UMMA TOKEN INVESTOR

About me

I am happy

Translation is not possible.

ውበትን መጠበቅ በትዳር ውስጥ

           አብላጫ ቁጥር ያላቸው ሴቶች ከትዳር በኋላ  ራሳቸውን ይጥላሉ። አንዳንድ ሴቶች ራሳቸውን በመጠበቅ ረገድ ከኒካህ በፊት የነበራቸው እና ከኒካህ በኋላ የሚኖራቸው ሁኔታ የሠማይና የመሬት ያህል ይለያያል። ይህ ከባድ ስህተት ብዙ ትዳሮችን የጦርነት ቀጠና አድርጓቸዋል። ወጣት ሴቶች ከትዳር በኋላ ከትዳር በፊት ከነበራቸው ልምድ በተሻለ ውበታቸውን ለመጠበቅ እና ለባሎቻቸው ዕይታ በመጉላት ላይ ብርቱ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ትዳር ውበታቸውን ከመጠበቅና ከመንከባከብ ጋር የሚለያዩበት የመሰነባበቻ ድንበር አለመሆኑን መረዳት አለባቸው። እንድያውም ትዳር ከመቼውም ግዜ በበለጠ ውበት የሚጠበቅበት፣ ለትዳር አጋር ራስን ውብ አድርጎ ለማሳየት ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥበት የአዲስ ህይወት መክፈቻ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። በዚህ ጉዳይ ላይ አላህን መፍራትና የባሎቻቸውን ሀቅ መጠበቅ አለባቸው። 

መልካም ሚስት ባልዋ አላህን በማይፈቅደው ፈተና ላይ እንዳይወድቅ ዐቅሟ የቻለውን ሁሉ ታደርጋለች። ዘወትር ራሷን ውብ በማድረግ ዓለሙን ሁሉ ረስቶ ዐይኖቹ በርሷ ላይ ብቻ ያጠሩ እንዲሆኑ ትተጋለች። በባልዋ ዐይን አስቃሚና ራሷን ያልጠበቀች ሆና ከመታየት የበለጠ የሚያስጠላትና የሚያስፈራት ነገር አይኖርም።

ትክክል ነው ባለቤትሽ ውብ ሁነሽ አጠገቡ ስትቀርቢ እርካታን ያገኛል። ደስታ ይሠማዋል። አላህ አንቺን ስለሠጠው አመስጋኝ ይሆናል። ይህ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ግን ውበትሽን በመጠበቅሽ የመጀመሪያው ተጠቃሚ አንቺው ራስሽ ነሽ። ውበትሽን ስትጠብቂ ስለራስሽ ያለሽ ግምት ከፍ ያለ ይሆናል። ጥሩ ይሠማሻል። ዘወትር ውብ ለመሆን መሞከር ውብ ነገር ነው።

ብዙ ሚስቶች ከትዳር ጥቂት ወራት ቆይታ በኋላ ክብደታቸው ይጨምራል። ባል የሠውነት መገጣጠሚያቸው ለመለየት እስኪቸገር ድረስ ያለመጠን ይወፍራሉ። ራሳቸውን ለመጠበቅ የአመጋገብ ስርዓታቸውን ለማስተካከልም ሆነ በኢስላማዊ አዳብ በቤት ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ አይፈቅዱም። በአጭር ግዜ ውስጥ ባል ፍፁም ማየት የማይፈልገውን ገጽታ ይላበሳሉ። ውፍረት ውበትን ከመዋጡም በተጨማሪ ለጤና ችግር ያጋልጣል። ይህን ማወቅና መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ፀጉር የሴት ልጅ ውበት ዋነኛ  መገለጫ ነው። ከትዳር በኋላ ፀጉርሽን ብዙ ግዜ የምትታጠቢበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀርም። ይህም ስለሆነ ለፀጉርሽ የምትሰጪው አንክብካቤ ከትዳር በፊት ከነበረው ሁኔታ በብዙ መጠን መጨመር አለበት። ውሃ የሚነካው ፀጉር ብዙ እንክብካቤ ያስፈልገዋል።

አለባበስ ውበትን ያጎላል። ከባልሽ ጋር በሚኖርሽ ቆይታዎች ሁሉ አቅም በፈቀደ አለባበስሽ ዘናጭና ዓይኖቹን ከአንቺ ላይ የማያስነቅል መሆን አለበት። በቤት ውስጥ ከእርሱ ጋር ካለሽ በፍፁም ያረጁና ቆሻሻ ልብሶችን ከመልበስ ተጠንቀቂ። አዲስና ንፁህ  ልብሶች በባልሽ ፊት ካልለበስሻቸው ትርጉም የላቸውም። በቻልሽው መጠን በየግዜው አለባበስ ስልትሽን ቀያይሪ። አለባበስሽ ዘወትር አዲስ ሠው የሚመለከት ያህል እንዲሠማው የማድረግ ዐቅም ይኑረው።

ጠረን ነፍስን ያናግራል። ትዝታዎችን ይሸከማል። በባልሽ ፊት የሚኖርሽ ጠረን ልብን የሚሠረስር ጣዕም እንዲኖረው ጥረት አድርጊ። ሁልግዜ በጥሩ ሽታ ባልሽን ልትቀርቢው ይገባል። ይህን ለማሳካት በየዕለቱ መታጠብና ሽቶ መታጠን የሚያስፈልግ ከሆነ ከማድረግ ወደ ኋላ አትበይ። ሽቶሽ ግን በፍፁም ተከትሎሽ ከቤት እንዳይወጣ ጥንቃቄ አድርጊ። ውብ ጠረንሽ ማሽተት የሚፈቀድለት በአላህ ቃል የህይወት አጋርሽ የሆነው የባልሽ አፍንጫ ብቻ ነው።

