yahya Husen Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

yahya Husen shared a
Translation is not possible.

ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ!

🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢

በትንሹ ለ100 ሺህ ዓመታት ቀብርህ ውስጥ ምን ትሰራለህ? ከደጋጎቹ አንዱ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ። "በርግጥ ለደጋጎች ካልሆነ በቀር ቀብር አስፈሪ ነው። ዱንያንና ውስጧን እጅግ የምጠላ ስሆን አሁን እድሜዬ 54 ነው። በትንሹ ቀብሬ ውስጥ ለ100 ሺ ዓመታት ምንድን ነው የምሰራው? ስል አሰብኩ።

እናም እንደሚከተለው መስራት ጀመርኩ ። እኔ እንደሆነ እሞታለሁ፣ የሚጠብቀኝም ሙሉ በሙሉ ጨለማና ባዶ የሆነ ቀብር ነው። እናም ይህ ቀብር ጌጣጌጥ ይሻል፣ የማደርጋትን እያንዳንዷን ኢስቲግፋርና አዝካር ብቸኝነቴን ያጫውተኝ ዘንድ ወደ ቀብሬ ቀድሞ እንዲጠብቀኝ እየላኩት ነው ብዬ ማሰብ ጀመርኩ። እውነቴን ነው አልቀለድኩም፣ የቀብሬን ለሕድ በሺዎች በሚቆጠሩ ተስቢሖች ማጌጡን ተያያዝኩት።

እዚህ ሳለሁ በትንሹ 300 ጊዜ ቁርአንን ቀርቼ አኸትመዋለሁ፣ እያንዳንዷን የሰላት ረከዐ ለቀብር ሒሳብ አካውንት ላይ ጥሪት አድርጌ አስባታለሁ፣ ሁሉም ጥሎኝ ወደ ቤቱ ይመለሳል፣ ምናልባት ብቻዬን ሚሊዮን ዓመታትን እዛ ነኝ። ቀብሬ የግድ ጨፌ፣ ብርሃናማ እና የምርም ጀነት መሆን ይኖርበታል።

እናም ከእያንዳንዷ መልካም ተግባር፣ ከዚክርና ቁርአኔ፣ ከሰደቃና ተሸሁዴ በነርሱ ተከብቤ አብረን ስንስቅና ስንጫወት በእዝነ ህሊናዬ አስባለሁ። በዚህ ጨዋታ መሃል በረሱሉ (ሰዐወ) የተደረገ ሶለዋት ጨዋታውን ሲካፈል አስባለሁ። ከሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወት....

ምድር ላይ ሳለሁ ከሃሜትና ነገር ማዋሰድ፣ ለአላህ ተብሎ ካልተሰራ ስራዬ ውጤት ማለትም ከጭንቀት፣ ከቅጣትና ከጨለማና ቅጣት አይሻለኝም?!

ከዛሬ ጀምሮ ለናንተ ያለኝ ምክር ይላሉ ይህ ደግ ሰው

ቀብራችሁን ባንክ አድርጉትና ሁሌም ከመልካም ስራዎች ጣል እያደረጋችሁበት ሙሉት። በዒባዳዎች ላይ ጠንክሩ። ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ፣ ከዱንያ ይልቅ ለወዲያኛው ዓለም ተጠበብ።

አሁንማ ቤተሰብ መሃል ሆነህ ያሻህን ትለብሳለህ፣ ትመገባለህ እንዲሁም ደስ ብሎህ እንቅልፍህንም ትተኛለህ። ሁሉም ፍላጎቶቻችን ተሟልተው እንኳ ተጨባጫችንን እናማርራለን። ይህ ምቾት ማጣት እስቲ ከምድር ሆድ ውስጥ ቢሆን ብለህ አስበው?!

ስለዚህ እያንዳንዷን ተስቢሕ በትኩረት አድርግ፣ መልካም አጫዋችና አቀማማጬ ትሆኝልኝ ዘንድ ቀብር ቀድመሽ ጠብቂኝ በላት።"

[ሐሳቡ (አላህ ይዘንላቸውና)የዶክተር ሙስጠፋ ማሕሙድ ነው።]

Send as a message
Share on my page
Share in the group
yahya Husen shared a
Translation is not possible.

ገደልነው ሲሉ ህያው ሞተ ሲሉም እየዳነ ዛሬም ድረስ በህይወት ያለ ተንቀሳቃሹ ሰማዕት። ተራማጁ ሸሂድ። የማይነጥፍ የወንድነት ባህር! የፍልስጤማዊያን ኩራት! የዘመኑ አብሪ ኮከብ! የጦር ሊቅ! የኬምስትሪ ደቂቅ። ፍፁም ትሁት አስተዋይና ለስላሳ ቁጥብነትን የተላበሰ ጀግና። መልካም ልብ፣ ደግ ማንነትን የታደለ ወንድ።

ጌታዬ ሆይ!

ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑልወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ

© mahimahisho

የሚያሰማራቸው ወታደሮች፣ አብላልቶ የሚተኩሳቸው ሮኬቶች የወራሪዋን ራዳር ጥሰው ሰማዩን እየሰነጣጠቁ ጠላትን ማሸበር ከጀመሩ እነሆ 23 አመታት ተቆጠሩ። የእስራኤል የስለላ ተቋም ሮኬቶቹ ሲሰሩ እንኳ አያቅም። ተምዘግዛጊ ሮኬቶችን እንደታጠቁ ያወቁት በ2001 አየሩን ሰንጥቀው ከተማቸው ውስጥ ሲያርፉ ነው።

ከእነዚህ ሮኬቶች ጀርባ አንድ የኬምስትሪ ምሩቅ አለ። ለዚህ ብሎ የተማረ። ብረትን ከፖታሺየም ናይትሬትና የወዳደቁ እቃዎችን ከማዳበሪያ ጋር ቀምሞ በቆርቆሮ ሲሊንደር አብላልቶ ሮኬቶቹን የሚያዘጋጅ ታንክን በዲንጋይ የገጠመ ፍፁም ለአላህ ያደረ ዓቢድ። ባመሸበት ቦታ የማያድር ባረፈደበት መንደር የማይውል። በእናቱ ቀብር ላይ እንኳ ያልተገኘ ፍፁም ጥንቁቅ።

ሞሳዶች አስማተኛው ሰይጣን ይሉታል። ከጠቅላይ ሚኒስቴር ሽሞን ፔሬዝ እስከ ቢኒያሚን ኔታንያሆ በሰማይ በምድር የሚፈለግ ረብጣ ዶላር መድበው ደህንነቶቻቸውን አሰማርተው የዛሬሀያ ስምንት ዓመት እንዲገደል ትዕዛዝ ያስተላለፉበት የጋዛው ኮማንደር።

በማለዳ ተነስተው ከስክስ ጫማቸውን አጥልቀው ተራራውን ሮጠው ያላገኙት፣ የጥይት አሩር እየተኮሱ ቦንብ ከአውሮፕላን ቢያዘንቡ ፍፁም ሊገሉት ያልቻሉት የፍልስጤማዊያን ቁልፍ ሰው።

በእግሮቹ የሚራመድ ሸሂድ ቢሉት አትገረሙ። በእርግጥም ልክ ናቸው። ብዙ ጊዜ ከሞት ድኗል። የሞሳድ ደህንነቶች ከጓደኞቹ በአንዱ የእጅ ስልክ ላይ የተጠመደውን ፈንጂ ተኩሰው ሲገድሏቸው፣ መኪናው በድሮን ተደብድባ ሁለት ጠባቂዎቹና አንድ ረዳቱ ሲገደሉ እርሱ ተርፏል። የተማረበትን ዩንቨርስቲ ሊጎበኝ በሄደበት F1 የጦር ጀቶች ዩንቨርስቲውን ዶግ አመድ ሲያደርጉት በህይወት ድኗል። የእስራኤል አየር ኃይል ጋዛ በሚገኘው መኖርያ ቤቱ ላይ ድብደባ ፈፅሞ ሚስቱና ሁለት እንቦቃቅላ ልጆቹን ገድሎ የሙጃሂዶቹን አከርካሪ አጥንት ሰበርነው አዎ አስወገድነው ገደልነው ብለው በደስታ ውስኪ ሲራጩ ነፍሱ አዛኙንና ኃያሉን አላህ ለመገናኘት አልተፈቀደላትም ነበርና አለሁ ብሎ ብቅ ብሏል።

ሙሐመድ ዲያብ ኢብራሒም ይሰኛል። ፍልስጤማዊያን ደይፍ ይሉታል እንግዳ እንደማለት ነው። በእርግጥም እርሱ በወራሪዋ ደህንነቶች ታድኖ ሊገደል፣ ተጠፍሮም ሊያዝ ያልቻለ አሳዳጆቹ እጅ ሳይገባ ሀያ ስምንት አመታቶችን ያስቆጠረ ሁሌም እንግዳ ሰው ነው።

የሙስሊሞች ለቅሶ የእናቶች እሪታ፣ የልጆች ስቅስቅታ በጆሮው ሲንቆረቆር ለበይክ ብሎ በለጋ ዕድሜው የተነሳ ወጣትነቱን በትግል ያሳለፈ ትንታግ ነው። ወንድሞቹ ሲሞሻለቁ፣ እህቶቹ በድምፅ አልባ መሳሪያ ሲወቁ ትከሻም ልቡም ለመሸከም አልፈቀዱለትም፡፡ ድንቡሽቡሽ ፊት ያላቸው እንቦቃቅላ ልጆቹን ትቶ፣ የእናቱን የእጅ ደበሳ ርቆ በጂሃድ ሜዳ ላይ ተሰየመ፡፡

