#የዘካ_ግዴታነት፣ #ልቅናውና_ከርሱ_ጋር #ተያያዥነት_ያላቸው_ነገሮች
#ክፍል_2
#ሐዲሥ 216 / 1207
ጦልሐት ኢብኑ ዑበይዱላህ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፤ አንድ ሰው ከአላህ መልዕክተኛ ዘንድ መጣ። የነድጅ ሰው ነው። ጸጉሩ ተንጨብርሯል። የሚስገመገም ድምጽ እንሰማዋለን። የሚናገረው ግን አይገባንም። ወደ አላህ መልዕክተኛ ቀረበና ስለ ኢስላም ጠየቃቸው። የአላህ መልዕክተኛም “በቀንና በሌሊት አምስት ወቅት ሶላቶች ናቸው” አሉት። “ከዚህ ውጭ ሌላ አለብኝን?” አላቸው። “በፈቃደኝነት የምትሰግዳቸው ካልሆኑ በቀር የለብህም” አሉት። “የረመዷንን ወር መጾም” ሲሉም ነገሩት። “ከርሱ ውጭ ሌላ ጾም አለብኝን?” አላቸው። “በፈቃደኝነት የምትጾመው ካልሆነ በስተቀር የለብህም” አሉት። የአላህ መልዕክተኛ ዘካንም አወሱለት። “ከርሱ ሌላ ምጽዋት አለብኝን?” አላቸው። “በፈቃደኝነት የምትመጸወተው ካልሆነ በቀር የለብህም” አሉት። ሰውየው “ከዚህ ቅንጣት ታክል አልጨምርም፤ አላጎድልም” ብሎ ሔደ። የአላህ መልዕክተኛ “እውነቱን ከሆነ ዳነ” አሉ።
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ የአላህ መልዕክተኛ የማስተማር ስልት። ነገር አለማወሳሰባቸው። ለማንኛውም ሰው በሚገባው መልክ በቀላሉ ማስረዳታቸው። ጸጉር ስንጠቃ ውስጥ አለመግባታቸው። ለኢስላም መሠረቶችና አንኳሮች ቅድሚያ ትኩረት መስጠታቸው።
2/ ከላይ የተወሱት የኢስላም አባይት መሠረቶች ናቸው። ማንኛውም ሰው በትኩረት ሊፈጽማቸው ይገባል። እነርሱን ችላ ማለት እምነትን ያደክማል።
3/ የኢስላምን መሠረታዊ ድርጊቶች ያከናወነ የመዳን ተስፋው ሠፊ ነው። መልዕክተኛው እንዳሉት “እውነቱን ከሆነ ይድናል።”
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1