1//ተዉሂድ ማለት ምን ማለት ነዉ??

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

➬ተዉሂድ ማለት አላህን በጌታነቱ በብቸኛ ተመላኪነቱ በስሞቹ እና በባህሪያቱ ብቸኛ ማድረግ ነዉ።

➩አምልኮት (ዒባዳ) ሁሉ ለአላህ ብቻ ማድረግ መላት ነዉ።

2//የተዉሂድ ክፍሎች ስንት ናቸዉ ???

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ተዉሂድ በ3 የሚከፈል ሲሆን እነሱም፦

➢ተወሂደል አር-ሩቡቢያ

➢ተዉሂደል አል-ኡሉሂያ

➢ተዉሂደል አል-አስማኢ ወሲፋት

       ❶.ተዉሂደል አል-ሩቡቢያ

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

➮ይህ የተዉሂድ ክፍል አላህን በስራዎቹ አንድ ማረግ ነዉ።

➲ይህም ማለት መፍጠር ሲሳይም መስጠት ነገሮችንን ማስተናበር መግደል እና ህያዕ ማድረግ በመሳሰሉት ድርጊቶች አላህን ብቸኛ ማረግ ነዉ ።

➬ከአላህ ሌላ ፈጣሪ የለም

አላህ ጀለወአላ ይህንን እንዲህ በማለት ይገልፅልናል ።

<<አላህ የነገሩን ሁሉ ፈጣሪ ነዉ>>

    📚ሱረቱል [አል-ዙመር 62] 

ከአላህ ሌላ ሲሳይ የሚሰጥ የለም።ይህንን በማስመልከት አላህ እንዲህ ብሏል ፦

➣(በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ)።

  

            📚ሱረቱል [ሁድ 6]

➩ከአላህ ሌላ ነገሮችን የሚያስተናብር የለም አላህ ጀለአላህ እንዲህ ብሏል፦

<<ነገርን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያስተናብራል።>>

          📚ሱረቱል{አል-ሰጀዳህ 5}

➬ከአላህ ሌላ ህያዕ ሊያደርግ ወይም ሊገድል የሚችል የለም።

አላህ ጀለአላህ እንዲህ ብሏል፦

➢(ህያዕ ያደርገል ፤ይገድላልም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነዉ)።

            📚ሱረቱል [አል-ሀዲድ 2]

           ❷.ተዉሂደ አል-ኡሉሂያ

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

➬ይህ የተዉሂድ ክፍል አላህን በአምልኮት ብቸኛ ማረግ ነዉ ።

ይህም፦➢በዱዓ

            ➢በፍራቻ

            ➢በመመካት እና

            ➢እርዳታን በመጠየቅ ብቸኛ ማድረግ ነዉ።

➩አላህ እሱን ብቻ መለመን እንዳለብን ሲነግረን እንዲህ ይላል፦(ጌታችሁም አለ! ለምኑኝ እቀበላችሀለሁና)

           📚ሱረቱል [ኻፊር 60]

➢ከአላህ በስተቀር በሌላ አንመካም።አላህ አማኞችን በእርሱ ላይ ብቻ ሊመኩ እንደሚገባ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፦

➩(አማኞች እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩ)

📚  ሱረቱል {አል-ማኢዳህ 23}

➬ከአላህ ዉጭ ሌላ ፍጡራን በማይችሉት ጉዳይ እርዳታ ከአላህ ዉጪ ከማንም አይጠየቅም። ይህን በማስመልከት አላህ በሱረቱል [አል-ፋቲሀ] ላይ ደጋግመን የምናነባቸዉ አንቀፆች አዉርዷል።

➢{አንተን ብቻ እናመልካለን ካንተ ብቻ እርዳታ እንጠይቃለን}።

         ❸ተዉሂድ አል-አስማዒ ወሲፋት

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

➬ይህ የተዉሂድ ክፍል ደግሞ በቁርአን እና ትክክል በሆኑ የመለዕክተኛዉ ሀዲሶች ዉስጥ የመጡትን የአላህ ስሞች እና ባህሪያት ከማንም ስሞችና ባህሪያት ጋር

            ➢ ባያመሳስሉ 

            ➢ቃሉን ሳያዛቡ

            ➢ትርጉማቸዉን ሳይለዉጡ(ሳያስተባብሉ) ለአላህ እንደሚገቡ ማመን ማለት ነዉ።

➬የአላህ( ጀለወላህ) ስሞች ብዙ ናቸዉ ፤ በ99 የተገደቡ አይደሉም ።

ከእነሱም መካከል፦

          ➢አል-ረህማን

          ➢አል-ረሂም

          ➢አል-በሲር

          ➢አል-አዚዝ

          ➢አል-ሀኪም.......

ሼር

Send as a message
Share on my page
Share in the group