የብሩህ አዕምሮ ባለቤት የመሐፈዝ አቅሙ ከፍተኛ የሰማውን ቀብ፣ ያየውን ልቅም አድርጎ የሚይዝ ፈጣን ነው። በየትኛውም ቴሌቪዥን ታይቶ አይታወቅም። ምንም አይነት ቴክኖሎጂ የማይጠቀም ባለ ዊልቸሩ የጦር መሪ።

አባቱ ልብስ እየሰፉ በአነስተኛ የዶሮ እርባታ እንቁላል እየሸጡ ያሳደጉት ልጅ ዛሬ ስሙን እንጂ ማንነቱን ለማወቅ ከብዷል። አላህ ረጅም ሐያት ከሙሉ አፊያ ጋር!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
yahya Husen shared a
1 year Translate
Translation is not possible.

"አል-አቅሷዐ በመስቀላዊያን እጅ ውስጥ ሆኖ ሳለ እኔ እንዴት ፈገግ ልል እችላለሁ? ምግብ እና ውሃ ከእኔ ጋር እንዴት ጣዕም ሊኖራቸው ይችላል?!" ይህ ቁድስን ከወራሪዎቹ የመስቀል ጦረኞች ነፃ ሳያወጣ በፊት አንድ ጊዜም ፈገግ ብሎ የማያውቀው የጀግኖቹ ጀግና የኩርዳዊው #ሰላሁዲን_አልአዩቢ ንግግር ነበር!

የቅርቡን የዚህችን እጅግ ጥንታዊት ከተማ ታሪክ እናንሳ እንኳ ቢባል ለ በርካታ መቶ አመታት በባይዛንታይን ሮሞች አረመኔያዊ አገዛዝ ስትማቅቅ የቆየችው ቁድስ በነ #ኻሊድ_ኢብን_ወሊድ እና #አቡኡበይዳ_ኢብን_አልጀራህ የሚመራው ጦር ባይዛንታይኖችን አንበርክኮ ቁድስ ዳግም በሙስሊሞች እጅ ለመግባት ችላ ነበር። የቁድስን ቁልፍ ቦታው ድረስ ሂደው የተቀበሉት #ኡመር_ኢብኑል_ኸጧብ የቁድስን ነዋሪዎች ነፃነት አውጀው ነበር የተመለሱት። ቁድስ ከዚያ በሗላ በፍትህና በኢስላማዊው ስልጣን ተንቆጠቆጠች። በኡመር ጊዜ ሙስሊሞች ከተቆጣጠሯት በሗላ ቁድስ እስከ መጨረሻው በሙስሊሞች እጅ አልቆየችም። የሙስሊሞችን መከፋፈልና እርስበርስ መባላት ተጠቅመው ባይዛንታይኖች ዳግም ቁድስን ተቆጣጠሩ። ቁድስ ዳግም የጨለማ ዘመን ውስጥ ገባች። ከተማዋን በደል ግፍና ጭካኔ ሞላት! በከተማዋ የሚስኪኖች ዋይታና የገዥዎች ከልክ ያለፈ አረመኔነት እንጅ አይሰማም አይታይም ነበር! ቁድስ በባይዛንታይኖች እንደዚህ በበደል ተውጣ ቆዝማ አዝና ብዙ አመታትን አሳለፈች! አሏህ #ሰልጁቅ የተሰኙ ቱርኮችን ከወደ ምስራቅ ኤዥያ አስነሳ። የሰልጁቅ የልጅ ልጅ የሆኑት እነ #ቱግሪል#ቻግሪ#አልፕ_አርስላን#መሊክ_ሻህ የመሳሰሉ ተወዳዳሪ አልባ ጀግና የጦር መሪዎች የአለም ልእለሀያል የነበረውን የባይዛንታይን ሮም ስርወመንግስት ስብርብር አድርገው የቱርኮች የኢስላም ገባሪ አደረጉት። ከሰልጁቆች ጎሳ #ከኪኒክ የሚመዘዘው የሰልጁቆቹ ጦር መሪ #አቲሲዝ_ቤይ ባይዛንታይኖችን አንኮታኩቶ ዳግም ቁድስ ነፃ አወጣት። አላህ ዲኑን በማን እንደሚረዳው ይአጅባል። ገና ከሰለሙ ጥቂት አመታትን ያስቆጠሩት ሰልጁቅ ቱርኮች የኢስላም ቅዱስ ከተሞችን በሙሉ አስመልሰው ከቻይና እስከ ሮም ያሉ የኢስላም ጠላቶችን በጉልበቶቻቸው አንበረከኳቸው። በሃያሎቹ ወራሪዎች የሰልጁቆች የአባሲድና የኸዋርዚም ሙስሊም መንግስታቶች ሲደመሰሱ አሁንም ዳግም አውሮፓዊያን ተባብረው "የመስቀል ጦርነት" በሙስሊሞች ላይ አወጁ። ሁሉንም የአውሮፓ መንግስታት ባካተተውና በጳጳስ ክሊመንት በተባረከው በዚህ ጦርነት ሙስሊሞች እንደ ቅጠል ረገፉ! ኢየሩሳሌምን ( ቁድስ ) የሰው ደም ሀይቅ ሆኖ ተንጣለለባት። ህፃናት አዛውንት ሳይሉ ፣ ሴት ደካማ ሳይሉ መስቀላዊያኑ ሁሉንም በሰይፋቸው አረዷቸው። ቁድስም ዳግም በጭራቆች እጅ ገባች። ቁድስን ዳግም ማስመለስ የአንድ በአሁኗ የኢራቋ ቲክሪት ከተማ የተወለደ ኩርዳዊ ሙጃሂድ ተራ ሆነ። ያ ሙጃሂድ የሙጃሂድ ልጅ ሰላሁዲን አልአዩቢ ይባላል። ሰላሁዲን በሰልጁቅ የጦር መሪ በነበረው በኢማዱዲን ዘንኪ ልጅ በኑረዲን ዘንኪ አመራር ስር ሆኖ በወታደራዊ ክህሎት ተኮትኩቶ በኡለሞች ተርቢ ታንፆ አደገ። አባቱ ሰላሁዲንን ከልጆች ጋር ሲጫወት ባገኘው ጊዜ ብድግ አደረገና ፍርጥ አደረገው። እና ተቆጣው ሰደበው "እኔ አድገህ ቁድስን ታስመልሳለህ እያልኩ አንተ እዚህ አቧራ ታቦናለህ?" አለው። ሰላሁዲን አላለቀሰም። ለምን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃልና።

