UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

وَلَا تَزِدِ الظَّالِمِينَ إِلَّا تَبَارًا

«ከሓዲዎችንም ከጥፋት በቀር አትጨምርላቸው፤»

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Nesru Ahmed shared a
Translation is not possible.

እማ ቦምብ ሲመታኝ ወድያው ነው የሚ*ገለኝ ወይስ በጣም እያመመኝ ነው የምሞተው? ስሞትስ ብቻዬን ነው የምሞተው ? አይ ሁላችንም አንድ ላይ ነው የምንሞተው የኔ ልጅ።

...

ጁሪ ተጨዋች ሳቂታ፣ ሁሌም በጩኸቷ ቤት የምታደምቅ ልጅ ነበረች፣ ከወ*ረ*ራው በኃላ ግን ምግብ አትበላም እንደ ድሮ፣ ያ ሁላ ሳቅ ጨዋታ የለም፣ እናቷ የድሮ ትዝታዎችን እያነሳች ለማጫወት ብትሞክርም ጁሪ በትካዜ ከመዋጥ ውጪ ከእናቷ ጋር መቦረቅ መጫወት ካቆመች ሰነባበተች፣ ጦ*ርነቱ ካበቃ በኃላ መጀመርያ እንዳደርግልሽ የምትፈልጊው ነገር ምንድነው ? ተብላ በእናቷ ስትጠየቅ... ምንም ነገር አልፈልግም ፣ ይሄ ቦምብ ብቻ ይቁምልኝ፣ሌላ ምንም አልፈልግም። እሱን ብቻ ነው የምፈልገው ....

...

ወደ ደቡባዊ ስፍራ እንድንሰደድ ትዕዛዝ ቢተላለፍም ወደ ደቡባዊ ጋዛ መሄጃ ጎዳናው ሁሉ አስክሬን ነው (ለስደት የሚወጡ ሰዎች መንገድ ላይ በቦምብ ዒላማ ተደርገው ተገለዋል)፣ አስክሬን ማንሳት ስለተከለከለ ጎዳናው ሁሉ በወዳደቁ አስክሬን የተሞላ ነው። መንገድ ላይ በቦምብ የመመታቱን ዕድል ተቋቁሜ እንኳን ጉዞ ብጀምር ልጄን በነዚህ አስክሬን መሃል ይዤ መራመድ እንዴት ይቻለኛል ? ...

...

ይህ የአልጀዚራ ጋዜጠኛዋ ዩምና አል ሰዒድ እና የልጇ ጁሪ አሁናዊ ተጨባጭ ነው ፣ በህይወት ተርፎ መቆየት ከቻሉ ደሞ ለነገ በራሷ ተሰንዶ ሊቀመጥ የሚችልና በሩዋንዳዋ ኢማኩሌ ኢሊባጊዛ 'ለወሬ ነጋሪ መትረፍ' መፃህፍት ተርታ የሚሰለፍ የዘ*ር ማ*ጥፋት ታሪክ ነው ። ከነ ልጇ አትርፎ ለዛ መብቃቱን ካደላቸው...

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Nesru Ahmed shared a
Translation is not possible.

ከዛሬው ጉባኤ የወጣ የጋራ ስምምነት መግለጫ!

🔴 በጋዛ ሰርጥ ላይ ያለውን የእብደት ጦርነት ለማስቆም ታሪካዊ፣ ልዩ እና ቆራጥ ውሳኔ ወስዷል።

🔴 በጋዛ ሰርጥ ላይ ለ17 አመታት የቆየውን ከበባ ለማንሳት ውሳኔ ሰጥቷል።

🔴 የራፋህ ድንበርን በቋሚነት በመክፈት፣ ለነዳጅ፣ ለእርዳታ እና ለህክምና ቁሳቁሶች ምቹ መተላለፊያ እንዲሆን ተወስኗል።

🔴 የጋዛ ሰርጥ መልሶ ግንባታን የሚያግዝ ፈንድ የጋራ ጥምረት በአስቸኳይ በማቋቋም ከ41 ሺህ በላይ ሙሉ በሙሉ የወደመ መኖሪያ ቤቶችን እንዲሁም ከ222 ሺህ በላይ በከፊል የወደሙ መኖሪያ ቤቶችን የመንግስት መስሪያ ቤቶችን፣ መስጊዶችን፣ ቤተክርስትያኖችን፣ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመገንባት የወሰነ ሲሆን ይህን የፈፀሙ የጦር ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ እና ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች እና ለሚመለከታቸው ፍርድ ቤቶች ለማቅረብ የአረብ እስላማዊ የህግ አካል ለማቋቋም ተወስኗል።

