abu mehdi Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

abu mehdi shared a
Translation is not possible.

ሳቅ ከዑለሞች ጋር። ፈገግታ ሱና ነው።

✍አንድ ሰው ሻዕቢይ ጋር መጣና እንደዚህ ብሎ ጠየቃቸው...

ጠያቂ ፦የሆነችን ልጅ ካገባኋት በኋላ እንደምታነክስ አወኩ... መፍታት እችላለሁ እንዴ?

ሸይኹ፦

ግልብያ ልትወዳደርባት ከሆነ ያገባሀት ፍታት !

..

ሻዕቢይ ተጠየቁ...

ጠያቂ፦ኢህራም ያደረገ ሰዉ (ሃጂ ስነ ስራአት ላይ ያለ ሰዉ) ሰውነቱን ማከክ ይችላልን ?

ሸይኹ፦ አዎ

ጠያቂ፦እስከምን ድረስ ?

ሸይኹ፦ አጥንቱ እስኪታይ ድረስ !

..

አንድ ሰው አቡ ሃኒፋ ዘንድ መጣና ጠየቃችው...

ጠያቂ፦ ገላዬን ለመታጠብ ወንዝ ውስጥ ስገባ ወደ ቂብላ ልዙር ወይስ ወደሌላ?

አቡ ሃኒፋ፦ ልብስህ እንዳይሰረቅ ወደልብስህ ዙር !

..

አንድ ሰው ቃዲ መሀመድ ኢብን ኢስማኢል አል-ኡምራኒን እንደዚህ ብሎ ጠየቃቸው...

ጠያቂ፦ያ ሼኽ! ሚስቴ የማህፀን ማስወገድ ኦፕሬሽን አድርጋ

ነበር እናም አሁን መውለድ ትችላለች?

ሸይኹ፦ ልጄ! ማህፀኗ ከወጣ እንዴት

ብላ ነው የምትወልደው?

ጠያቂዉ፦ አላህ ከፈለገስ?

ሸይኹ፦ አላህ ከፈለገማ አንተም ትወልዳለህ !

..

Send as a message
Share on my page
Share in the group