UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ሀመር ተመልሼ ዳዕዋ መስጠት ጀመርኩ 15 ሰዎችን በአንድ ጊዜ ሳሰልም " በአጋንንት እየመረዛቸው ነው ተብዬ ታሰርኩ

ለሳምንት ቆይቼ ከእንግዲህ ዳዕዋ ላለመስጠት አስፈርመው ለቀቁኝ ዳዕዋዬን ግን አላቋረጥኩም ነበር ።

በሌላ ቀን 30 ወጣቶችን አስልሜ በሚስጥር ያዙት አልኳቸው ለምን? የምን መደበቅ ነው እንደውም ጣቢያ እንሂድ ብለው ተያይዘን ሄድን

ዳዕዋ ሰጥቶን እስልምናን ተቀብለን ነው አሉ ሁላችንንም አሰሩን በሳምንቱ ተፈታን እስሩን ለመድኩት ዳዕዋ እየሰጠሁ ካሰለምኩ በኃላ መስገጃዬን ይዤ ጣቢያ በመሄድ አስልሚያለሁ እሰሩኝ ማለት ጀመርኩ ለብዙ ጊዜ ሳሰልም ለሳምንት እየታሰርኩ ስለቀቅ በመጨረሻ ሰለቹኝ በቃ እንዳትመጣ እንደፈለግክ ብለው ለቀቁኝ

በነፃነት ዳዕዋ መስጠት ጀመርኩ.. እናቴ ፣ እህቶቼ ፣ ወንድሞቼን ጨምሮ ብዙ ሰዎች በእጄ እስልምናን ተቀበሉ አልሃምዱሊላህ

ዳግማይ ሀበሻዊው ቢላል

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከአቡበክር ረዐ ደጃፍ ህዝብ ይንጋጋል። አንዳች ግራ ያጋባቸው ጉዳይ እንዳለ ሁኔታቸው ያሳብቃል፦«አንተ የነቢ ምትክ! ሰማይ ዝናብ አቁሟል፣ ምድር ቡቃያዋን አግታለች ህዝብህ ሊያልቅ ነው»

ነቢያቸው ሙቶ የቲም የሆኑትን ህዝቦች አቡበክር በሀዘን እየተመለከታቸው፦«ሂዱ ፤ ትዕግስ አድርጋችሁ ጠብቁ አላህ በዚህ ምሽት መልካም ዜና እንደሚያሰማኝ ተስፋዬን ጥዬበታለሁ»

ህዝብ ይህን ካደመጠ በኋላ በአሚራቸው ተስፋ ጥለው ወደየመጡበት ተበታተኑ። ቀኑ ተጠናቅቆ ሰማዩ ሊጠቁር መቅላት ሲጀምር 1 ሺህ የሚሆኑ ግመሎች የንግድ ሸጠሸቆጦችን እና ቀለቦችን ጭነው መዲና ተከሰቱ።

የመዲና ነዋርያን የንግድ ሸቀጦቹን ሲመለከቱ ተገልብጠው በመውጣት አቀባበል ያደርጉላቸው ጀመር። ግመሎቹም የጫኑትን ሸቀጥ ይዘው ወደ ባለንብረቱ ዑስማን ቤት አቀኑ።

ግመሎች የጫኑትን ጭነት ከዑስማን ቤት እንዳራገፉትም ነጋዴዎች ሸቀጡን ለመረከብ የዑስማንን ቤት ተንጋጉበት።

ዑስማን፦«ምን ፈልጋችሁ ነው?»

ነጋዴዎች፦«ለምን እንደመጣን አንተም ታውቃለህ፤ ህዝቡ ምን ያህል እንደተቸገረ ትረዳለህ»

ዑስማን፦«በምን ያህል ትርፍ ትገዙኛላችሁ?»

ነጋዴዎች፦«ሁለት እጥፍ አድርገን እንገዛሀለን»

ዑስማን፦«አይ ከዚህ በላይ ተሰጥቶኛል»

ነጋዴዎች፦«እሺ 4 እጥፍ እንስጥህ»

ዑስማን፦«ከዚህም በላይ ተሰጥቶኛል»

ነጋዴዎች፦«5 እጥፍ እናድርግልሃ!»

