UMMA TOKEN INVESTOR

abdlaa mehamd shared a
Translation is not possible.

ላንተና @ላንቺ@

#ፊትሽከሚጠቁር

#ርዝቅህከሚጠብ

#ሰውፊትከመዋረድ

“ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡

ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡” (አን-ኑር 24:31)

" ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!" (ኢስራዕ:

Send as a message
Share on my page
Share in the group
abdlaa mehamd shared a
Translation is not possible.

‹‹መህዲ›› በመጨረሻው ዘመን ከደጃልና ዒሳ መምጣት አስቀድሞ የሚነሳ ታላቅ ‹‹ኸሊፋ›› ነው። ‹‹መህዲ›› የማዕረግ ስሙ ሲሆን ‹‹ሁዳ›› ከሚለው ቃል የተገኘና ‹‹የተመራ ቅን ኸሊፋ›› ማለት ነው። መጠሪያ ሙሉ ስሙ ደግሞ ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ አል-መህዲ›› ነው።

ስለ መህዲ በቁርኣን የተነገረ ምንም ነገር አናገኝም። መረጃዎቹ በሙሉ ከሐዲስ የተገኙ ሲሆን ከሃያ በላይ የተረጋገጡ ዘገባዎች ይገኛሉ። ብዙ የሱንና ዑለማዎች ስለ መህዲ የፃፉ ሲሆን ቲርሚዚና አቡ-ዳውድ ራሱን የቻለ ምዕራፍ ሰጥተውታል።

ከሁሉም ታዋቂው ሐዲስ አቡ-ዳውድ የዘገቡት ሲሆን ነቢዩ (ዐሰወ) እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ትንሳኤ ሊቆም አንድ ቀን ቢቀረው እንኳን አላህ ከቤተሰቤ የሆነን፤ ስሙ ከእኔና ከአባቴ ጋር የሚመሳሰል መሪን ሳያስነሳና በበደል የተዋጠችውን ምድር በፍትህ ሳይሞላት አይተዋትም።››

(አቡ-ዳውድ 4282)

ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው መህዲ የነቢዩ (ዐሰወ) ቤተሰብ ነው። ስሙም የነቢዩን (ዐሰወ) እና አባታቸውን የያዘ ሲሆን ‹‹ሙሐመድ ኢብን አብዱላህ›› ወይም ‹‹አህመድ ኢብን አብዱላህ›› ነው። የሚመጣውም ዓለም በዙልም በተዋጠችበት በመጨረሻው ዘመን ሲሆን የአላህን ቃል ከፍ በማድረግ ፍትህን ያነግሳል።

ኡሙ ሰላማ (ረዐ) እንደተናገረችው ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ በፋጡማ በኩል የሚገኝ ቤተሰቤ ነው።›› ብለዋል። ኢብኑል ቀይም ይሄንን ሐዲስ ሲያብራሩ ‹‹መህዲ የሐሰን ዘር ሲሆን አል-ሐሰን ለሙስሊሙ አንድነት ሲሉ ኸሊፋነታቸውን አሳልፈው በመስጠታቸው ምክንያት አላህም በመጨረሻው ዘመን ከቤተሰባቸው ታላቅ ኸሊፋ በማስነሳት ክሷቸዋል።›› ሲሉ ፅፈዋል።

(አቡ-ዳወድ 11/373)

አቡ-ሰዓድ አልኩድሪ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ (ዐሰወ) ስለ መህዲ ገፅታ ሲናገሩ ‹‹ቁመቱ ረጂም፣ ትከሻው ሰፊ፣ አፍንጫው አጠፍ ያለ ነው።›› ብለዋል።

(አቡ-ዳውድ 4265)

መህዲ የሚነሳበትን ቦታ በተመለከተ የተለያዩ ዘገባዎች አሉ። ከፊሎቹ ከሻም ከፊሉ ከኹራሳን ሌላው ደግሞ ከመዲና እንደሆነ ይናገራሉ። ኢብን ከሲር የሁሉንም ሐዲሶች ጥቅል ሀሳብ ሲያስቀምጡ ‹‹የሚነሳው ከምስራቅ ነው። ከዚያም ወደ መካ ይሄዳል። ሰዎችም በከዓባ ዙሪያ ቃልኪዳን ይገቡለታል።›› ብለዋል። እንዲሁም በሌላ መጽሐፋቸው ‹‹በሐዲስ በተጠቀሰው መሰረት ባንዲራው ጥቁር ነው።›› በማለት አብራርተዋል።

