Translation is not possible.

ሸይኻችንን እናሳክም ዘንድ የቀረበ ጥሪ!

🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑

በዓፋር ክልል በአዉሲረሱ ዞን በዱብቲ ወረዳ ሰላም ጃሚዕ መስጅድ መስራች፣ ኢማም፣ ኻጢብና ሙዓሊም(መምሕር) የሆኑት ሸይኽ ሷሊሕ ሙስጠፋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በልብ ሕመም ምክንያት ከሚወዱት ማሕበረሰብ ተነጥለዉ የቆዩ ሲሆን በአሁን ሰዓት ሕመሙ ጠንቶባቸዉ ወደከፍተኛ የልብ ሕመም ስትሮክ ደረጃ ተሻግሮ ከባቲ ወደ ደሴ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብለዉ  በኢትዮጠቢብ ሆስፒታል ሕክምናቸዉን እየተከታተሉ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ ከኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ዶክተሮች በኩል ሸይኹን ለማዳን  የበኩላቸዉን ጥረት እንደሚያደርጉና ነገር ግን ሕመሙ ከበድ ያለ በመሆኑ ለከፍተኛ ሕክምና ራሳቸዉን እንዲያዘጋጁ የሸይኹን ቤተሰብ አሳስቧል። በአሁን ሰአት ሸይኹን ከጎናቸዉ ሆኖ እያስታመመ የሚገኘዉ ብቸኛ ወንድ ልጃቸዉም ቢሆን ለዚህ ሕክምና የሚሆን አቅም የለለዉ በመሆኑ በከፍተኛ ጭንቀትና ሀሳብ ዉስጥ ይገኛል። 

እስከ አሁን ድረስ ባለፈዉ አንድ ወር ሙሉ ለሸይኹ ሕክምና  ወጪ የ400,000ብር የብድር ዕዳ ያለባቸዉ ሲሆን ከዚህ በኋላ ለሚደረገዉ ሕክምና ተገማች 2ሚሊዮን በድምሩ 2.4(ሁለት ሚሊዮን አራመቶ ሺህ ብር) የሚያስፈልግ በመሆኑ ሁሉም ሙስሊም ማሕበረሰብ እንዲሁም ማንኛዉም ሀገርና ወገን ወዳድ የሆነ ሁሉ የሸይኹን ሕይወት ለመታደግ እንረባረብ ዘንድ አደራ ለማለት እንወዳለን።

ከስር የተጠቀሱት  የሸይኹ ልጃቸዉ የባንክ አካዉንት ቁጥሮች ናቸዉ።

ሙሉ ስም: Abdusomed Sualih Mustefa

🛑 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:  1000214014355

📌አቢሲኒያ ባንክ: 80152628

🛑አዋሽ ባንክ: 01304266942800

📌ዘምዘም ባንክ: 0000320820101

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group