ዑስማን፦«ከዚህም በላይ ተሰጥቶኛል»

ነጋዴዎች፦«በከተማዋ ያለነው ነጋዴዎች እኛው ነን ማንም እኛን አልቀደመንምም፤ ታድያ ማን ነው ከዚህ በላይ የሰጠህ?»

ዑስማን፦«አላህ በእያንዳንዱ ዲርሀም 10 ሀሰናት ሰጥቶኛል። እያንዳንዱን ሀሰናትም በ10 አባዝቶልኛል፤ ከዚህ በላይ ልትሰጡኝ ትችላላችሁ?»

ነጋዴዎች፦«አንችልም»

ዑስማን፦«አላህን ምስክር አድርግያለሁ፤ ግመሎቼ ጭነውት የመጡትን ሸቀጦች በሙሉ ለድሃ ሙስሊሞች በነፃ ለግሼዋለሁ»

ንግግሩን እንዳጠናቀቀም ከግቢው የሚገኘውን ሸቀጥ በሙሉ ለድሆች በማከፋፈል ጀነትን ገዝቶ አደረ። በነቢ ሰዐወ እግር ስር ቁጭ ብለው የታነፁ ከዋክብቶችን የሚያስተናግዱት ጀነቶች ምንኛ ታደሉ!!!

Sefwan

Send as a message
Share on my page
Share in the group
hayder mohammed Сhanged his profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሰውዬው ጥቁር ባርያ ለአገልጋይነት ገዝቶ፦ «ልታገለግዪኝ ነው የገዛሁሽ» ይላታል።

ድምጿን ከፍ አድርጋ ሳቀችበት።

«ያምሻል እንዴ?» አላት፤ በግርምት እያያት።

«የልቦችን ድብቅ ሚስጥር አዋቂ የሆነው ጥራት ይገባው እኔ እብድ አይደለሁም» አለችው።

ንግግሯን ቀጠለች፦ «ከቁርኣን የሀፈዝከው አለ እንዴ?»

«አዎን» አላት።

«እስቲ አሰማኝማ!» አለችው።

«ቢስሚላሂ ረሕማኒ ረሒም» ብሎ ወደ ቁርአኑ ሊገባ ሲል ራሷን ስታ ወደቀች።

ስትነቃም፦ «ያ አላህ ይኼ የዜናህ ጅማሮ እንዲህ ከደፋን፤ የፊትህ እይታ እንዴት ያደርገን ይሆን!!!»

ቀኑ መሸ። ሴቲቱ ከአሳዳሪዋ ጋ ቁጭ ብላ ሳለች ወገቡን ከፍራሹ ሊያሳርፍ አሳዳሪዋ ቢጋደም፦ «አንተዬ! ትንሽ አታፍርም? ጌታህ አይተኛም አንተ ትተኸው ትተኛለህን?»

በግርምት ይመለከታታል፤ መልስ አይሰጣትም። ንግግሯን እንዲህ ስትልም በግጥም አዋዛችለት፦

«አቤት ድንቄም ወዳጅ! እንዴትስ ይተኛል

ሀዘኑን ተኝቶ እሚያርፈው መስሎታል

የኔ ብጤ ልቦች ተነስተው በረዋል

ለፍጥረታት ገዢው እጆችን ነስተዋል

ጌታህን አስደስት መዳንን ከፈለግክ

ሀራም ከመከተል ጎንህን አርቀክ »

ሰምቷት ዝም አለ። የሌሊቱ አጋማሽ አልፎ ከዋክብት ወደ ማደርያዎቻቸው ለመሄድ ሲዘገጃጁ እንስቷ ከጌታዋ እንዲህ ስትል ታወጋ ነበር፦ «ለኔ ባለህ ውዴታ ይሁንብህ እንዳትቀጣኝ እማፀንሃለሁ»

«እሱ እንደሚወድሽ በምን አወቅሽ?» ይላታል አሳዳሪዋ።

«አንተን አስተኝቶ በዚህ ውድቅት ሌሊት እኔን ከፊቱ ያቆመኝ ጌታ አይወደኝም ብለህ ታስባልህ?»

ድሮ ሴቶች ነበሩ፤ አሁንም ሌሊተኛ ሴቶች አሉን!

Sefwan Ahmedin

_________

ምንጭ፦

حلية الأوليآء وطبقات الأصفيآء

Send as a message
Share on my page
Share in the group