(አልቢዳያህ ወልኒያህ 19/63፤ አልፊታን ወልመላሂም 1/49)

ኢማም አህመድ እንደዘገቡት መህዲ መሪነት ሲመረጥ ፍላጎቱም ክህሎቱም አልነበረውም። እናም ‹‹አላህ በአንድ ሌሊት ይመራዋል።›› ብለዋል (ዐሰወ)። ኢብን ከሲር ሐዲሱን ሲያብራሩ፡- ‹‹ይህ ማለት አላህ ይረዳዋል፣ ከዚህ በፊት ያልነበረውን ችሎታም ይሰጠዋል ማለት ነው።›› ብለዋል።

(አህመድ 2/58/ አልፊታን ወልመላሂም 1/29)

መህዲ ኸሊፋነትን ከተረከበ በኋላ ሙስሊም አገራትን በአንድ በማፅናት በቀደመው ኢስላማዊ አስተዳደር ስር ያስገባቸዋል። ከዚያም በቡኻሪ እና ሙስሊም (2897) እንደተዘገበው ከሮማውያን ጋር የመጨረሻው ታላቁ ጦርነት ‹‹አል-መልሃማ አል-ኩብራ›› ይካሄዳል። ሙስሊሞችም ዳቢቅ ላይ ድል ደርጋሉ። ከዚህ በፊት ያልተከፈቱ አገራትንም ይከፍታሉ። ከዚያ በኋላ ሙስሊሞች በየትኛውም ኃይል አይሸነፉም። አላህ አማኞችን ከፍተኛ የሀብት መትረፍረፍ ይባርካቸዋል።

ሸይህ ዑመር ሱለይማን አል-አሽቀር ሐዲሱን መሰረት በማድረግ እንደተናገሩት ‹‹ይህ ጦርነት ከባድ ውድመትን ስለሚያስከትል ዓለም አሁን ካለችው ስልጣኔ ወደኋላ በመመለስ እንደ ጥንቱ በጦር በጋሻ በፈረስ መጠቀም ይጀምራሉ።›› ብለዋል።

(አል-ቂያማህ አስ-ሱግራ 275)

መህዲ ታላቅ ጦርነት አድርጎ ሙስሊሞችን የበላይ ቢያደርግም ጊዜው የቂያማህ ቀን መቃረቢያ በመሆኑ ከባባዶቹ ፊትናዎች ይከሰታሉ። ከእነዚህም መካከል ቀዳሚው የደጃል መነሳት ነው። እሱን ተከትለው የዕጁጅና መዕጁጆች ከጉድጓዳቸው ይወጣሉ። በዚህ ጊዜ አላህ ዒሳን (ዐሰ) ለእርዳታ ይልከዋል።

በሐዲስ እንደተጠቀሰው ዒሳ (ዐሰ) ወደ ምድር የሚወርደው በፈጅር ሰላት ወቅት ነው። ነቢዩ (ዐሰወ) ስናገሩ ‹‹መህዲ ዒሳን አሰግደን ይለዋል። ዒሳም እናንተ መሪዎች መሆናችሁ ከቂያማህ ምልክቱ ነውና አንተ አሰግደን ይለዋል። ዒሳም ከመህዲ ኋላ ተከትሎ ይሰግዳል።›› ብለዋል።

(ሙስሊም 225)

ከዚያ በኋላ ዒሳ ከሙስሊሞች ጋር በመሆን የዕጁጆችንና ደጃልን በመጋደል በአላህ ዕርዳታ ያጠፋቸዋል። ነቢዩ (ዐሰወ) እንደተናገሩት ‹‹ሙስሊሞች ለሰባት ዓመታት ያህል የየዕጁጆችን አጥንት ቀስትና ጋሻ ለማገዶነት ይጠቀሙበታል።

መህዲ በኸሊፋነት የሚቆይባቸው ዓመታት ‹‹ሰባት›› እንደሆኑ አብዛኛዎቹ የሐዲስ ምሁራን ይናገራሉ። ከእነሱ መካከል አንዱ የኢብኑ ማጃህ ሲሆኑ ነቢዩ (ዐሰወ) ‹‹መህዲ ሰባት አጭር ጊዜያትን ይቆያል።›› ማለታቸውን ዘግበዋል።

