Translation is not possible.

ከአቡበክር ረዐ ደጃፍ ህዝብ ይንጋጋል። አንዳች ግራ ያጋባቸው ጉዳይ እንዳለ ሁኔታቸው ያሳብቃል፦«አንተ የነቢ ምትክ! ሰማይ ዝናብ አቁሟል፣ ምድር ቡቃያዋን አግታለች ህዝብህ ሊያልቅ ነው»

ነቢያቸው ሙቶ የቲም የሆኑትን ህዝቦች አቡበክር በሀዘን እየተመለከታቸው፦«ሂዱ ፤ ትዕግስ አድርጋችሁ ጠብቁ አላህ በዚህ ምሽት መልካም ዜና እንደሚያሰማኝ ተስፋዬን ጥዬበታለሁ»

ህዝብ ይህን ካደመጠ በኋላ በአሚራቸው ተስፋ ጥለው ወደየመጡበት ተበታተኑ። ቀኑ ተጠናቅቆ ሰማዩ ሊጠቁር መቅላት ሲጀምር 1 ሺህ የሚሆኑ ግመሎች የንግድ ሸጠሸቆጦችን እና ቀለቦችን ጭነው መዲና ተከሰቱ።

የመዲና ነዋርያን የንግድ ሸቀጦቹን ሲመለከቱ ተገልብጠው በመውጣት አቀባበል ያደርጉላቸው ጀመር። ግመሎቹም የጫኑትን ሸቀጥ ይዘው ወደ ባለንብረቱ ዑስማን ቤት አቀኑ።

ግመሎች የጫኑትን ጭነት ከዑስማን ቤት እንዳራገፉትም ነጋዴዎች ሸቀጡን ለመረከብ የዑስማንን ቤት ተንጋጉበት።

ዑስማን፦«ምን ፈልጋችሁ ነው?»

ነጋዴዎች፦«ለምን እንደመጣን አንተም ታውቃለህ፤ ህዝቡ ምን ያህል እንደተቸገረ ትረዳለህ»

ዑስማን፦«በምን ያህል ትርፍ ትገዙኛላችሁ?»

ነጋዴዎች፦«ሁለት እጥፍ አድርገን እንገዛሀለን»

ዑስማን፦«አይ ከዚህ በላይ ተሰጥቶኛል»

ነጋዴዎች፦«እሺ 4 እጥፍ እንስጥህ»

ዑስማን፦«ከዚህም በላይ ተሰጥቶኛል»

ነጋዴዎች፦«5 እጥፍ እናድርግልሃ!»

ዑስማን፦«ከዚህም በላይ ተሰጥቶኛል»

ነጋዴዎች፦«በከተማዋ ያለነው ነጋዴዎች እኛው ነን ማንም እኛን አልቀደመንምም፤ ታድያ ማን ነው ከዚህ በላይ የሰጠህ?»

ዑስማን፦«አላህ በእያንዳንዱ ዲርሀም 10 ሀሰናት ሰጥቶኛል። እያንዳንዱን ሀሰናትም በ10 አባዝቶልኛል፤ ከዚህ በላይ ልትሰጡኝ ትችላላችሁ?»

ነጋዴዎች፦«አንችልም»

ዑስማን፦«አላህን ምስክር አድርግያለሁ፤ ግመሎቼ ጭነውት የመጡትን ሸቀጦች በሙሉ ለድሃ ሙስሊሞች በነፃ ለግሼዋለሁ»

ንግግሩን እንዳጠናቀቀም ከግቢው የሚገኘውን ሸቀጥ በሙሉ ለድሆች በማከፋፈል ጀነትን ገዝቶ አደረ። በነቢ ሰዐወ እግር ስር ቁጭ ብለው የታነፁ ከዋክብቶችን የሚያስተናግዱት ጀነቶች ምንኛ ታደሉ!!!

Sefwan

Send as a message
Share on my page
Share in the group