Islam Peace Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Islam Peace shared a
7 month Translate
Translation is not possible.

• سُبْحَانَ اللهِ»

• الحَمْدُ للهِ»

• لَا إلَهَ إلَّا اللهُ»

• اللهُ أكْبَرُ»

• سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ»

• سُبْحَانَ اللهِ العَظِيمِ»

• لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ»

• أسْتَغْفِرُ اللهَ وَأتُوبُ إلَيْهِ»

• لَا إلَهَ إلَّا أَنْتَ سُبْحَانَكَ إنِّي كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينَ»

ጌታዬ ሆይ! ይቅር በለን። አንተን በማስታወስ፣ አንተን በማመስገን፣ አንተን ባማረ መልኩ በመገዛትም ላይ አግዘን።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Islam Peace shared a
Translation is not possible.

የፍልሴጤም ህፃናት እውን ፍቅር አይገባቸውም?

አለም ሁሉ ፊቱን ያዞረባቸው በምን ወንጀላቸው ይሆን ጀነትን እስኪገቡ ይቺ አለም ከቶ ለነሱ የተሰራች አትመስልም።ለሁሉም ልጆቿ ሰብስባ ስታበላ ስታጫውት ለነሱ ግን የተለየች ነች ባጭሩ መጥፎ እንጀራ እናት ነች ከአፈሯ ተፈጥረው ሲያበቁ እንደሌላው ሰው በላይዋ ላይ እንዲራመዱ ሳትፈቅድላቸው ከአፍላነታቸው ትቀጫቸዋለች።የህይወትን ትርጉሙ በቅጡ ሳይረዱ የሞትን ፅዋ እየቀመሱ ነው።ከህይወት ይልቅ የሞትን መራራነት እያዩ እየተጸዉ ነው።ከመገናኘት ይልቅ የመለያይትን ውርጅብኟን በየለቱ ታስቃኛቸዋለች።ሞተውም ተከብረው እንዳይቀበሩ ይመስል በመኖሪያ ቤታቸው ላይ እያወደመቻቸው ከአፈር በታች ሆነዋል።ስማቸው እንኳ ሳይተወቅ አካላቸው እንዲበታተን የጭካኔን ጥግ ቀምሰዋል።ልክ ሙሽሪኮች "ሙስላ" እንዳደሩጉት አነስ ኢብኑ ነድር ረዲየላሁ ዓንሁ ማንነታቸውን መለየት ዘበት እየሆነ ነው።ህፃናት ቦርቀው ተጫውተው የሚያድጉበት ዘመን በፊልስጤም ምድር ካከተመ ሰነበተ ቁስላቸው በረታ ህመማቸው ዳግም አገርሽቶ ከእለታት ግልቢያ ውስጥ እየጎደሉ የዋይታ ሲቃን በፊልስጤም ምድር ቢያሰሙም ደራሽ ጠጋኝ አተው ሲዋትቱ እዚም እዛም ይታያሉ።የሰብአዊነት መለኪያው ከነሱ እየተገፈፈው የእስራኤል መንግስትና ጦርሃይል በፍሊስጤም ሆስፒታል ላይ ሳይቀር የጭካኔ በትራቸውን በማሳረፍ የአረመኔት አረንቋ ውስጥ ሰጥመዋል።በታሪክ መዝገብም የማይረሳ ክፋትን ፈፅመው ዱንያን አጨልሞባቸዋል።ሚስቶች ከባለቤቶቻቸው እየተነጠሉ ነው። ትናንት አብረው የዋሉ በአንድ ቀን ልዩነት ተነጥለው ይቀራሉ።ዋ.....ዋ.... ማንን ይጠሩ ከሰማዩ ሀይል ውጪ ማንም የለም።ለፍሊስጤሞች ያላቸው ብስራት አላህ በሸሂድነት እንዲቀበላቸው ያለው እድል ነው።ሀቢባችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በርግጥ ሸሂድ መሆንን ወደዋል። በአላህ መንገድ ላይ ብገደል ዳግም ነፍሴ ተመልሳ አሁንም በአላህ መንገድ ብገደል አሁንም ነፍሴ ተመልሳ ዳግም በአላህ መንገድ ብገደል ወደድኩኝ  ብለዋል

አላህ ሆይ በስቃይ ውስጥ ያሉትን ወንድሞቻችን አንተው እዘንላቸው።ያረብ ድሉን ቅርብ አድርገው

#islam #gaza

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Islam Peace shared a
Translation is not possible.