በቤት ውስጥ የሚኖርሽን ጠረን ሁልግዜ ብዙም ሳትቸገሪ ጣፍጭ ሆኖ እንዲቀጥል ወጥ ቤት ስትገቢ የምትለብሺው ተለዋጭ ልብስ ማዘጋጀት ጠቃሚ ይሆናል።

ለህይወት አጋርሽ ውብና ንጹህ ለመሆን የምታደርጊውን ጥረት ሁሉ የአላህን ትዕዛዝ ለመፈጸም እንደምታደርጊው መልካም ስራ አስቢው። በእርግጥም የአላህን ውዴታ የሚያስገኝልሽ መልካም ስራ ነው። በአላህ ፈቃድ ይህ መልካም ስራሽ ጀነትን የሚያወርስሽ ምክንያት ሊሆን ይችላል። የአላህ ቸርነት ሠፊ ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ነብዩላህ ዳውድ በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ሳለ አንዲት ሴት መጣችና

ጌታህ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ ብላ ጠየቀቻቸው?

እኔ አባታቸው የሞተባቸውን ( 3 ) የቲም ልጆችን አሳድጋለሁ። ጉሮሮዋቸውን

የምደፍነውም ጥጥ በመፍተልና በመሸጥ ከማገኘው ገንዘብ ነው።

ዛሬ ግን ጥጤን ፈትዬ በጨርቅ ከረጢት ቋጥሬ ልመሸጥ ወደ ገበያ በመሄድ

ላይ ሳለሁ አንድ አሞራ ልሸጥ የቋጠርኩትን ጥጥ ይዞብኝ በረረ።

አሁን ለልጆቼ ዳቦ መግዣ አጣሁ ልጆቼ በረሀብ እየተንገላቱ ነው ብላ

ንግግሯን ሣትጨርስ..... በሩ ተንኳኳ ፍቃድ ተሠጣቸውና ወደ ውስጥ ገቡ።

በሩን ያንኳኩት 10 ነጋዴዎች ነበሩ። በእጃቸው አንድ ሺህ ዲናር ይዘዋል

ከመሀከላቸው አንዱ መናገር ጀመረ

አንቱ የአላህ ነብይ ሆይ! ባህር ላይ እየተጓዝን ሳለ መርከባችን መስመጥ

ጀመረች ሞታችንን በመጠባበቅ ላይ ሳለን አንድ አሞራ በጨርቅ የተቋጠረ

የጥጥ ፈትል ከላይ ጣለልን በጨርቁም ቀዳዳውን ደፈንን መርከባችንም

ከመስመጥ ይልቅ ወደ ላይ ተንሳፈፈ በአላህ ፍቃድ ከሞት ዳንን አላህ ለዋለልን

ውለታ ምስጋና ይሆን ዘንድ እያንዳዳችን መቶ ዲናር በድምሩ አንድ ሺህ ዲናር

ለመስጠት ቃል ገባን እና ይህው ገንዘባችን ለፈለጉት ሠው ሠደቃ ይሥጡት

በማለት ብሩን እንዲቀበሏቸው እጃቸውን ዘረጉ።

ነብዩላሂ ዳውድም ወደ ሴትየዋ በመዞር << ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ

በየብስና በባህር ይነግድልሻል አንቺ ግን በዳይ ትይዋለሽ በይ ገንዘቡን

ተቀብለሽ ይዘሽ ሂጂ>> በማለት አዘዟት

ሴትየዋም በተናገረችው ቃል እየተፀፀተች ውስጧ በደስታ ተሞልቶ መንገዷን ቀጠለች።

ስንቶቻችን ነን የምንቀበለውን ሳናውቅ ባጣነው ነገር ፈጣሪያችንን

የምናማርረው? መልእክቱን ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶዎ ሼር ያድርጉ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🍒የትዳር ዋነኛ አላማ ይህ ነው ከማግባትህ በፊት መጀመርታ ለምን እንደምታገባ ዋነኛ አላማውን እወቅ🍒🌸

▣አልሼይኽ ሳልህ አልፈውዛን ❴ሀፊዘሁላህ❵ እንዲህ ይላሉ▣

➞▹▹የትዳር ➷ዋነኛ አላማዎች ➷ጥሩ ሷሊህ ልጆችን ➷ማፍራት ነው ስለሆነም ➷አንድ ባል ጥሩ ➷ሷሊህ የሆነችን ሚስት ➷መምረጥ አለበት◃◃◌

➞▹▹የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል ➷ዲን  ያላትን ምረጥ ➷ታርፋለህ  ➷ዲኑን እና ➷ፀባዩን  አኽላቁን ➷የወደዳቹሁለት  ከመጣ ➷ዳሩት ይህን ካላደረጋቹሁ ➷በዱንያ በምድር  ላይ  ➷ፈሳድ ይበዛል ይስፋፋል◃◃◌

➞▹▹አንድ ወንድ ➷እሚታጫት ሴት ➷የዘር ሀረጋን አይመልከት ➷መልኳንም ➷ውበቷን ብቻ አይመልከት ➷ገዘቧንም አይመልከት ነገር ግን  ➷ሷሊህነቷን ዲኗን ➷ይመልከት  ምክንያቱም ➷ሷሊህ ልጆችን ለማፍራት◃◃◌

#ምንጭ

📚((خطبة جمعة بعنوان أسباب صلاح الأولاد 1432هـ.))

በዙ ወንዶች እየተፈተንበት ያለ እርእስ አላህ ከዘነላቸው በስቸቀር

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Seyfedin Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group