የተባረከው የፍልስጤም ምድር
ክፍል 5
✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️
ፍልስጤሞች ከ20ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ህልውናቸውን ሊያስክድ የመጣባቸውን ባዕድ ኃይል በከፍተኛ አልበገር ባይነት የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ በሳዑዲና በግብፅ የሚገኙ አንቱ የተሰኙ ሙፍቲ ዑለማኦች ሳይቀሩ ለምን ምድሩን ጥላችሁላቸው አትሰደዱም የሚል ወኔ ሰላቢ ምክር እየለገሷቸውም እንኳ እጅ አልሰጡም፡፡
የመከላከሉ ጦርነት አጀማመርና ሂደት እንደ አንድ ተጨቋኝ ህዝብ ትግል የተለያዩ መርሐላዎችን አልፏል
በ1918 አንድ የአርበኞች ኮሚቴ የፍልስጤም ሹርጣ አባላትን በማካተት በሕቡዕ ተቋቋመ፡፡ ይህ ኮሚቴ ለዐረብ አብዮት መሠረት በመጣልና በምሥራቅ ኦርዶን በሚኖሩ ዐረቦች ዘንድ የጽዮናዊያንን ሤራ በማጋለጥና ንቃተ-ህሊና በመፍጠር የላቀ ሚና ተጫውቷል፡፡ ኮሚቴው በመሪዎቹና በአስተባባሪዎቹ ላይ በደረሰው እስራትና ማሳደድ የተነሣ ሊዳከም ቢችልም ብሶት እያባባሰው የመጣው የፍልስጤም መነሳሳት ግን እየቀጠለ የጃፋና የቡራቅ አብዮት ን ወለደ፡፡ ምንም እንኳ ባደረጃጀት ያልተሟሉና ግብታዊ የነበሩ ቢሆንም ትግሉን በማቀጣጠልና የጽዮናዊያን መሠሪ እቅድ ባንዴ ፍጻሜ እንዳያገኝ በማጓተት የጎላ ድርሻ ነበራቸው፡፡
የፍልስጤም ታጋዮች ተጨማሪ ኃይል ማደራጀት ቀጠሉ፡፡ ከነዚህ መሀል በኢዘዲን አልቀሳም የተደራጀው በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ ኢዘዲን አልቀሳም ማነው? እሱ ከሶሪያ ወደ ፍልስጤም በመምጣት የዲን ኡስታዝ ሆኖ የራሱን የትግል እንቅስቃሴ የጀመረ ሰው ነው፡፡ በ1926 አንድ የንቅናቄ ኮሚቴ ውስጥ በአባልነት ይመዘገባል፡፡ በ1928 የንቅናቄውን የሐይፋ ቅርንጫፍ ይመሰርታል፡፡ ቀጥሎም የዚሁ ቅርንጫፍ መሪ ይሆናል፡፡ በ1930 የንቅናቄው የአስተዳደር ኮሚቴ አባል በመሆን የመሪነቱን ቦታ ይጨብጣል፡፡
ከዚህ በኋላ አልቀሳም የመንግሥት ሠራተኛ በመምሰል በብዙ የፍልስጥኤም ክልሎች እየተዘዋወረ በአምስት አምስት አባላት የተደራጁ ህዋሳትን በስፋት አዋቀረ፡፡ ኢስላማዊ ህግጋት የትግሉ መመሪያ መሆን እንዳለባቸው አስተማረ፡፡ ብቸኛው የነፃነት መንገድም ጂሃድ ፊ ሠቢሊላህ መሆኑን አሠመረበት፡፡ አፅንዖት አደረገበት፡፡
ይህ በኢዘዲን አልቀሳም የተደረጃ የህቡዕ ንቅናቄ በዐይነቱ ለየት ያለና በዐረብ ፍልስጤሞች የትግል ታሪክ ውስጥ ትልቁ የመስዋዕትነት ንቅናቄ እንደሆነም ይታመናል፡፡ ማዘዣ ቢሮዎቹ ደሃው ህዝብ በሚበዛበት የኢያሪኮ ከተማ ነበር፡፡ በአካባቢው ላይ ሰፊ ተቀባይነት እያገኘ ሲመጣ አደረጃጀቱን አሰፋው፡፡ የደዕዋና የአህዝቦት፣ የወታደራዊ ሥልጠና፣ የአቅርቦት፣ የኤሌክትሮኒክስና የውጭ ግንኙነት አካላትን በመፍጠር አቋሙን ይበልጥ አጠናከረ፡፡
በ1935 ኢዘዲን አልቀሳም የአብዮቱን መጀመር ይፋ አደረገ፡፡ ይህም የሆነው ሠላማዊ መፍትሄ የማፈላለጉ ጥረት ለተደጋጋሚ ጊዜ ተሞክሮ ያለውጤት መቅረቱ እውን ከሆነ በኋላ ነው፡፡ የአብዮቱን መጀመር ተከትሎ በቀሳም ታጣቂዎችና በእንግሊዝ ጦር መካከል ተከታታይ ግጭቶች ተካሄዱ፡፡ ብዙ ፍልሚያዎች ተደረጉ፡፡ ኋላ አልቀሳም ማፈግፈግ ግድ ሆነበት፡፡ ከተወሰኑ የጦር ጓዶቹ ጋር አንድ ቦታ ላይ ከበባ ተደረገበት፡፡ እጁን በሰላም እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ አልፈቀደም፡፡ በተከተለው የተኩስ ልውውጥ ዐቅጣጫዋ በውል ያልተለየ ጥይት አገኘችው፡፡ ተገደለ፡፡ በተቀሩት ጓዶቹና በእንግሊዝ ጦር መካከል የከረረ ውጊያ ተካሂዶ የሞቱት ሞተው የተቀሩት ጠላት እጅ ወደቁ፡፡
ይቀጥላል……
መረጃው ሌሎች ጋር እንድደርስ ሸር ማድረጋችሁን አትርሱ።
💯ተጨማሪ መረጃ እንድደርስዎ ቻናላችንን Join በማድረግ ይቀላቀሉ
👇👇👇
ቴሌግራም:–
https://t.me/Brathersmedia
👇👇👇
ኡማ ላይፍ:–
https://ummalife.com/Brathersmedia