Translation is not possible.

የፍልስጤም ታሪክ

ምዕራፍ -2

እስራኤል ክፉ ፅንስ

ክፍል-4

[ተፃፈ-በአብዱልከሪም ሙሐመድ]

እስራኤል የሚባል ሀገር በፍልስጤም ምድር ላይ ከመወለዱ በፊት ሂደቱን ለማስቆም የተካሄዱ እርምጃዎች ነበሩ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በ ዲሴምበር 1931 ከኢስራዕ-ወል-ሚዕራጅ ቀን ቀደም ብሎ የ22 ሙስሊም ሀገራት ተወካዮችና ታላላቅ ሰዎች በተገኙበት የተካሄደው ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ይጠቀሳል፡፡

በዚህ ፕሮግራም ላይ ሙፍቲ ሙሀመድ አሚን አል-ሁሴይኒ ፍልስጤም እና አል-አቅሷን በኢስላማዊው አለም ውስጥ ያላቸውን ጠቀሜታ አበክረው አስምረውበታል፡፡ በተጨማሪም ኮንፈረንሱ በዚች አገር ውስጥ የፅዮናውያንና የእንግሊዝን እንቅስቃሴ እንዲሁም የአይሁዳዊያንን ፍልሰት እንዴት መግታት ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ መክሯል፡፡

በመጨረሻም የደረሱበት ውሳኔም ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ በእየሩሳሌም (ቁዱስ) ለመስራት፣ ሁሉንም የአይሁዳዊያን ምርት ላይ አገዳ መጣል እና የእርሻ መሬት ወረራውን ለመከላከል ተቋም መመስረት የሚሉት ይገኙበታል፡፡ ከዚህ ቀደም ብሎ በጁላይ የጀነራል አርተር ግሬንፍል ዋቾፕ በፍልስጤም ከፍተኛ ኮሚሽነር ሆኖ ተሾመ፤ እሱም ወደ ፍልስጤም ሲገባ የአይሁዳዊያን መኖሪያ ቤት እውን የመሆን ዋነኛ ራዕይ አንግቦ ነበር፡፡

ለአረቦች የውሸት እቅዶችን በመቅረፅ ለማዘናጋት እና ፍላጎታቸውን ቸል በማለትና የአይሁዳዊያንን ብዛት በቻለው ሁሉ ከፍ ለማድረግ ሲሰራ ቆይቷል፡፡በዚህም እሱ ከመጣ በኋላ በ1932 ወደ 9553 የሚሆኑ ከዛም በ1933 ከ3 እጥፍ በላይ አድጎ 30327 እንዲሁም በ1934 መጨረሻ 42359 አይሁዳዊያን ስደተኞች ወደ ፍልስጤም እንደገቡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በኦገስት 1932 ቀኝ ግዛትንና የአይሁዳዊያንን ፍልሰት ለመዋጋት እንዲሁም አረባዊ አንድነትን ለማምጣት ያለመ ‹የነፃነት ፓርቲ› ተፈጠረ፡፡

ደጋፊና አባላቶቹም የሀገሪቱ በጀት ሲሶው ለመከላከያ ሃይል መዋሉ ለወደፊት ባዕድ ሀገር ያለፍላጎታቸው ለመመስረት እንደሆነ ተገንዝበዋል፤ በዚህም የባልፎር አዋጅን እና የእንግሊዝን ሞግዚትነት እንደሚቃወሙ ገለፁ፡፡

በዚሁ አመት በ1932 የፍልስጤም ወጣቶች እንዴት ለብሔራዊ ንቅናቄ መዘጋጀት እንዳለባቸው የሚያወያይ ኮንፈረንስ በያፋህ ተካሄደ፡፡

በፍልስጤማዊያን ከተወሰዱ እርምጃዎች ውስጥ በ1935 የተካሄደው የሼህ ዒዘዲን አል-ቃሲም አብዮት ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ለገዢዋ እንግሊዝ የሁኔታው አደገኛነት የሚያሳይ ማንቂያ ደውል ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ሼህ ዒዘዲን አል-ቃሲም ከሌሎች ሙጃሂዶች ጋር በመሆን የፍልስጤምን መሬት ከጠላት ለመከላከል ጂሀድ አወጁ፡፡ በዚህም ጀኒን ላይ ከእንግሊዛ ጦር ጋር በመፋለም ምንኛ ያማረ ሰምዓትነትን ተቀዳጁ፡፡

ከአል-ቃሲም ሰምዓትነት 1 ወር በኋላ ከፍተኛ ኮሚሽነር ዋቾፕ በህግ አውጪ ምክር ቤት የተዘጋጀውን እቅድ በፍልስጤም የፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርድ ለቀረበው ጥያቄ እንደምላሽ አቀረበ፡፡

አዲስ ህገ-መንግስት መቅረፅ፣ ዲሞክራሲያዊ አመራርን መተግበር፣ የመሬት ሽያጭ ሁኔታዎችን፣ የስደተኞች ብዛትን ከሀገሪቱ የመቀበል አቅም ጋር የሚያሰላ ስታቲስቲካል ቢሮን መመስረትንና የመሳሰሉትን እቅዱ ቢያካትትም ብዙ ለውጥ ለመፍጠር አልቻለም፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group