የተባረከው የፍልስጤም ምድር
ክፍል 4
✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️
እንግዲህ!
የእንግሊዝና የአይሁድ ጽዮናዊያን ሤራ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ሲውጠነጠን እንደነበረ ግልጽ ነው፡፡ በመሠረቱ የፍልስጤም መከራና ሥቃይ የተጠነሰሰው መላውን ሙስሊም ዓለም በሥሩ ሲያስተዳድር የነበረው የቱርክ ዑስማንያ ኢስላማዊ መንግሥት በምዕራባዊያን እጅ ሲሸነፍና ጨርሶም በ1924 እንዲያበቃለት ሲደረግ ነው፡፡ የውድቀቱ ቀጥተኛ ውጤት ሆነና ባንድ መንግሥት ጥላ ሥር ተማክሎ ይኖር የነበረው ሙስሊሙ ዓለም ዛሬ በሚታየው መልኩ በምዕራባዊያን እቅድና ፍላጎት የተከፋፈለ ጭፍራ ሆነ፡፡ እያንዳንዱ ራሱን ’ነፃ መንግሥት´ እያለ አወጀ፡፡
ምዕራባዊያን ይሄን ነገር እንደምን አሳኩት?
ኢስላማዊውን መንግሥት ለመከፋፈል የተጠቀሙበት ዘዴ የቱርክና የዐረብ ብሔርተኛ ስሜትን በመጫር ነበር፡፡ በኢስላም መለኮታዊ ዓርማ “ላ ኢላሀ ኢልለላህ ሙሐመዱን ረሡሉልላህ” በሚለው ሥር ወንድማማች ሁኖ ባንድ ዱንያዊና ዲናዊ ዓላማና ግብ ተሳስሮ የኖረውን ህዝብ ገዢና ተገዢ አድርገው በመሳል አቃቃሩት፡፡ ቱርኮችን እንደገዢ፡፡ ዐረቦቹን እንደ ተገዢ፡፡ በዚህም ዐረቦች ከቱርክ ነፃ መውጣት አለባችሁ ተባሉ፡፡ እነሱም በየፊናቸው የተነገራቸውን ተቀብለው ዐረብ ብሔረተኝነትን በማራገብ ተጠመዱ፡፡ ያቺ የታሪካቸውና የሃይማኖታቸው ሞገስ የሆነችው ፍልስጤም ክብሯን ስትገፈፍና በባዕዳን ስትመዘበር እነሱ የእንግሊዝ መንግሥት በሰጣቸው የቤት ሥራ ተጠምደው አይሰሙም አይለሙም፡፡
የነቢያት አገር ቤት፣ የኢስራእ ወል ሚዕራጅ ጉዞ መነሻ፣ አቅሷ የኸሊል ምድር፣ የስንት ሙጃሂዶች ደም የፈሰሰባት ቅድስት ሀገር ከሐዲያን ሲያረክሷት ዐረቦች እዚያው ግድም ሆነው አንድ ነገር ማድረግ አልቻሉም፡፡ ክብርና ሞገሳቸው ከነበረው ኢስላማዊ አንድነት ይልቅ እስከዛሬ ተዋራጅ ሆነው ያሉበት ብሔራዊ ልዩነት ይሻለናል በሚል የዘቀጠ እምነት ጎራ ለዩ፡፡ ወደ ፍልስጤም ዞረው ለማየትና ተቃውሞ ለማደራጀት ጊዜ አልነበራቸውም፡፡ ለዘላለም ከክብር ሰገነት የወረዱበት ጎሠኛ ስሜት ዛሬ ወደሚገኙበት የውርደት አዘቅት እያንደረደራቸው ምንም ቢባሉ የሚያዳምጡ አልነበሩም፡፡
ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ግብጽ፣ ሳዑድ ዐረቢያ … ተብለው እንደተለያየ አገር መታወጅን ቀዳሚ አጀንዳ አድርገው መሽቀዳደም ይዘዋል፡፡ ምዕራባዊያን ውጥናቸው በዐረቦች እጅ ሲፈፀም እያዩ ባደባባይ ይስቃሉ፡፡ ዛሂድ ዑለሞች ተደብቀው ያለቅሳሉ፡፡
ፍልስጤም የዐረብ ወገኖቻቸውን እገዛ በመሻትም ጭምር አገራቸው የታላቁ ሶሪያ (ቢላዱ ሻም) አንድ አካል መሆኗን አበክረው ለማስረዳት ቢሞክሩም ለነሱ የተደገሠላቸው ሌላ ነገር ስለነበረ ሰሚ አላገኙም፡፡ እንደሌሎቹ ሁሉ ለነሱም አገራዊ ነፃነት እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም አልተደመጡም፡፡ እነሱ እስከመኖራቸውም እውቅና ሊሰጣቸው አልተፈለገም፡፡ በነሱ ላይ የአይሁድ አገር ቤት ተመሥርቶ እንደ መንግሥት እንዲታወቅ ነበር የተፈለገው፡፡ “የምን ፍልስጤም ብሎ ሀገር” ሌሎቹ ዐረብ አገራት በመሬታቸው ላይ የአይሁድ ሠፋሪ ሳይኖርባቸው ብሔራዊ ተብዬውን ነፃነት ሲሰጡ ፍልስጤም ግን ባዕድ ሠፋሪም ሠፍሮባት ብሔራዊ ተብዬውን የይስሙላ ነፃነትም ተነፍጋ ህልውናዋን ለማስቀጠል ትታገል ጀመር...
ይቀጥላል……
መረጃው ሌሎች ጋር እንድደርስ ሸር ማድረጋችሁን አትርሱ።
💯ተጨማሪ መረጃ እንድደርስዎ ቻናላችንን Join በማድረግ ይቀላቀሉ
👇👇👇
ቴሌግራም:–
https://t.me/Brathersmedia
👇👇👇
ኡማ ላይፍ:–
https://ummalife.com/Brathersmedia