UMMA TOKEN INVESTOR

Tofik Musema shared a
Translation is not possible.

🟢⚫️🔴🟠 የሐማስ፣ የፍልስጤም ኢስላሚክ ጂሃድ፣ የፍልስጤም ነጻ አውጪ ህዝባዊ ግንባር እና የፍልስጤም ብሄራዊ ተነሳሽነት ንቅናቄ የጋራ መግለጫ፡-

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

የፍልስጤም አስተዳደር ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ሙስጠፋን አዲስ መንግስት እንዲያቋቁሙ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሾመበትን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የፍልስጤም ብሄራዊ የተቃውሞ አንጃዎች የሚከተለውን ያረጋግጣሉ።

1. አሁን ትልቁ ሀገራዊ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አረመኔያዊውን የጽዮናውያን ጥቃት እና በጋዛ ሰርጥ በወገኖቻችን ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት እና የረሃብ ጦርነት መጋፈጥ እንዲሁም በዌስት ባንክ እና የዌስት ባንክ ሰፋሪዎችን ወንጀሎች መጋፈጥ ነው - በተለይም አል ቁድስን አል-አቅሳ መስጂድን ላይ የተጋረጠው ጉልህ ሀገራዊ አደጋ መከላከል ቅድሚያ ይሰጠዋል - ከሁሉም በላይ ግንባር ቀደም የሆነው አደጋ ደግሞ ቀጣይነት ያለው የመፈናቀል አደጋ ነው።

2. ህዝባችንና ሀገራዊ ጉዳያችን ቅድሚያ መሰጠት ባለበት ታሪካዊ ወቅት ላይ የግለሰብ ውሳኔዎችን መወሰን እና አዲስ መንግስት መመስረት አይነት ብሄራዊ መግባባት የሚፈልግ ውሳኔ እና እርምጃዎችን መውሰድ የአንድ ወገንተኝነት ፖሊሲ ማጠናከሪያ ነው ። እንዲሁ አይነት እርምጃዎች ከሁሉም የፍልስጤም ሕዝብ ክፍሎች ተሳትፎ ያለበት ነፃ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በማዘጋጀት መግባባትና አንድነት እንዲሁም አንድ ወጥ የሆነ ብሔራዊ አመራር ማቋቋም የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ናቸው።

3. እነዚህ እርምጃዎች በፍልስጤም አመራር ውስጥ ያለውን ቀውስ ጥልቀት የሚያሳዩ፣ አስተዳደሩ ከእውነታው የራቀ መሆኑን፣ በአስተዳደሩ እና በህዝባችን ስጋቶች እና ፍላጎቶች መካከል ያለውን ከፍተኛ ክፍተት ያመለክታሉ። በእነዚህ ፖሊሲዎች እና አቅጣጫዎች ላይ እምነት ማጣታቸውን አብዛኛው ህዝባችን እየገለፀ ነው።

4. ከተመሳሳይ የፖለቲካ ስርዓት እና የፓርቲዎች አከባቢ አንዱን መንግስት በሌላ ወይም አንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር በሌላ መተካት የህዝባችን መብት ነው።

የፍልስጤም አስተዳደር የአንድ ወገንተኝነት ፖሊሲን ለማስቀጠል በሚያደርገው ጥረት የፍልስጤም ግንባርን አንድ ለማድረግ እና በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመመከት ሁሉንም ሀገራዊ ጥረቶች ለማጣጣም የሚደረጉ ጥረቶችን ወደ ጎን በመተው የታየውን ጎጂ አካሄድ ውድቅ ማድረጋችን እንገልፃለን።

ህዝባችን እና ህያው ሃይሎቻችን ይህን ሞኝነት ከአሁኑ እና የወደፊት አላማችን እና የህዝባችን ጥቅም ፣መብት እና ብሄራዊ መብቶች ጋር ያለውን ተቃርኖ በጥሞና እነዲያጤኑት እንጠይቃለን። ይህን ያለንበትን ታሪካዊና አንገብጋቢ ጊዜ በመምራት ረገድ ሀገራዊ ጉዳያችንን ባስጠበቀና የህዝባችንን ምኞት በሚያሳካ መልኩ መግባባት ላይ ለመድረስ ሁሉም የሀገሪቱ ሃይሎች እና አንጃዎች በተለይም በፋታህ ንቅናቄ ውስጥ ያሉ ወንድሞች ጠንከር ያለ እና ውጤታማ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ህጋዊ መብታቸውን ተጠቅመው፣ መሬታቸውንና ቅዱስ ቦታቸውን ነፃ አውጥተው ነፃ አገራቸውን በሙሉ ሉዓላዊነት ዋና ከተማዋን አል ቁድስ አድርገው መመስረት እንዲችሉ እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።

