Translation is not possible.

የፍልስጤም ታሪክ

ምዕራፍ -2

እስራኤል ክፉ ፅንስ

ክፍል-3

[ተፃፈ-በአብዱልከሪም ሙሐመድ ]

በ1925 ያ ወሮ-በላ ባልፎር የአል-ቁድስን (እየሩሳሌም) ምድር በድጋሚ ረገጠ፡፡ የመጣበትም አላማ አዲሱን የሂብሩ ዩኒቨርሲቲ ምርቃት ፕሮግራም ላይ ለመገኘት ነበር፡፡ የሚገርመው ደግሞ የተገነባው አል-ዛይቱውን ተራራ ላይ ሲሆን በ1918 ከባለቤቶቹ (ፍልስጤማዊያን) የእንግሊዝ ወታደሮች ቀምተው ለፅዮናዊያን የሰጡት መሬት ነበር፡፡

ይህ ጉብኝት ታላቅ ተቃውሞን (አመፅ) አስከተለ ፤ ታላቅ አድማን ፍልስጤም በባልፎር ላይ አወጀች፡፡ ይህንን የተመለከቱ ወታደሮች ወደ ቤይሩት (ሊባኖስ) ከዛም በመርከብ ተሳፍሮ ወደ ሃገሩ እግሬ አውጪኝ እንዲል አደረጉት፡፡

በመጀመሪያዎቹ 10 አመታት ብቻ 76400 አይሁዳዊያን (አብዛኞቹ ከምስራቅ አውሮፓ) ወደ ፍልስጤም እንደገቡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የቁጥሩ ማሻቀብ ስጋት የገባቸው ፍልስጤማዊያን የፅዮናውያንን እንቅስቃሴ በቻሉት ሁሉ ለማስቆም መታገል እንዳለባቸው አሰቡ፡፡

ይህ በንዲህ እንዳለ በሴፕቴምበር 1928 የተፈጠረው የአል-ቡራቅ ክስተት በሁለቱ ጎራዎች መካከል ሰላማዊ አየር ሊነፍስ እንደማይችል ያመላከተ ፍንጭ ነበር፡፡

አይሁዳዊያን የእኛ ብቻ የሆነውን የአል-ቁድስ መስጂድ ምዕራባዊ ግድግዳ ላይ እጃቸውን ለማሳረፍ ሙከራ አደረጉ፡፡ ይህ ነው ደም አፋሳሽ ክስተቶች የያዘውን የቡራቅ አብዮት እንዲፈነዳ ምክንያት የሆነው፡፡ ከዚህ በኋላ ፍልስጤማዊያን በ አል-ኸሊል (ሄብሮን)፣ናቡለስ፣ባይሳን እና ሳፋድ ውስጥ የሰፈሩ አይሁዳዊያን ላይ ጥቃት አደረሱ፡፡

በአፀፋው የእንግሊዝ ወታደሮች ከአይሁዶች ጋር በመሆን ወደ ግብፅ የጦር ሃይል እርዳታን በጠየቁት ላይ እርምጃ ወሰዱ ፡፡ የእግረኛ ጦራቸውን፣ግዙፍ የጦር መርከባቸውን እና የአየር ሃይላቸውን በመጠቀም አመፁን ለማፈን ጥረት ሲያደርጉ ዴር ያሲን እና ሊፍታን የመሳሰሉ መኖሪያ ቦታዎች ፈራረሱ፡፡

ፍልስጤም ትኩሳት ያዛት ፤ እዚም እዛም ፀብ፣ብጥብጥ፣እልቂት ሆነ፡፡ በዚህም ከአንድ ሺህ በላይ (አብዛኞቹ አረቦች ነበሩ) ሰዎች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ 26ቱ የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው (25ቱ አረቦች ነበሩ)፡፡

በ1930 የፈላሾች ቁጥር 104750 ከዛም በቀጣይ 6 አመታት 284645 (ሳይመዘገቡ እና በህገወጥ መንገድ የገቡ ሳይቆጠር) ደርሶ ነበር፡፡

ክፍል 4 ይቀጥላል…ኢንሻአሏህ

Send as a message
Share on my page
Share in the group