Перевод невозможен

🟢⚫️🔴🟠 የሐማስ፣ የፍልስጤም ኢስላሚክ ጂሃድ፣ የፍልስጤም ነጻ አውጪ ህዝባዊ ግንባር እና የፍልስጤም ብሄራዊ ተነሳሽነት ንቅናቄ የጋራ መግለጫ፡-

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

የፍልስጤም አስተዳደር ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ሙስጠፋን አዲስ መንግስት እንዲያቋቁሙ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሾመበትን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የፍልስጤም ብሄራዊ የተቃውሞ አንጃዎች የሚከተለውን ያረጋግጣሉ።

1. አሁን ትልቁ ሀገራዊ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አረመኔያዊውን የጽዮናውያን ጥቃት እና በጋዛ ሰርጥ በወገኖቻችን ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት እና የረሃብ ጦርነት መጋፈጥ እንዲሁም በዌስት ባንክ እና የዌስት ባንክ ሰፋሪዎችን ወንጀሎች መጋፈጥ ነው - በተለይም አል ቁድስን አል-አቅሳ መስጂድን ላይ የተጋረጠው ጉልህ ሀገራዊ አደጋ መከላከል ቅድሚያ ይሰጠዋል - ከሁሉም በላይ ግንባር ቀደም የሆነው አደጋ ደግሞ ቀጣይነት ያለው የመፈናቀል አደጋ ነው።

2. ህዝባችንና ሀገራዊ ጉዳያችን ቅድሚያ መሰጠት ባለበት ታሪካዊ ወቅት ላይ የግለሰብ ውሳኔዎችን መወሰን እና አዲስ መንግስት መመስረት አይነት ብሄራዊ መግባባት የሚፈልግ ውሳኔ እና እርምጃዎችን መውሰድ የአንድ ወገንተኝነት ፖሊሲ ማጠናከሪያ ነው ። እንዲሁ አይነት እርምጃዎች ከሁሉም የፍልስጤም ሕዝብ ክፍሎች ተሳትፎ ያለበት ነፃ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በማዘጋጀት መግባባትና አንድነት እንዲሁም አንድ ወጥ የሆነ ብሔራዊ አመራር ማቋቋም የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ናቸው።

3. እነዚህ እርምጃዎች በፍልስጤም አመራር ውስጥ ያለውን ቀውስ ጥልቀት የሚያሳዩ፣ አስተዳደሩ ከእውነታው የራቀ መሆኑን፣ በአስተዳደሩ እና በህዝባችን ስጋቶች እና ፍላጎቶች መካከል ያለውን ከፍተኛ ክፍተት ያመለክታሉ። በእነዚህ ፖሊሲዎች እና አቅጣጫዎች ላይ እምነት ማጣታቸውን አብዛኛው ህዝባችን እየገለፀ ነው።

4. ከተመሳሳይ የፖለቲካ ስርዓት እና የፓርቲዎች አከባቢ አንዱን መንግስት በሌላ ወይም አንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር በሌላ መተካት የህዝባችን መብት ነው።

የፍልስጤም አስተዳደር የአንድ ወገንተኝነት ፖሊሲን ለማስቀጠል በሚያደርገው ጥረት የፍልስጤም ግንባርን አንድ ለማድረግ እና በህዝባችን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመመከት ሁሉንም ሀገራዊ ጥረቶች ለማጣጣም የሚደረጉ ጥረቶችን ወደ ጎን በመተው የታየውን ጎጂ አካሄድ ውድቅ ማድረጋችን እንገልፃለን።

ህዝባችን እና ህያው ሃይሎቻችን ይህን ሞኝነት ከአሁኑ እና የወደፊት አላማችን እና የህዝባችን ጥቅም ፣መብት እና ብሄራዊ መብቶች ጋር ያለውን ተቃርኖ በጥሞና እነዲያጤኑት እንጠይቃለን። ይህን ያለንበትን ታሪካዊና አንገብጋቢ ጊዜ በመምራት ረገድ ሀገራዊ ጉዳያችንን ባስጠበቀና የህዝባችንን ምኞት በሚያሳካ መልኩ መግባባት ላይ ለመድረስ ሁሉም የሀገሪቱ ሃይሎች እና አንጃዎች በተለይም በፋታህ ንቅናቄ ውስጥ ያሉ ወንድሞች ጠንከር ያለ እና ውጤታማ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ህጋዊ መብታቸውን ተጠቅመው፣ መሬታቸውንና ቅዱስ ቦታቸውን ነፃ አውጥተው ነፃ አገራቸውን በሙሉ ሉዓላዊነት ዋና ከተማዋን አል ቁድስ አድርገው መመስረት እንዲችሉ እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን።

እስላማዊ ተቃውሞ ንቅናቄ - ሐማስ

እስላሚክ ጂሃድ ንቅናቄ

ህዝባዊ ግንባር ለፍልስጤም ነፃ አውጪ

የፍልስጤም ብሔራዊ ተነሳሽነት ንቅናቄ

አርብ፡ 5 ረመዳን 1445 ሂ

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе