7 month Translate
Translation is not possible.

የሰለሃዲን አል አዩቢን ታሪክ መርምሩ ። እስከ 30 አመታት እድሜው ብዙም ሃይማኖተኛ የማይባል ተራ ወጣት ሆኖ አሳልፏል ። አላማው በፈረስ ግልቢያ መወዳደር እና መዝናናት ብቻ ነበር ። በ30 አመት እድሜው ወደ ግብፅ መጣ ። አላማ አልባ ከሆነ ህይወት ወደ ባለ ታላቅ ማንነት እንዴት ሊለወጥ እንደቻለ እየነገርኩህ ነው ። ሕይወቱን የቀየረችው አንድ ቅፅበት ናት ። እንዳልኩህ ግልፅ አላማ አልነበረውም በፈረስ ግልቢያ ችሎታው የሚኩራራ ሰው ነበር ። ግብፅ ላይ አንድ መስቀላዊ አንድን ሙስሊም አዛውንት በጫማው ሲረግጣቸው ተመለከተ ። ይህ ቅፅበት ለእርሱ የለውጥ መነሻ ሆነ ። ከውስጡ የአመፅ ስሜቱን አቀጣጠለ ። ከዚያች እለት ጀምሮ ሙስሊሙን አለም ከመስቀላውያን ነፃ ለማውጣት ፣ በአላህ መንገድ ለመፋለም ቃል ገባ ። ሰለሀዲን የተለወጠው በዚህ መንገድ ነው ። አንዲት ቅፅበት ፍፁም ቀየረችው ። ህይወቱን ሙሉ በአላህ መንገድ ሊፋለም ወሰነ ። ፍልስጥኤምን ነፃ ሳያወጣ ላይለቅ ወሰነ ። « አል አቅሷ መስጅድ ምርኮኛ በሆነበት ሁኔታ እንዴት እስቃለሁ? » ሊሞት ሲል ፈገግ አለ ። በዙርያው የነበሩት ሁሉ ተገረሙ ። « ሰዎች ሊሞቱ ሲሉ ይታወካሉ ፣ ያለቅሳሉ አንተ ግን ትስቃለህ» አሉት ። « አዎ!  ዛሬ እስቃለሁ » አለ ።ለምን? ሲሉት « ከአላህ መልእክተኛ ጋር ተገናኝቼ ፦ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የኢስራእ ጊዜ የረገጡትን የተቀደሰ ቦታ ከወራሪ ሀይል ነፃ አውጥቻለሁ የምልበት ቀን ስለሆነ » ሲል መለሰ ።

የሰለሀዲን ትልቅ ህልም እንዴት እውን ሊሆን እንደቻለ አስተውሉ ። ልክ እንደ ሰለሀዲን ፦ «  ህይወቴን ሙሉ በአላህ መንገድ በሚደረግ ትግል ውስጥ ላሳልፍ ቃል እገባለሁ» በማለት መማል ትችላለህን? ሰለሀዲን ይህችን ቃል ለራሱ ከገባ በኋላ ዘሎ ወደ ጦር ሜዳ አልተዘፈቀም ። ለቀጣዮቹ 15 አመታት ያህል ዝግጅት አድርጓል ።

በጊዚያዊ ስሜትና በፅኑ አላማ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ ። « ፍልስጥኤም ነፃ ለማውጣት ከዛሬ ጀምሮ አስር ጓደኞቼን ሃይማኖተኛ አደርጋለሁ ፣ ከአላህ ጋር ያለኝን ግንኙነት እጠብቃለሁ ፣ በትምህርቴ እጎብዛለሁ ፣ በዙሪያዬ ያሉ ወንድሞቸንም ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ እረዳቸዋለሁ ። » በማለት ወስን ። አንች ደግሞ ፦ « ባልንጀሮቼን ቁርአን ይሀፍዙ ዘንድ እገዛ አደርግላቸዋለሁ» በማለት ወስኝ ። በሰለሀዲን አል አዩቢ ዙርያ ሴቶችን ቁርአን የሚያቀሩና ዲን የሚያስተምሩ አንድ ሺህ ያህል የሴት አሊሞች ነበሩ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group