እስላማዊ ተቃውሞ ንቅናቄ - ሐማስ

እስላሚክ ጂሃድ ንቅናቄ

ህዝባዊ ግንባር ለፍልስጤም ነፃ አውጪ

የፍልስጤም ብሔራዊ ተነሳሽነት ንቅናቄ

አርብ፡ 5 ረመዳን 1445 ሂ

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ነፃ የህክምና አገልግሎት:-

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 'የግብፅ ኮፕቲክ ሚሽነሪ' ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከአሜሪካን ሀገር በሚመጡ የህክምና ባለሙያዎች ከጥር 27 ጀምሮ እስከ የካቲት 1- 2016 ዓ.ም ድረስ ነፃ የውስጥ ደዌ ህክምና ፣ የህፃናት ህክምና ፣ የጥርስ ህክምና ፣ የልብ ህክምና ፣ የቆዳና አባላዘር ህክምና ፣ የፕላስቲክ ቀዶ-ህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጥ ይሆናል።

በመሆኑም የነፃ ህክምና ማግኘት የምትፈልጉ ታካሚዎች በተጠቀሱት ቀናት በሆስፒታሉ በመገኘት የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

የህክምና ቀናት

- ከሰኞ ጥር 27 ጀምሮ እስከ አርብ የካቲት 1- 2016 ዓ.ም ድረስ!

የህክምና ሰዓት

- ከጠዋቱ 2 : 30 እስከ ምሽቱ 11 : 30!

አድራሻ

- አዲስአበባ ፤ ጉለሌ ክ/ከተማ ፤ ወረዳ 1 ፣ ከሽሮሜዳ ወደ ቁስቋም በሚወስደው መንገድ ላይ ያገኙናል!

ለበለጠ መረጃ

- በነፃ የስልክ መስመራችን 998 ላይ ይደውሉ!

Via: Kidus Petros Hospital

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Tofik Musema shared a
Translation is not possible.

📈ተጨማሪ

የየመን ፕሬዝዳንት እና የየመን ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ማህዲ አል-ማሻት የየመን ሪፐብሊክ ጠላት የሆኑ አካላትን እና ሀገራትን የሚዘረዝር ረቂቅ ህግ ማዘጋጀት ጀመሩ፤ በዝርዝሩ ውስጥ የጽዮናዊው አካል በቀዳሚነት ተቀምጧል።

ይህ የሆነው አሜሪካ አንሰራላህን ‹የአሸባሪዎች ስም ዝርዝር› ተብዬው ውስጥ ከጨመረች ከሰዓታት በኋላ ነው።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Tofik Musema shared a
Translation is not possible.

ሸይኻችንን እናሳክም ዘንድ የቀረበ ጥሪ!

🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑

በዓፋር ክልል በአዉሲረሱ ዞን በዱብቲ ወረዳ ሰላም ጃሚዕ መስጅድ መስራች፣ ኢማም፣ ኻጢብና ሙዓሊም(መምሕር) የሆኑት ሸይኽ ሷሊሕ ሙስጠፋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በልብ ሕመም ምክንያት ከሚወዱት ማሕበረሰብ ተነጥለዉ የቆዩ ሲሆን በአሁን ሰዓት ሕመሙ ጠንቶባቸዉ ወደከፍተኛ የልብ ሕመም ስትሮክ ደረጃ ተሻግሮ ከባቲ ወደ ደሴ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብለዉ  በኢትዮጠቢብ ሆስፒታል ሕክምናቸዉን እየተከታተሉ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ከኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ዶክተሮች በኩል ሸይኹን ለማዳን  የበኩላቸዉን ጥረት እንደሚያደርጉና ነገር ግን ሕመሙ ከበድ ያለ በመሆኑ ለከፍተኛ ሕክምና ራሳቸዉን እንዲያዘጋጁ የሸይኹን ቤተሰብ አሳስቧል። በአሁን ሰአት ሸይኹን ከጎናቸዉ ሆኖ እያስታመመ የሚገኘዉ ብቸኛ ወንድ ልጃቸዉም ቢሆን ለዚህ ሕክምና የሚሆን አቅም የለለዉ በመሆኑ በከፍተኛ ጭንቀትና ሀሳብ ዉስጥ ይገኛል። 

እስከ አሁን ድረስ ባለፈዉ አንድ ወር ሙሉ ለሸይኹ ሕክምና  ወጪ የ400,000ብር የብድር ዕዳ ያለባቸዉ ሲሆን ከዚህ በኋላ ለሚደረገዉ ሕክምና ተገማች 2ሚሊዮን በድምሩ 2.4(ሁለት ሚሊዮን አራመቶ ሺህ ብር) የሚያስፈልግ በመሆኑ ሁሉም ሙስሊም ማሕበረሰብ እንዲሁም ማንኛዉም ሀገርና ወገን ወዳድ የሆነ ሁሉ የሸይኹን ሕይወት ለመታደግ እንረባረብ ዘንድ አደራ ለማለት እንወዳለን።

ከስር የተጠቀሱት  የሸይኹ ልጃቸዉ የባንክ አካዉንት ቁጥሮች ናቸዉ።

ሙሉ ስም: Abdusomed Sualih Mustefa

🛑 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:  1000214014355

📌አቢሲኒያ ባንክ: 80152628

🛑አዋሽ ባንክ: 01304266942800

📌ዘምዘም ባንክ: 0000320820101

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Tofik Musema shared a
Translation is not possible.

ሳራያ አል ቁድስ፡ በጁህር አል-ዲክ አካባቢ የነበሩ የጽዮናውያን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በሞርታር መሳሪያ ደብድበናል፡፡

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group