(ኢብን ማጃህ 4039)

አል-መህዲ እስኪመጣ ሙስሊሙ ጂሐድን በመተው መጠበቅ ይኖርበታል? ለሚለው ጥያቄ ሸይህ ሙሐመድ ሷሊህ አል-ሙነጂድ በፈትዋ ገፃቸው እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹ከጂሐድ መዘንጋት ከከባባድ ወንጀሎች አንዱ ነው። አላህ ያዘዘው ሁሉም የራሱን ግዴታ እንዲሞላ ነው። መህዲ የራሱ ጂሐድ አለው። ይሄም ህዝብ የራሱን ጂሐድ ማድረግ ግዴታው ነው።

#አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡-

وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ كُلُّهُ لِلَّهِ ۚ فَإِنِ انتَهَوْا فَإِنَّ اللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሏቸው፡፡ ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡

[ ሱረቱ አል-አንፋል - 39 ]

Send as a message
Share on my page
Share in the group
abdlaa mehamd shared a
Translation is not possible.

1//ተዉሂድ ማለት ምን ማለት ነዉ??

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

➬ተዉሂድ ማለት አላህን በጌታነቱ በብቸኛ ተመላኪነቱ በስሞቹ እና በባህሪያቱ ብቸኛ ማድረግ ነዉ።

➩አምልኮት (ዒባዳ) ሁሉ ለአላህ ብቻ ማድረግ መላት ነዉ።

2//የተዉሂድ ክፍሎች ስንት ናቸዉ ???

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ተዉሂድ በ3 የሚከፈል ሲሆን እነሱም፦

➢ተወሂደል አር-ሩቡቢያ

➢ተዉሂደል አል-ኡሉሂያ

➢ተዉሂደል አል-አስማኢ ወሲፋት

       ❶.ተዉሂደል አል-ሩቡቢያ

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

➮ይህ የተዉሂድ ክፍል አላህን በስራዎቹ አንድ ማረግ ነዉ።

➲ይህም ማለት መፍጠር ሲሳይም መስጠት ነገሮችንን ማስተናበር መግደል እና ህያዕ ማድረግ በመሳሰሉት ድርጊቶች አላህን ብቸኛ ማረግ ነዉ ።

➬ከአላህ ሌላ ፈጣሪ የለም

አላህ ጀለወአላ ይህንን እንዲህ በማለት ይገልፅልናል ።

<<አላህ የነገሩን ሁሉ ፈጣሪ ነዉ>>

    📚ሱረቱል [አል-ዙመር 62] 

ከአላህ ሌላ ሲሳይ የሚሰጥ የለም።ይህንን በማስመልከት አላህ እንዲህ ብሏል ፦

➣(በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ)።

  

            📚ሱረቱል [ሁድ 6]

➩ከአላህ ሌላ ነገሮችን የሚያስተናብር የለም አላህ ጀለአላህ እንዲህ ብሏል፦

<<ነገርን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያስተናብራል።>>

          📚ሱረቱል{አል-ሰጀዳህ 5}

➬ከአላህ ሌላ ህያዕ ሊያደርግ ወይም ሊገድል የሚችል የለም።

አላህ ጀለአላህ እንዲህ ብሏል፦

➢(ህያዕ ያደርገል ፤ይገድላልም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነዉ)።

            📚ሱረቱል [አል-ሀዲድ 2]

           ❷.ተዉሂደ አል-ኡሉሂያ

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

➬ይህ የተዉሂድ ክፍል አላህን በአምልኮት ብቸኛ ማረግ ነዉ ።

ይህም፦➢በዱዓ

            ➢በፍራቻ

            ➢በመመካት እና

            ➢እርዳታን በመጠየቅ ብቸኛ ማድረግ ነዉ።

➩አላህ እሱን ብቻ መለመን እንዳለብን ሲነግረን እንዲህ ይላል፦(ጌታችሁም አለ! ለምኑኝ እቀበላችሀለሁና)

           📚ሱረቱል [ኻፊር 60]

➢ከአላህ በስተቀር በሌላ አንመካም።አላህ አማኞችን በእርሱ ላይ ብቻ ሊመኩ እንደሚገባ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፦

➩(አማኞች እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ)

