UMMA TOKEN INVESTOR

Amrela.meki shared a
6 month Translate
Translation is not possible.

የሰለሃዲን አል አዩቢን ታሪክ መርምሩ ። እስከ 30 አመታት እድሜው ብዙም ሃይማኖተኛ የማይባል ተራ ወጣት ሆኖ አሳልፏል ። አላማው በፈረስ ግልቢያ መወዳደር እና መዝናናት ብቻ ነበር ። በ30 አመት እድሜው ወደ ግብፅ መጣ ። አላማ አልባ ከሆነ ህይወት ወደ ባለ ታላቅ ማንነት እንዴት ሊለወጥ እንደቻለ እየነገርኩህ ነው ። ሕይወቱን የቀየረችው አንድ ቅፅበት ናት ። እንዳልኩህ ግልፅ አላማ አልነበረውም በፈረስ ግልቢያ ችሎታው የሚኩራራ ሰው ነበር ። ግብፅ ላይ አንድ መስቀላዊ አንድን ሙስሊም አዛውንት በጫማው ሲረግጣቸው ተመለከተ ። ይህ ቅፅበት ለእርሱ የለውጥ መነሻ ሆነ ። ከውስጡ የአመፅ ስሜቱን አቀጣጠለ ። ከዚያች እለት ጀምሮ ሙስሊሙን አለም ከመስቀላውያን ነፃ ለማውጣት ፣ በአላህ መንገድ ለመፋለም ቃል ገባ ። ሰለሀዲን የተለወጠው በዚህ መንገድ ነው ። አንዲት ቅፅበት ፍፁም ቀየረችው ። ህይወቱን ሙሉ በአላህ መንገድ ሊፋለም ወሰነ ። ፍልስጥኤምን ነፃ ሳያወጣ ላይለቅ ወሰነ ። « አል አቅሷ መስጅድ ምርኮኛ በሆነበት ሁኔታ እንዴት እስቃለሁ? » ሊሞት ሲል ፈገግ አለ ። በዙርያው የነበሩት ሁሉ ተገረሙ ። « ሰዎች ሊሞቱ ሲሉ ይታወካሉ ፣ ያለቅሳሉ አንተ ግን ትስቃለህ» አሉት ። « አዎ!  ዛሬ እስቃለሁ » አለ ።ለምን? ሲሉት « ከአላህ መልእክተኛ ጋር ተገናኝቼ ፦ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የኢስራእ ጊዜ የረገጡትን የተቀደሰ ቦታ ከወራሪ ሀይል ነፃ አውጥቻለሁ የምልበት ቀን ስለሆነ » ሲል መለሰ ።

የሰለሀዲን ትልቅ ህልም እንዴት እውን ሊሆን እንደቻለ አስተውሉ ። ልክ እንደ ሰለሀዲን ፦ «  ህይወቴን ሙሉ በአላህ መንገድ በሚደረግ ትግል ውስጥ ላሳልፍ ቃል እገባለሁ» በማለት መማል ትችላለህን? ሰለሀዲን ይህችን ቃል ለራሱ ከገባ በኋላ ዘሎ ወደ ጦር ሜዳ አልተዘፈቀም ። ለቀጣዮቹ 15 አመታት ያህል ዝግጅት አድርጓል ።

በጊዚያዊ ስሜትና በፅኑ አላማ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ ። « ፍልስጥኤም ነፃ ለማውጣት ከዛሬ ጀምሮ አስር ጓደኞቼን ሃይማኖተኛ አደርጋለሁ ፣ ከአላህ ጋር ያለኝን ግንኙነት እጠብቃለሁ ፣ በትምህርቴ እጎብዛለሁ ፣ በዙሪያዬ ያሉ ወንድሞቸንም ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ እረዳቸዋለሁ ። » በማለት ወስን ። አንች ደግሞ ፦ « ባልንጀሮቼን ቁርአን ይሀፍዙ ዘንድ እገዛ አደርግላቸዋለሁ» በማለት ወስኝ ። በሰለሀዲን አል አዩቢ ዙርያ ሴቶችን ቁርአን የሚያቀሩና ዲን የሚያስተምሩ አንድ ሺህ ያህል የሴት አሊሞች ነበሩ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Amrela.meki shared a
Translation is not possible.

በፍልስጤሟ ምድር ጋዛ ወራሪዋ ከሰማይ በወረወረችው የድሮን እሳት ቤታቸው ዶግ አመድ ሆኖ በላያቸው ላይ ተናደ። አስራ አንድ ሙሉ ቤተሰብ ከፍርስራሹ መሐል ተጋደመ። በቦታው የደረሱት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ቆፍረውና ቧጠው ሲያወጧቸው ሁሉም ሞተው እናት ነፍሷ ከጀሰዷ ሊላቀቅ የመጨረሻ እስትንፋሷ ላይ ነበረች።

በዝግታ አይኗን እያስለመለመች ታቃስታለች። በሆዷ የታቀፈችው ፅንስ በህይወት ይቆይ ዘንድ እግሯን ከፈት ልጇን ደገፍ አድርጋ ተንጋላለች። ሆስፒታል እንደደረሰች እስትንፋሷ ተቋርጦ ጌታዋን ስትገናኝ ፅንሱ ግን በህይወት ነበር። ዶክተሮች በአላህ ፈቃድ የልጁን ህይወት ማትረፍ ቻሉ። አስራ አንድ ሙሉ ቤተሰቦቹን ባጣበት ቅፅበት እርሱ ይህቺን አለም ተቀላቀለ። መገን የአላህዬ ነገር Mahi Mahisho

Send as a message
Share on my page
Share in the group