እሁድ 14/04/2016
:
በትናንትናው እለት በበጥበብ ኢንስቲትዩት አማካኝነት በተዘጋጀ የስልጠና ፕሮግራም ዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር እና ሌሎችም ከመገናኛ መስመር ወደዛ ያሉ ስብስቦች ተሳታፊ የሆኑበት በአይነቱ የተለየ የስልጠና ፕሮግራም ሲከወን ውሏል።
___
➡️ዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር እና ሌሎች ኮተቤ እና ለሚ ኩራ አካባቢ ጀመዐ መስርተው ለመንቀሳቀስ የሚሞክሩ ስብስቦች በአንድነት የኢስላም ልዩ መገለጫዎች በሚል ርዕስ እና ግማሹን የቀን ክፍል ደግሞ ለኢስላም መስራት በሚሉ ርዕሶች ላይ ስልጠናውን ተቋድሷል።
👉🏻በጠዋቱ ክፍለጊዜ ዑስታዙ "በአለም ላይ ካሉ ብዙ ሺ...ሺ እምነቶች ኢስላም በምን ተለይቶባችሁ ሙስሊም ሆናችሁ? " በማለት ፕሮግራሙን ሀ ብሎ የጀመረ ሲሆን አለም የሚታይበትን የተለያዩ መንገዶች በማንሳት እንዲሁም ኢስላም ከሀይማኖትም ከፍ ያለ ዲን እንደሆነ "ኢስላም አጠቃላይ የህይወት አቅጣጫ ነው" በማለት ውብ የሆኑ ሀሳቦችን የኢስላም ልዩ መገለጫዎች በሚል ርዕስ ሲያነሳሳልን ቆይቷል። እኛም ጥሩ ነገር እንደወሰድንበት ተስፋ አለን አልሀምዱሊላህ።
👉🏻በከሰዐቱ ክፍለ ጊዜ ደግሞ ለኢስላም መስራት ምን ማለት ነው? ሰዎችን ወደ አላህ የመጥራት አላማ እንቅፋቶች ምንዳዎች ብዙ ብዙ ጉዳዮች ላይ ከዑስታዝ አብዱልመጂድ ጋር በማንሳት ጥሩ ቆይታ ተደርጓል ።በዚህ ፕሮግራም ለኢስላም መስራት ግዴታ መሆኑን የሚቃወም አለ ወይ? ተብሎ እንደሌለ ሲያይ ሁሉም በያለበት ግዴታውን ይወጣ በማለት ሀላፊነታችንን እንድንወጣ አሳስበውን እኛም ኢንሻአልላህ ብለን መጥተናል።
👉🏻 ሶስተኛው ፕሮግራም ግን ያው ከተለያየ ጀመዐ ግን የዳዕዋ ድርቅ የመታው ከሚባሉ አካባቢዎች እንደመምጣታችን በየአካባቢያችን ያሉ ኢስላሚክ እንቅስቃሴዎችን እና ጀመዐችንን አስተዋውቀናል በፕሮግራሙ የተሳተፉት ጀመዐዎች ዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር ፣ዳሩሰዐዳ፣ኢብን ሙኽታር ሲሆኑ ይህም አካባቢን ለመቀየር ግድ የሚሰጣቸው ብዙ ወጣቶች እየተፈጠሩ እንደሆነ ማሳያ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።
🩶🩶🩶በመጨረሻም እንደሁሌው ይህን ፕሮግራም አዘጋጅተው ለጋበዙን በጥበቦች እንዲሁም ከእኛ ጋር የተሳተፉትን ሌሎች ጀመዐዎች እናመሰግናለን።🤍🤍🤍