🔴 የወራሪዋ አምባሳደሮች ከአረብ እና ሁሉም እስላማዊ ሀገራት ማባረር ፣የሀገራቸውን አምባሳደሮች በመጥራት እየተፈጸመ ላለው ወንጀል እና እልቂት ምላሽ እና ይህንን ወራሪ ሙሉ በሙሉ ቦይኮት ለማድረግ ተወስኗል።

🔴 ወራሪውን ከፍልስጤም ግዛት ማባረር፣ ወረራውን ማስቆም እና እየሩሳሌም ዋና ከተማዋ በማድረግ የፍልስጤም ሀገርን ለመመስረት ስምምነት ላር ተደርሷል።

የሙሐመድ ትውልድ From Ultra palestine

#palestine

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#gaza genocide

ያለንበት ተጨባጭ!

ሳወድ አረቢያ እና ስፔን!

Look at Our Situation!

saudi vs spain

**

Pic from socal midea

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Nesru Ahmed shared a
Translation is not possible.

አንድ ወጣት ስራ ለመቀጠር ፈለገ በድርጅቱ ውስጥም ትልቅ ቦታ

ለማግኘት ወደ አንድ ድርጅት አቀና ።

ወጣቱ ቃለ መጠይቁን በጥሩ ሁኔታ አለፈ ።ለመጨረሻ ቃለ

መጠይቅ ለማድረግም ከዳይሬክተሩ ጋር ተገናኘ። ዳይሬክተሩ

የመጨረሻውን መጠይቅ ካረገለት በኋላ ...

የወጣቱን የትምህርት፣ችሎታ የሚያሳየውም ሰነድ (ሲቪ)አገላብጦ

ካየ በኋላ በጣም ጥሩ መሆኑን ገለፀ።

ዳይሬክተሩ:- ከአሁን በፊት የተሻለ የትምህርት እድል አግኝተሃል

ሲል ጠየቀው ?

ልጁም:- "አይ" ሲሳ መለሰ

ትምህርትህን እንድትከታተል እና የትምህርት ቤት ክፍያዎችን

ከፍሎ ያስተማረህ አባትህ ነው?

'ወጣቱ :- አዎ.' ብሎ መለሰ።

ዳይሬክተሩ :- አባትህ ምንድነው የሚሰራው?

ወጣቱ:- አባቴ አንጥረኛ ነው"

ዳይሬክተሩ:- ወጣቱ እጆቹን እንዲያሳየው ጠየቀው።

ወጣቱ :- ለስላሳ እና ፍጹም የሆነ እጆቹን አሳየው

ዳይሬክተሩ:- ወላጅ አባትህን በሥራ ረድተሃቸው ታውቃለህ?

ወጣቱ:- በጭራሽ፣ ወላጅ አባቴ መጻሕፍቶችን እንዳነብና

እንዳጠና ነበር ፍላጎቱ ። እና ደግሞ ከኔ በተሻለ ሁኔታ ስራውን

መስራት ይችላል።

ዳይሬክተሩ እንዲህ አለ፡-

ለዛሬ ወደ ቤትህ ትመለሳለህ እቤት እንደደረስክም የአባትህን እጅ

በደንብ አርገህ ታጥብና ነገ ጥዋት ተመልሰህ አግኘኝ ብሎ ቀጠሮ

ያዘለት ።

ወጣቱ ስራውን የማግኘት እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ተሰማው።

ወደ ቤቱ እንደተመለሰም የአባቱን እጅ እንዲያጥብለት አባቱን

ፍቃድ ጠየቀው?

