UMMA TOKEN INVESTOR

ሰባቱ(7) የ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› መስፈርቶች (ሸርጦች)

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ ናበጣም አዛኝ በኾነዉ፦

1.✍ዕውቀት፡- ይህም ማለት የዚህ ቃል መልዕክት እና ቃሉ ዉድቅ

የሚያደርጋቸዉንና እና የሚያፀድቃቸውን ነገሮች ጠንቅቆ ማወቅ ማለት ነው፡፡

ለዚህም ማስረጃው ቀጣዩ የአላህ ቃል ነው፡፡

ﻭَﻟَﺎ ﻳَﻤْﻠِﻚُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺪْﻋُﻮﻥَ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻧِﻪِ ﺍﻟﺸَّﻔَﺎﻋَﺔَ ﺇِﻟَّﺎ ﻣَﻦْ ﺷَﻬِﺪَ ﺑِﺎﻟْﺤَﻖِّ ﻭَﻫُﻢْ ﻳَﻌْﻠَﻤُﻮﻥَ

ﺍﻟﺰﺧﺮﻑ : ٨٦

(እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸዉ እነሱ የሚያውቁ ሆነው በእውነት

ከመሰከሩት በስተቀር ምልጃን አይችሉም) አል-ዙኸሩፍ 86

2✍.እርግጠኛነት፡- በአላህ ብቸኛ አምላክነት ላይ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆን

ነው፡፡አላህ (ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡-

ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺭَﺳُﻮﻟِﻪِ ﺛُﻢَّ ﻟَﻢْ ﻳَﺮْﺗَﺎﺑُﻮﺍ ﻭَﺟَﺎﻫَﺪُﻭﺍ ﺑِﺄَﻣْﻮَﺍﻟِﻬِﻢْ ﻭَﺃَﻧْﻔُﺴِﻬِﻢْ

ﻓِﻲ ﺳَﺒِﻴﻞِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﻫُﻢُ ﺍﻟﺼَّﺎﺩِﻗُﻮﻥَ

ﺍﻟﺤﺠﺮﺍﺕ: ١٥

({እዉነተኞቹ} ምእመናን እነዚያ በአላህና በመልእክተኛዉ ያመኑት ከዚያም

ያልተጠረጠሩት ናቸው) አል-ሑጁራት 15

የአላህ መልእክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) ለአቡ ሑረይራ (ረዲየ አላሁ አንሁ) እንዲህ

ብለውታል፡- ‹‹ ከዚህ አጥር በስተጀርባ የአላህን ብቸኛ አምላክነት ከልቡ

በእርግጠኝነት የሚመሰክር ሰው ብታገኝ በጀነት አበስረው፡፡›› ሙስሊም

ዘግበዉታል

3.✍መቀበል፡- የላኢላሀ ኢለላህን መልእክት (አላህን በብቸኝነት ማምለክን)

ከልብ መቀበልና ለሌላ አካል የሚከናወኑ አምልኮቶችን መተው ነው፡፡ ይህንን

ያልተቀበለ ግን አላህ ኩራተኛነታቸውን እና አለመቀበላቸው እንዲህ በማለት

ከገለፃቸው ሙሽሪኮች መደዳ ይሰለፋል፡፡

ﺇِﻧَّﻬُﻢْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﺇِﺫَﺍ ﻗِﻴﻞَ ﻟَﻬُﻢْ ﻟَﺎ ﺇِﻟَﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻳَﺴْﺘَﻜْﺒِﺮُﻭﻥَ

ﺍﻟﺼﺎﻓﺎﺕ: ٣٥ – ٣٦

(እነርሱ፤ ‹ከአላህ ሌላ አምልኮት የሚገባው ሆኖ የሚመለክ አምላክ የለም›

በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበር፡፡ እኛ ለእብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው

ነን ይሉም ነበር፡፡) አልሷፋት 35-36

4.✍መታዘዝ፡- ይህ ማለት ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› የሚለው የምስክርነት ቃል

ለሚያመላክታቸው ትዕዛዛትና ክልከላዎች ሙሉ ታዛዥ ተከታይና ተናናሽ መሆን

ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

ﻭَﻣَﻦْ ﻳُﺴْﻠِﻢْ ﻭَﺟْﻬَﻪُ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﻫُﻮَ ﻣُﺤْﺴِﻦٌ ﻓَﻘَﺪِ ﺍﺳْﺘَﻤْﺴَﻚَ ﺑِﺎﻟْﻌُﺮْﻭَﺓِ ﺍﻟْﻮُﺛْﻘَﻰ ﻭَﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ

ﻋَﺎﻗِﺒَﺔُ ﺍﻟْﺄُﻣُﻮﺭِ

ﻟﻘﻤﺎﻥ : ٢٢

(እርሱ መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን (በመታዘዝና በመተናነስ) ወደ አላህ የሚሰጥ

ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ…)

ሉቅማን 22

5.✍ እውነተኝነት፡- የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል በሚሰጥበት ጊዜ

እውነተኛ መሆን ማለት ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ

‹‹ማንኛውም ከልቡ በእውነተኛነት በአላህ ብቸኛ አምላክነትና በሙሐመድ

(ሰ.ዐ.ወ) መልዕክተኝነት የሚመሰክር ሰው አላህ ከእሳት እርም ይለዋል ››

ቡኻሪ ዘግበዉታል

6.✍መውደድ፡- ይህ ማለት ላኢላሀ ኢለላህ የሚለውን የምስክርነት ቃል ፣ አላህን

እንዲሁም አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩትን የተውሂድ ሰዎችን መውደድ ነው፡፡

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል ፡-

( ﻭَﻣِﻦَ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﻣَﻦْ ﻳَﺘَّﺨِﺬُ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺃَﻧْﺪَﺍﺩًﺍ ﻳُﺤِﺒُّﻮﻧَﻬُﻢْ ﻛَﺤُﺐِّ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﺃَﺷَﺪُّ

ﺣُﺒًّﺎ ﻟِﻠَّﻪِ

ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ: ١٦٥

(ከሰዎችም አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን

(ጣዖታትን) የሚይዙ አሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ)

ይበልጥ የበረቱ ናቸው) አል በቀራህ 165

7✍ማጥራት፡- ይህም ማለት የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል የሰጠ ሰው

ስራውን ከሽርክ ማጥራት አለበት፡፡ እንዲሁም በዚህ የምስክርነት ቃል የዱንያ

ጥቅማጥቅሞችን ከመከጀል፣ ከይዩልኝ እና ይስሙልኝ መጥራት አለበት፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ‹‹የቂያማ ዕለት የኔን ምልጃ

በማግኘት ዕድለኛ የሚሆነው ላ ኢላሀ ኢለላህን ከልቡ ያለ ሰው ነው፡፡››

🎀ቡኻሪ ዘግበውታል🎀

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በዚህ ሰሞን መደሰት እንደክህደት ይሰማን ጀምሯል። ከአልጋችን መተኛትም ክህደት መስሎ ይታየናል። መሳቅ እንኳን ይከብደናል፣ እነሱ አዝነው ሳለ የኛ #መሳቅ_ትልቅ ክህደት ሆኖብናል።

ባለፉት ሳምንታት በምንም ጉዳይ መደሰት በእነሱ ሀዘን ላይ ክህደት እንደመፈፀመ ይሰማናል።

ምንም ማድረግ ካለመቻላችን የተነሳ በህይወት መኖራችን ያሳፍረናል።

‹‹እንዴት አደርክ?›› ለሚለው ጥያቄ ምላ

ሽ አጥተናል።

አዎን! እምነት ያስተሳስረን ወገኖቻችን ጎድለውብናል። አላህ ቃልህን ምትሞላ ነህ'ና ቃል የገባህልንን ድል አሳየን!

Follow

Send as a message
Share on my page
Share in the group
DILU.UmmaLifeMedia Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

መለስ ዜናዊን (ላ ረሒመሁላህ) ጠየቁት፦

«አሚሶም ይህን ያህል ዘመቻዎችን በአልሸባብ ላይ እያካሄደ እንዴት አልሸባብን ማጥፋት አልተቻለም? »

መልሱ የሚገርም ነበር ፦

« ሞቼም ድል አደርጋለሁ የሚልን ሰራዊት መጋፈጥ ፈተና ነው» ነበር ያላቸው።

መለስ እዚህ ጋር ሐቅን ተናግሯል። አንድን ሰው ትልቁ የምታስፈራራበት ነገር ሞት ነው። «አንተ ስትገድለኝ ጀነት እገባለሁ» የሚልን ሰው ግን በምን ታስፈራራዋለህ?  በምንም!!!!!!!!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በዚህ ሰሞን መደሰት እንደክህደት ይሰማን ጀምሯል። ከአልጋችን መተኛትም ክህደት መስሎ ይታየናል። መሳቅ እንኳ ይከብደናል፣ እነሱ አዝነው ሳለ የኛ መሳቅ ትልቅ ክህደት ሆኖብናል።

በዚህ ሰሞን በምንም ጉዳይ መደሰት በእነሱ ሀዘን ላይ ክህደት እንደመፈፀም ይሰማናል። ምንም ማድረግ ካለመቻላችን የተነሳ በህይወት መኖራችን ያሳፍረናል። ‹‹እንዴት አደርክ?›› ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አጥተናል።

አዎን! እምነት ያስተሳሰረን ወገኖቻችን ጎድለውብናል። ኢላህ ቃልህን ምትሞላ ነህ'ና ቃል የገባህልንን ድል አሳየን!

Follow

Send as a message
Share on my page
Share in the group