UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

በጣም አስተማሪና ድንቅ ግጥም ጨርሳችሁ አንብቡት

.............ማን ይሆን ?...........

ማን ይሆን ከኛ ውስጥ ኸቲማው ያማረ

ሞት የቀለለለት ጉዞው የሰመረ

ለማን ይሆን ምቹ የጨለማው ቤቱ

አላህ የከበበው በሰፊው ራህመቱ

ተነስ ተብሎ ጡሩንባ ሲነፋ

ውስጡዋ ያለን ሁሉ መሬት ስትተፋ

ማን ይሆን ከኛ ውስጥ ትልቅ ባለተስፋ

ባይተዋር የማይሆን መንገድ የማይጠፍ

ማን ሞተ ከኛ ውስጥ በሀጅ ላይ እያለ

ነገን የሚነሳ ለበይክ እያለ

በጅሀድ ማን ሞተ እምነቱን አንግሶ

ነገን የሚወጣ በደም ተለውሶ

እንደ እሳት እራት ሲጨናበስ ኸልቁ

እነማን ይሆኑ በውጤት የላቁ

ክስተቱን ያልፈሩ መውጫውን ያወቁ

በመህሸር ላይ ቆሞ የሰው ልጅ ሲታመስ

ዋ! ነፋሴ እያለ ሁሉም ሰው ሲላቀስ

ማን ይሆን ከኛ ውስጥ ከውስጣችን እያለ

ነገን ማይደነግጥ ጭንቁ የቀለለ

ሰው ጠላቱ ሲሆን የልብ ጓደኛ

አላህ የወደደው ማን ይጠራል ከኛ

ሰው በላቡ ሲጠመቅ በጥም ሲተራመስ

ከነብያችን ሀውድ ማን ይሆን የሚቀምስ

ፀሀይ ስትቀርብ የስንዝር ያህል

ማን ይሆን ከኛ ውስጥ በጥላው የሚውል

ሰው ሁሉ ሲሰለፋ ለምርመራ ሲቀርብ

ውጤቱን ለማወቅ ሲጨነቅ ሲጠበብ

ከኛ ውስጥ ኪታቡን ማን ከቀኝ ያገኛል

እዩልኝ እያለ ሰዎች ይጋብዛል

ሰው ሁሉ ጎድሎበት በዕዳ ሲፈላለግ

ከወላጅ ከሚስቱ ከልጁ ሲደበቅ

የኸይር ሚዛኑ ማነው የሚደፍ

ደስታው ልክ ያለፈ ሀሴቱ የሰፍ

ኧረ ማነው ከኛ አላህን የፈራ

መልካሞች ጋር ነገን የሚጠራ

ማን አለ ከኛ ውስጥ በሚስጥር የሰራ

በለሊት ተነስቶ እንባውን የዘራ

ከፈጣሪው ጋራ በሚስጥር ያወራ

ፊቶች ሲጨልሙ ፊቱ የሚያበራ

ማን ይሆን ከኛ ውስጥ የሸፉዓ ብቁ

መሄጃ ጠፍቶዋቸው ሰዎች ሲጨነቁ

ማንን ያናግራል አላህ ጠጋ ብሎ

ከሰው ሁሉ መርጦ ከህዝቦች ነጥሎ

ሰው ሁሉ ሲዋረድ በፋርዱ አደባባይ

ማነው ከኛ መሀል በዙፋን የሚታይ

ከኛ መሀል ማነው ህልሙ የሚሳካ

የፈጣሪውን ፊት አይቶ የሚረካ

ማነው ከኛ መሀል በስም የሚጠራ

ከእናት ከአባቱ ከሚወደው ጋራ

እነማን ይሆኑ ነገን የሚያዩ

ሰዎች በስራቸው ደረጃ ሲለዩ

ከሰባ ሶስቱ /73/ ሰልፍ አንዱ የጀነት ሲሆን

ማነው ከኛ መሀል ከአንዱ የሚሆን

የእኔ እና እናንተ ምን ይሆን እጣችን

ከየትኛው አንጃ ይሆን ምድባችን

ማነው ከኛ መሀል በእርግጥ ያልታደለ

የአላህ ራህመት ሰፊ ሆኖ ሳለ

ከጀሀነም እሳት ይግባ የተባለ

ጀሀነም ስትራብ ሰው ስታነፈንፍ

ያዳለጠው ሲወድቅ ትረፍ ያለው ሲተርፍ

ማን ይሆን ሲራጡን የሚያልፈው በሮ

የእሳቱን ጉድጓድ ወደኋላ ጥሎ

ሰው ሳቅ በሳቅ ሆነ ዋለ ሲፈነድቅ

ለረጅሙ ጉዞ ትንሽም ሳይሰንቅ

እንዴት ዋልክ ሲሉት ሰው ደህና ነኝ እያለ

ቀብር የሚባለው ከፊቱ እያለ

እንደምን ነህ ሲሉት ሰው ሰላም ነኝ እያለ

ሲራጥ ሳይታለፍ የምን ሰላም አለ

ሲራጥ ሳይታለፍ የምን ሰላም አለ።

https://ummalife.com/marufabadir

Maruf Abadir | UmmaLife

Maruf Abadir | UmmaLife

I am medical student in wolkite university inshallah i will share contents focus on Science, Health and Islam.
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ኡማው ቢስተካከል እስልምና ይነሰራል!!

ይህ የሁሉም ሙስሊም እምነት እና ምኞት ነው። ግን ትልቁ ችግራችን: ሁላችንም ሌሎች ተስተካክለው እንዲገኙ እንመክራለን እንጂ ራሳችንን ለማስተካከል አንጥርም።።

ወንድም አለም "ኡማ" የሚባለው እኮ እኔ እና አንተ ነን። "የኡማው መስተካከል" ሲባል የሆነ እንደ ሰላማዊ ሰልፍ ሁሉም "ሆ" ብሎ ወጥቶ ተስተካክሎ የሚገባበት ፕሮግራም አይደለም፤ እኔ ራሴን ሳስተካክል፣ አንተም ራስህን ስታስተካክል: የዛኔ ኡማው ይስተካከል እና ነስሩ ይመጣል።

አሁንም ሌላ ሰው እንዳታስብ 🫵አንተ! አዎን አንተ ራስህ! እስኪ ቆም በልና ከእስልምና ጋ ያለህን ትስስር ፈትሽ። ወላህ! በአላህ እዝነት እንጂ ጥፋት ላይ ነው ያለነው፤ አላህ ከእዝነቱ ከጥፋት ስንመለስ ያጣነው ክብር ይሰጠናል እናም ዛሬውኑ እንመለስ!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Abdullah Muhammed Сhanged his profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group