📚  ሱረቱል {አል-ማኢዳህ 23}

➬ከአላህ ዉጭ ሌላ ፍጡራን በማይችሉት ጉዳይ እርዳታ ከአላህ ዉጪ ከማንም አይጠየቅም። ይህን በማስመልከት አላህ በሱረቱል [አል-ፋቲሀ] ላይ ደጋግመን የምናነባቸዉ አንቀፆች አዉርዷል።

➢{አንተን ብቻ እናመልካለን ካንተ ብቻ እርዳታ እንጠይቃለን}።

         ❸ተዉሂድ አል-አስማዒ ወሲፋት

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

➬ይህ የተዉሂድ ክፍል ደግሞ በቁርአን እና ትክክል በሆኑ የመለዕክተኛዉ ሀዲሶች ዉስጥ የመጡትን የአላህ ስሞች እና ባህሪያት ከማንም ስሞችና ባህሪያት ጋር

            ➢ ባያመሳስሉ 

            ➢ቃሉን ሳያዛቡ

            ➢ትርጉማቸዉን ሳይለዉጡ(ሳያስተባብሉ) ለአላህ እንደሚገቡ ማመን ማለት ነዉ።

➬የአላህ( ጀለወላህ) ስሞች ብዙ ናቸዉ ፤ በ99 የተገደቡ አይደሉም ።

ከእነሱም መካከል፦

          ➢አል-ረህማን

          ➢አል-ረሂም

          ➢አል-በሲር

          ➢አል-አዚዝ

          ➢አል-ሀኪም.......

ሼር

Send as a message
Share on my page
Share in the group
abdlaa mehamd shared a
Translation is not possible.

#ሸይኽ ኢብን ባዝ ተጠየቁ ፡ ሙቅ ውሃን በምናፈስበት ጊዜ

ቢስሚላህ እንላለንን፣ ይህም ጂን ቦታው ላይ ይኖራል ብሎ

በመፍራት ነው

መልስ፡

"አዎን! ቢስሚላህ ይበል ምን አልባት ቦታው ላይ ጂን ካለ

እንዲነቃ ለማድረግ ነው" ከዛም ሽይኹ እንዲህ አሉ" በርግጥም

በአንድ ወቅት አንድን ሰው ጂን ይዞት በሚቀራበት ቦታ ተገኝቼ

ነበር

#ሩቃ የሚያደርገው ሰው በሰውየው ላይ ለተደበቀው ጂኒ "ለምን

ያዝከው "አለው

#ጂንውም "የሞቀ ውሃ በአንዱ ልጄ ላይ ደፋና ገደለው "አለ

#የሚቀራዉ ሰውዬ ደግሞ "እሱ ልጅህ በቦታው መኖሩን

ስላላወቀ ነው" አለው

#ጂኒው ደግሞ "ለምን ቢስሚላህ አይልም ነበር እንዲያሳውቀው

(እንዲያነቃው)"

#ሽይኽ ዘይድ አል መድኸሊ ረሂምሁሏህ እንዲህ አሉ ፡

"ለማንኛውም የሞቀ ውሃ በፍሳሽ ትቦዎችም ይሁን በመሬት ላይ

አይደፋም ምክኛቱም መሬት በነዋሪዎች የተሞላች ነች

ምናልባትም በጂኖች አለም ወይም በትንንሽ ፍጡሮች ላይ ያርፋል

በዚህም ለበቀል ይነሳሱና ይይዙታል።ስለዚህ አንድ ሰው የሞቀን

ውሃ መድፋት ከፈለገ በቀዝቃዛ ውሃ ቅዝቃዘው የማያስቸግር

እስኪሆን ያብርደውከዛም ከፈለገ የፍሳሽ ትቦዎች ውስጥ ከፈለገ

መሬት ላይ ያፍሠው" ንግግራቸው እዚህ ጋር አለቀ ረሂመሁሏህ.

፟፟=========================

#ጉዳዩ አደገኛ ነው ሙስሊሞች ሆይ ነቃ በሉ ለወንድሞቻችሁ

ለእህቶቻችሁ ለእናቶቻችሁ አድርሱላቸው ስንትና ስንት እህቶች

በዚህ ሰበብ ችግር ውስት ይገባሉ ፓስታ የቀቀሉበትን ውሃ

አውጥተው በመድፋት ስንቱ ተለክፎዋል ስለዚህ አድርሱላቸው!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group