Translation is not possible.

ሰውዬው ጥቁር ባርያ ለአገልጋይነት ገዝቶ፦ «ልታገለግዪኝ ነው የገዛሁሽ» ይላታል።

ድምጿን ከፍ አድርጋ ሳቀችበት።

«ያምሻል እንዴ?» አላት፤ በግርምት እያያት።

«የልቦችን ድብቅ ሚስጥር አዋቂ የሆነው ጥራት ይገባው እኔ እብድ አይደለሁም» አለችው።

ንግግሯን ቀጠለች፦ «ከቁርኣን የሀፈዝከው አለ እንዴ?»

«አዎን» አላት።

«እስቲ አሰማኝማ!» አለችው።

«ቢስሚላሂ ረሕማኒ ረሒም» ብሎ ወደ ቁርአኑ ሊገባ ሲል ራሷን ስታ ወደቀች።

ስትነቃም፦ «ያ አላህ ይኼ የዜናህ ጅማሮ እንዲህ ከደፋን፤ የፊትህ እይታ እንዴት ያደርገን ይሆን!!!»

ቀኑ መሸ። ሴቲቱ ከአሳዳሪዋ ጋ ቁጭ ብላ ሳለች ወገቡን ከፍራሹ ሊያሳርፍ አሳዳሪዋ ቢጋደም፦ «አንተዬ! ትንሽ አታፍርም? ጌታህ አይተኛም አንተ ትተኸው ትተኛለህን?»

በግርምት ይመለከታታል፤ መልስ አይሰጣትም። ንግግሯን እንዲህ ስትልም በግጥም አዋዛችለት፦

«አቤት ድንቄም ወዳጅ! እንዴትስ ይተኛል

ሀዘኑን ተኝቶ እሚያርፈው መስሎታል

የኔ ብጤ ልቦች ተነስተው በረዋል

ለፍጥረታት ገዢው እጆችን ነስተዋል

ጌታህን አስደስት መዳንን ከፈለግክ

ሀራም ከመከተል ጎንህን አርቀክ »

ሰምቷት ዝም አለ። የሌሊቱ አጋማሽ አልፎ ከዋክብት ወደ ማደርያዎቻቸው ለመሄድ ሲዘገጃጁ እንስቷ ከጌታዋ እንዲህ ስትል ታወጋ ነበር፦ «ለኔ ባለህ ውዴታ ይሁንብህ እንዳትቀጣኝ እማፀንሃለሁ»

«እሱ እንደሚወድሽ በምን አወቅሽ?» ይላታል አሳዳሪዋ።

«አንተን አስተኝቶ በዚህ ውድቅት ሌሊት እኔን ከፊቱ ያቆመኝ ጌታ አይወደኝም ብለህ ታስባልህ?»

ድሮ ሴቶች ነበሩ፤ አሁንም ሌሊተኛ ሴቶች አሉን!

Sefwan Ahmedin

_________

ምንጭ፦

حلية الأوليآء وطبقات الأصفيآء

Send as a message
Share on my page
Share in the group