*#ሱረቱ ዩሱፍ✍️*
ሱረቱ ዩሱፍ ማግኘትም፣ ማጣትም፣ ደስታም፣ ሐዘንም፣ ዉድቀትም ስኬትም፣ መታመንም መከዳትም፣ ፍቅርም ጥላቻም፣ ስደትም ለአገር መብቃትም፣ ከሚወዱት መለየትም መገናኘትም … የተተረከባት ድንቅ ምእራፍ ናት፡፡
በምዕራፏ መጀመርያ ላይ አላህ ለነቢዩ እንዲህ ይላቸዋል:-
نَحْنُ نَقُصُّ عَلَيْكَ أَحْسَنَ الْقَصَصِ بِمَا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ هَـٰذَا الْقُرْآنَ وَإِن كُنتَ مِن قَبْلِهِ لَمِنَ الْغَافِلِينَ
እኛ ይህንን ቁርኣን ወደ አንተ በማውረዳችን በጣም መልካም ዜናዎችን በአንተ ላይ እንተርክልሃለን፡፡ እነሆ ከእርሱ በፊት (ካለፉት ሕዝቦች ታሪክ) በእርግጥ ከዘንጊዎቹ ነበርክ፡፡(ሱረቱ ዩሱፍ - 3)
ለካስ ምርጥ ታሪክ የደስታ ብቻ አይደለም፡፡ የዱንያ ላይ ዉጣዉረዶቻችን ሁሉ ምርጥ ታሪኮቻችን እንደሆኑ አስቧቸው፡፡
የአንድን ነቢይ ሙሉ ታሪክ የያዘች ብቸኛዋ የቀርኣን ምዕራፍ ናት፡፡ ምዕራፏ ዩሱፍ በጉድጓድ ተጥሎ ከአባቱ ተነጥሎ በባርነት ሩቅ አገር ተሽጦ ባለሥልጣንም ሆኖ ያለፈበትን ታሪኮች ሁሉ ትጠቅስና በመጨረሻም የህልሙን ስኬትም ታወሳለች፡፡
አልም ተስፋ አድርግ፣ ጣር፣ ታገል፣ በአላህ ተመካ አላህ የታጋዮችንና የመልካሞችን ጥረት አይዘነጋምና፡፡ ነብዩላህ ዩሱፍ ከዛ መከራ ሁሉ አልፈው ትልቅ ስልጣን አጊንተው አባታቸውንና ቤተሰቦቻቸውንም ከገጠር አምጥተው በሰላም ግብፅ ሀገር ላይ ኖሩ!! ህይወት ልክ እንደዚሁ ናት መጀመሪያ ላይ ምንም ችግር (ሙሲባ) ቢገጥመን ሁሉም ነገር አልፎ አንድ ቀን ጥሩ የሆነ ግዜ እንደሚመጣ በሙሉ ልባችን አላህ ላይ ተስፋ ማረግ አለብን ሰው ነንና መፈተናችም አይቀርም። አላህ እንዲህ ይላል:-
أَحَسِبَ النَّاسُ أَن يُتْرَكُوا أَن يَقُولُوا آمَنَّا وَهُمْ لَا يُفْتَنُونَ
ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን? (ሱረቱል ዐንከቡት 2)
በዱንያ ላይ መፈተን ግድ ነውና በሚያጋጥሙን ሙሲባዎች ሶብር (ትዕግስት) ልናረግ የግድ ይለናል።
ዩሱፍን የፈተነች የዕቁብን ያስነባች ነቢያችን ሙሐመድን ﷺ በብርቱ መከራ ዉስጥ ያሳለፈች ዱንያ አንተን ብትፈትን ምኑ ይገርማል?!!
አላህ ከሶብረኞች (ከትዕግስተኞች) ያርገን🤲 አሚን