ይሻልሃል

~

ህይወት ውድ ነች። የጌታህን ውድ አደራ ጠብቅ። የረባ ትርጉም በሌለው ጉዳይ ላይ አጉል መስዋእትነት አትክፈል። በደመ ነፍስ እየተጓዝክ የማንንም ሰላም አታውክ። በህዝብ ስም እየማልክ የህዝብ ሰላም አትንሳ። በህዝብ ስም እያነባህ የህዝብ ሐቅ አትንካ።

ግዴለህም በጊዜ ተመከር። እምቢ ካልክ ግን መከራ ይመክርሃል። እወቅ! የግፍ ፅዋ ያስከፍላል። የሰው እንባ ከባድ ነው። ከኣኺራ በፊት ዱንያ ላይ አሳፋሪና አዋራጅ ፍፃሜ ላይ ይጥላል። ከሰመመንህ በጊዜ ንቃ። በራስህ ጩኸት አትደንቁር። እምቢ ካልክ አምሳ አጣሁ ብለህ ለያዥ ለገናዥ ስታስቸግር መቶው ይርቅሃል። እምቢ ካልክ የለመነህን ተቆርቋሪ ምክር ለምነህ ታጣዋለህ። የተሳፈርክበት ባቡር አቅጣጫው ሌላ ነው። ካለምክበት ላትደርስ ጉዞህን አትቀጥል። ሳትርቅ ውረድ። ግዴለህም ውረድ። ለህዝብ ስትል ውረድ። ለቤተሰብህ ስትል ውረድ። ለራስህ ስትል ውረድ። ጠብ የምታደርገው ላይኖር ህይወት አትክፈል። መኖርህ ለሚቆረቆሩልህ ሁሉ ትርፍ ነው። ሞትህ የቤተሰብ እዳ ነው።

ሃሳቤ #በተሳሳተና በማያዋጣ ትግል አጉል መስዋእትነት እየከፈልክ ላለኸው ሙስሊም ወንድሜ ነው! በቅንነት ላትረዳኝ በመልካም ላታስበኝ ምን አደከመኝ ማለት እችል ነበር። ግና ህይወትህ ያገባኛል ብዬ ነው መፃፌ። እንጂ ምን አገባኝ ማለት ማንን ያቅታል? አላህ ማስተዋሉን ያድልህ።

@Ibnu Munewor

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ኡማህ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥120 ኢብራሂም ለአሏህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِّلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

አልምጥ እና አልግጥ የሆኑ ሚሽነሪዎች፦ "ኡማህ" أُمَّة የሚለው ቃል ቁርኣን ላይ ያለ አግባብ ሁለት ቦታ ገብቷል፥ አንደኛው እንስሳትን ሕዝብ ሲል ሁለተኛው ደግሞ ኢብራሂምን ሕዝብ ይላል" እያሉ ያለ ዕውቀት ሲቦተረፉ ግርም ይላል። ሐቅን አጥልቆ እና ታጥቆ ለተነሳ ሙሥሊም ይህ አንኮላ እና እንኩቶ ትችት ከመጤፉ ነው፥ ለዚህ ቅሪላ እና አለሌ ትችት መልስ እንስጥ!

"ኡማህ" أُمَّة የሚለው ቃል "አመመ" أَمَّمَ ማለትም "ሐዘበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሕዝብ" ማለት ነው፥ የኡማህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኡመም" أُمَم ሲሆን "ሕዝቦች" ማለት ነው፦

6፥38 ከተንቀሳቃሽም በምድር የሚኼድ በሁለት ክንፎቹ የሚበርም በራሪ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ وَمَا مِن دَابَّةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا طَائِرٍ يَطِيرُ بِجَنَاحَيْهِ إِلَّا أُمَمٌ أَمْثَالُكُم

"ዳባህ" دَابَّة ማለት "እንስሳ" ማለት ነው፥ እንስሳት የየራሳቸው ስብስብ ስላላቸው "ሕዝቦች" ናቸው። ይህ ትችት መልስ በባይብል መሳ ለመሳ ስናየው "ሕዝብ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሐዘበ" ማለትም "ሰበሰበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስብስብ" ማለት ነው፥ እንስሳት እኮ "ስብስብ" አላቸው፦

ምሳሌ 30፥25 ገብረ ጕንዳን ኃይል የሌላቸው "ሕዝቦች" ናቸው። הַ֭נְּמָלִים עַ֣ם לֹא־עָ֑ז וַיָּכִ֖ינוּ בַקַּ֣יִץ לַחְמָֽם׃

ምሳሌ 30፥25 ሽኮኮዎች ያልበረቱ "ሕዝቦች ናቸው። פַנִּים עַ֣ם לֹא־עָצ֑וּם וַיָּשִׂ֖ימוּ בַסֶּ֣לַע בֵּיתָֽם׃

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "አም" עַ֣ם ማለት "ሕዝብ" ማለት ሲሆን ገብረ ጕንዳን እና ሽኮኮዎች "ሕዝብ" መባላቸው ስታነቡ ምን ይውጣችሁ ይሆን? ሁለተኛውን ትችት እስቲ እንመልከት፦

16፥120 ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ "ሕዝብ" ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡ إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِّلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ ኢብራሂም "ሕዝብ" የተባለው በመውለድ እና በመክበድ አባት፣ አያት፣ ቅድመ አያት፣ ቅም አያት፣ ቅማንት፣ ሽማት፣ ምንዥላት፣ እንጅላት፣ ፍናጅ እና ቅናጅ በመሆን መባዛቱን የሚያሳይ ነው። ይህ ትችት መልስ በባይብል መሳ ለመሳ ስናየው አብርሃም "ሕዝብ" እንደሚሆን ይናገራል፦

ዘፍጥረት 17፥6 እጅግም አበዛሃለሁ፥ "ሕዝብ" አደርግሃለሁ፥ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ። וְהִפְרֵתִ֤י אֹֽתְךָ֙ בִּמְאֹ֣ד מְאֹ֔ד וּנְתַתִּ֖יךָ לְגֹויִ֑ם וּמְלָכִ֖ים מִמְּךָ֥ יֵצֵֽאוּ׃

አብርሃም ሲወልድ እና ሲዋለድ በመብዛት ሕዝብ መሆኑን ካየን ዘንዳ ሕዝብ ከሆነ በኃላ አምላካችን አሏህ ቁርኣን ላይ "ኢብራሂም "ሕዝብ" ነበር" ቢለን እንዴት ያለ ዕውቀት ለትችት ትሮጣላችሁ? አሏህ የህዲኩም ወዩሠቢትና! አሚን። 

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🏝ከሰው እጅ ከጠበቅ ነጃ ይበለን

ከአብደላህ ቢን መስዑድ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለው ዱዓ ያደርጉ ነበር፦

﴿اللَّهُمَّ إنِّي أسْأَلُكَ الهُدى والتُّقى، والعَفافَ والغِنى. وفي روايةٍ: والعِفَّةَ﴾

“አላህ ሆይ! መቀናትን፣ ጥንቅቁነትን፣ ጥብቅነትንና ራስን መቻልን እጠይቅሃለው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 6761

Send as a message
Share on my page
Share in the group