እስራኤል በጋዛ የምድር ውጊያ ለመጀመር የያዘችውን እቅድ አራዘመች

ቴል አቪቭ የእግረኛ ጦር ዘመቻውን ያራዘመችው የአሜሪካ ተጨማሪ ኃይል መካከለኛው ምስራቅ እስከሚደርስ ድረስ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባሻገር ሃማስ ያገታቸውን ሰዎች እንዲለቅና የስብአዊ እርዳታ ጋዛ እንዲደርስ በሚል የምድር ውጊያው እንዲዘገይ የፕሬዝደንት ባይደን አስተዳደር ፍላጎት እንዳለውም ተገልጿል።

የአረብ ሀገራት የተኩስ አቁም እንዲደረግ እያቀረቡት ያለው ጥሪ ግን እስካሁን ሰሚ አላገኘም።

#follow

#share

#follow

#like

#palastine

#freegaza

#free_palastine

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Islam Peace shared a
Translation is not possible.

ስለ ፈለስጢን ምን አዲስ ነገር አለ⁉️

========================

✍ የፈለስጢን (የጋዛ ሙስሊሞች) ጉዳይ በየቀኑ አሳዛኝነቱ ቀጥሏል። በየቀኑ የንጹሐን ህይዎት እየተቀጠፈ ነው፣ በርካታ መሠረት ልማቶች እየወደሙ ነው።

ዛሬ ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት እስካሁን 5087 ሙስሊሞች በጽዮናዊቷ ያላባራ የቦምብ ዝናብ ተገድለዋል፣ ከነዚህ መካከል 2055 የሚሆኑት ህፃናት ሲሆኑ 1119 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። 217ቱ አዛውንቶች ነበሩ። 1500 የሚሆኑት በፍርስራሽ ስር እንደጠፉ ናቸው፤ ከመካከላቸው 800 የሚሆኑት ህፃናት አሉ። እስካሁን ድረስ ጀናዛቸው እንኳ አልተገኘም። 15,273 የሚሆኑት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አጠቃላይ የተፈናቀሉት 1 ሚሊዮን 400 ሺህ አካባቢ ሲሆኑ፤ 685 ሺህ የሚሆኑት ከሌሎች ቤተሰቦቻቸው ጋር ተፈናቅለዋል፣ 565 ሺህ የሚሆኑት ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞችና የእርዳታ ሥራ ኤጀንሲ (UNRWA) ጋር ግንኙነት ወዳላቸው ት/ቤቶች ተፈናቅለዋል፣ 101 ሺህ የሚሆኑት በመስጂዶች፣ በቤተ ክርስቲናትና በህዝባዊ ቦታዎች ተጠልለዋል፣ 70 የሚሆኑት በ67 ት/ቤቶች ተፈናቅለው ይገኛሉ።

የተለያዩ ሃገራት መንግስታት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ቢጠይቁም፤ አሜሪካ በጸጥታው ም/ቤት ያላትን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ተጠቅማ የፈለስጢናዊያን ጭፍጨፋ እንዲቀጥል አድርጋለች።

ምን ያክል የፈለስጢን ህፃናትና ሴቶች ተጨፍጭፈው ሲያልቁ እንደምትረካ አይታወቅም።

ሌላውም ዓለም በሰልፍ ድጋፉ እያሳዬ ቢሆንም ከዚያ የዘለለ ማድረግ አልቻለም።

በጋዛ አሁንም ቢሆን የውሃ፣ የመብራት፣ የምግብና የነዳጅ ማዕቀብ እንደተጣለ ነው። ባለፈ ብቻ 20 የሚሆኑ የጭነት መኪኖች ገብተው ነበር። ግን ለ2+ ሚሊዮን ህዝብ ምንም ማለት አይደለም። የጋዛን ሰብዓዊ ቀውስ ለመመከት በየቀኑ መቶ የጭነት መኪኖች መግባት አለባቸው።

አላህ በጥበቡ ከላይ ፈረጃውን አውርዶ ካሉበት በላእ ይገላግላቸው እንጂ እየተካሄደ ያለው ይፋዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ታሪክ የማይረሳው እጅግ አሰቃቂ እልቂት ነው።

ከዱዓእ ውጭ አቅም የለንምና ሁሌም ወንድሞቻችንን እናስታውሳቸው።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group