ሰላሁዲን ቁድስን ነፃ ሳያወጣ በፊት ስቆ አያውቅም ተደስቶ አያውቅም። ያ የአሏህ ወልይ በቱርኮች ጥምረት መላው የአውሮፓ መስቀላዊ ጦርን ደምስሶ ኢየሩሳሌም ( ቁድስን ) ዳግም ነፃ አወጣ።

ከዚያ በሗላ በግብፅ የነገሱት ቱርኮቹ ማምሉኮች ተረክበው ኢየሩሳሌምን ጠብቀው አ hiቆዩ።

ከነርሱ በሗላ የአለማችን የምንጊዜውም ሀያሉ ኢምፓየር የሚሰኘው የኦቶማን ኺላፋ ( ደውለቱል ኡስማኒያ ) ቦታውን ተክቶ በየትኛውም የአለም ጫፍ ያለን የኢስላም ሉአላዊነት ሳያስደፍር ለ 500 አመታት ቀጥ አድርጎ ገዛ። ያኔ እንኳንስ ቁድስንና ትሪፖሊን እንኳ ማጥቃት የኦቶማኖችን ጀሃነም ያስከትላል። አውሮፓን በእንብርክኳ ያስኬዳት ፣ ሩሲያን ወገቧን የሰበራት ያ የኦቶማን ኺላፋ እስከ ውድቀቱ መጨረሻ ድረስ ቁድስን መካንና መድናን ለጠላት አሳልፎ አልሰጠም ነበር!

#አሁን_ቁድስ ከአንደኛው የአለም ጦርነት በሗላ #በክርስቲያን_አይሁዳዊያን ጥምረት ስር ነች። እነሆ ቁድስ ማንባት ከጀመረች ድፍን አንድ ክፍለዘመን ሊሞላት ነው።

እና ከዚያ ሁሉ ጨለማ የወጣች ቁድስ አላህ አሁን ሌላ ሰላሁዲን ፣ ሌላ አቲሲዝ ቤይ ፣ ሌላ አልፕ አርስላንን አይልክላትም ብላችሁ ታስባላችሁ??? በፍፁም አታስቡ !

ወድቆ መነሳት ፤ ጨለሞ መብራት የቁድስ ተፈጥሮዎች ናቸው !

ቁድስን አንድ ጊዜ አረቦች ፣ 3 ጊዜ ቱርኮች አንድ ጊዜ ኩርዶች ነፃ አውጥተዋታል ! አሁንስ እነማን የነፃነት ሰንደቁን ይዘው ቁድስን ነፃ ያወጡ ይሆን? ሁሉንም ጊዜ ያሳየናል! ግና አትጠራጠሩ ቁድስ ነፃ ትወጣለች።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group