አባቱ በልጁ እንግዳ ተግባር ተገረመ ደስም አለው , ነገር ግን

የደስታ ስሜቱ የተደባለቀ ነበር።

ከዚያም እጆቹን ለልጁ አሳየው. ወጣቱ ቀስ እያለየአባቱን እጆች

አጠበ። ይህን ጊዜ የአባቱ እጆች የተሰነጣጠቁ እና በጣም ብዙ

ጠባሳ እንዳለባቸው አየ ። ይህን ያስተዋለው ለመጀመሪያ ጊዜ

ነበር።

በአባቱ እጆች ላይ አንዳንድ ቁስሎቹ ነበሩ ፣እነዚህ ቁስሎች

በጣም ያሙት ስለነበር ቆዳውን ሲነካቸው ያመው ነበር ።

ወጣቱ እነዚህ እጆች የእርሱ ትምህርት ገንዘብ ለመክፈል በየቀኑ

መሥራት ምን ማለት እንደሆነ ሲያውቅም ይህ የመጀመሪያው

ነው።

የአባቱ እጆች ላይ ያሉት እብጠቶች አባቱ ለእርሱ ትምህርት

መሰረታዊ፣ ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ለወደፊት ህይወቱ

የከፈለው ዋጋ ነው!!!

ወጣቱ የአባቱን እጅ ካጸዳ በኋላ ለጠቂት ያክል በዝምታ ቆመ

።ከዚያም የአባቱን የስራ መስሪያ ቁሳቁሶች ማፅዳት ጀመረ። በዚያ

ምሽት ላይ አባትና ልጅ ለረጅም ሰዓታት ተነጋገሩ፣ አብዛኛውን

የምሽቱን ክፍለ ጊዜ በጨዋታ እና በውግ አሳለፉ ።

በማግስቱ ጠዋት ወጣቱ ወደ ዳይሬክተሩ ቢሮ ሄደ።

ዳይሬክተሩ የወጣቱ አይን እንባ ሲያቀር አስተዋለ ።

ዳይሬክተሩ:- ትናንት ቤትህ ውስጥ ያደረግከውን ሁሉ ልትነግረኝ

ትችላለህ?

ልጁም 'የአባቴን እጅ አጥቤ ስጨርስ የአባቴን የስራ መገልገያ

( አውደ ጥበቡን )አጸዳሁ' ሲል መለሰ።

ዳይሬክተሩ :- ከዚህ ምን ተማርክ ?

ወጣቱ :- ወላጆቼ ባይኖሩ ኖሮ ዛሬ ላይ እኔ

[እኔ እንደማልሆን] ተረዳሁ ።በዚህም አባቴን በመርዳት አንድ ነገር

በራሴ ማድረግ ምን ያህል ከባድ እና ከባድ እንደሆነ አሁን

ተገነዘብኩ። ቤተሰቤን የመርዳትን አስፈላጊነት እና ጥቅም

ተገነዘብኩ አለ ።

ዳይሬክተሩም "በድርጅቴ የምቀጥረው እና በድርጅቴ ውስጥ

እንዲኖር የምፈልገው ይህንን ነው,።እርሱ የሌሎችን እርዳታ

የሚያደንቅ፣በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ለእኛ ሲሉ ብቻ የእነሱ ያልሆኑ

ሌሎች ነገሮችን ለማከናወን ሲሉ የሚደርስባቸውን ችግር እና

ስቃይ የሚያውቅ ሰው መቅጠር እፈልጋለሁ አለ ።

ሁላችንም የራሳችንን ሸክም መሸከም ስንጀምር ለወላጆቻችን

ልፋት ዋጋ መስጠት እንጀምራለን

ወላጆች በእንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅና

ላይ በደረሱ ጊዜ (ኡፍ) አትበላቸው፤ አትገላምጣቸውም።

መልካምን ቃል ተናገራቸው። ከትህትና የመነጨ የእዝነት እና

የርህራሄ ክንፍህን ዝቅ አድርግላቸው። እናም «ጌታዬ ሆይ!

በሕፃንነቴ በርህራሄ እንዳሳደጉኝ ሁሉ ምህረትህን ስጣቸው» በል

ቁርኣን ( 17 : 23 - 24 )

ወላጆችን ሁለቱንም ውደዱ። "ለእናንተ ጉልበታቸውን አጥተዋል::

አላህ ሆይ የሁለተንም ወላጆች ሀቅ የምንጠብቅ አድርገን

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group