Translation is not possible.

የንጉሥ አስሃማ ቢን አብጀር ነጃሺ መስጂድና ኢስላማዊ የምርምር ማዕከል ከ 10ሺ በላይ ምዕመናን እንደሚያስተናግድ ተገለጸ።

••••••••••••••••••••••••••••••

Mujib Amino

የንጉሥ አስሃማ ቢን አብጀር-ነጃሺ መስጂድና ኢስላማዊ የምርምር ማዕከል ዐቢይ ኮሚቴ ከፌደራል መጅሊስ አመራሮችና ስራ አስፈጻሚ፣ ከባለሙያዎች ፣ ከየክልሎች የመጅሊስ ተወካዮችና ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ ኤሊያና አዳራሽ በቀጣይ ግንባታዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ምክክር አድርጓል።

ሊሰራ በታቀድዉና በቅርቡ በሚጀመርዉ የንጉሦ ነጃሺ መስጂድ የግንባታ ዲዛይንና ይካተታሉ ከተባሉ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ገለጻ ተደርጎ ከታደሚዎች መሻሻል ስለሚገባቸዉ ጉዳዮች ላይ መክሯል።

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤ ፕሬዝደንት ልዩ አማካሪና የግንባታዉ ብሄራዊ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ የንጉሥ ነጃሺ ግንባታ ኢስላማዊነቱንና የማህበረሰቡ መገለጫነቱን በጠበቀ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን አንድነት በሚያሳይ መልኩ እንደሚገነባ አበስረዋል።

የንጉሥ አስሃማ ቢን አብጀር ነጃሺ መስጂድና ኢስላማዊ የምርምር ማዕከል 3 ዋና ዋና የግንባታ መዋቅር ያለዉ ሲሆን አንደኛዉና ዋነኘዉ የመስጂድ ስፋራ ነዉ። ይህ የመስጂድ ስፍራ ከ 12-18 ሺ ምዕመናን እንደሚያስተናግድ እቅድ ተይዞ በሀገራችን ትልቁን ስፍራ እንደሚይዝ ይገመታል። ከዚሁ የመስጂድ ስፍራ በታችም እስከ 1500 ተሽከርካሪዎችን የመያዝ አቅም ያለዉ ፓርኪንግም ይሰራል ተብሏል።

በፕሮጀክቶቹ ላይ ከተካተቱት ዉስጥ የማህበረሰብ አቀፍ ማዕከል ሲኖር የባህልና ኢግዚብሽን ፣ሙዚየምና ላይብረሪ ፣የአካል ብቃትና ጤና ማዕከል፣ ለወጣቶችና ለልጆች (ለህፃናት) አገልግሎት የሚሰጡት ማዕከላትን ያካትታል ተብሏል።

ሶስተኛዉ የፕሮጀክቱ አካል የሆነዉ የንግድ ማዕከል ሲሆን ንግድና የችርቻሮ ሱቆች ይኖሩታል ተብሎ ይጠበቃል።

የኮሚቴዉ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ከባለድርሻ አካላት የቀረቡትን ጥያቄና አስተያየት በመቀበል ግብዓት ወስደዋል።

የንጉሥ አስሃማ ቢን አብጀር ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ በቅርቡ ወደስራ ይገባል።

ኢንሻ አሏህ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group