Abdella Dawud Ali Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

About me

Muslim brother from Ethiopia 🇪🇹 * Information Technology support specialist and linguist in profession * Interested in reading 📚

Translation is not possible.

Assalamu alaykum, brothers and sisters!

Since we have received many Muslims from Ethiopia and other Arabic countries on our social network in recent days, our team has decided to add another language — Amharic. If any of you are translators or those willing to help with translations into the Amharic language, please write to us in a private message at the link: 👉 https://ummalife.com/ummalife.

አሰላሙ አላይኩም፣ እኅቶችና ወንድሞች!

ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ በሶሻል ኔትወርክችን ላይ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች ዓረብ ሀገሮች ብዙ ሙስሊሞችን ስንቀበል፣ ቡድናችን አማርኛ ቋንቋ እንዲጨመር ወስኗል። ከእናንተ መካከል ማንኛውም አስተርጓሚ ወይም በአማርኛ ትርጉም ላይ መረዳት የሚፈልጉ ከሆኑ፣ እባኮትን በሚከተለው ሊንክ በግል መልእክት ይጻፉልን፡

👉 https://ummalife.com/ummalife.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የረመዳን ገፀ በረከት

አንደኛው:- የፆመኛ የአፍ ሽታ ልክ እንደሚስክ ነው

አንድ ሰው ከምግብ ሲርቅ አፉ መጥፎ ጠረን ያመጣል፡፡ ምንም እንኳን ይህ ጠረን ሰዎች ዘንድ የተጠላ ቢሆንም አላህ ዘንድ ግን ከሚስክ ሽታ የተሻለ ጥሩ ሽታ ነው፡፡

ምክንያቱ ደግሞ አላህን በመታዘዝና በማምለክ የመጣ ስለሆነ ነው፡፡ ማንኛውም አላህን በመተዘዝና በማምለክ የመጣ ነገር እሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነው፡፡

አላህ ለሰራው ባለቤት የተሻለንና በላጭን ነገር ይተካዋል፡፡ ስለዚያ በአላህ መንገድ ላይ የአላህ ቃል የበላይ ትሆን ዘንድ ሲዋጋ ስለተገደለ ሰው ሰምተሃልን? የውመል ቂየማ ቁሱሉ ደም እያፈሰሰ ይመጣል፤ መልኩ ልክ እንደደም ነው ጠረኑ ደግሞ እንደሚስክ ነው፡፡

በሐጅ ጊዜ በተመሳሳይ መልኩ አላህ መላኢኮችን አረፋ ላይ ስለቆሙ ሰዎች እንዲ ይላቸዋል “እነኝህን ባሮቼን ተመልከቱ፤ ፀጉራቸው ተንጨባሮና አቧራ ለብሰው ወደ እኔ መጡ፡፡”አህመድና ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል

እዚህ ቦታ ላይ የፀጉር መንጨባረር አላህ ዘንድ ተወዷል፡፡ መነሻው አላህን መታዘዝና ኢህራምን ላለመፍታት እንዲሁም አለባበስን ከማሳመር መጠንቀቅ ስላለባት በመሆኑ ነው፡፡

ሁለተኛው:መላኢካዎች እስከሚያፈጥሩ ድረስ ምህረትን ይጠይቁላቸዋል

መላኢካዎች አላህ ዘንደ የተከበሩ ካዘዛቸው ዝንፍ የማይሉ ከከለከላቸው የማይቀርቡ ብፁአን ፍጡር ናቸው፡፡ ለፆመኞች የሚያደርጉት ዱዓ በአላህ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም፡፡

አላህ ለዚህች ኡማህ መላኢካዎች ዱዓ እንዲያደርጉ መፍቀዱ የኡማዋን ትልቅነት፣ የዝናው ከፍ ማለትም የፆማቸውንም ታላቅ ትሩፋት ይገልፃል፡፡

ምህረት (ኢስቲግፋር) መፈለግ ማለት አንድ ሰው ወንጀል በዱንያ ሆነ በአኺራ ድብቅ እንዲሆንለት ይህችንም ወንጀል አላህ እንዲያልፈው መጠየቅ ማለት ሲሆን ይህ ደገሞ ከምንፈልጋቸውና ከምንመኛቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ በላጩ ነው፡፡ የአደም ልጆች ምንጊዜም ተሳሳቾችና ድንበር አላፊዎት ናቸው በመሆኑም የአላህን ምህረት መከጀል ይገባቸዋል፡፡

ሶስተኛ:-ሰይጣናት በሰንሰለትና እግረ ሙቅ ይታሰራሉ

እስራቱ መልካም የአላህ ባሪያዎችን እንዲያጠሙና ከሐቅ እንዳያዘናጋቸው ያደርጋል፡፡ ይህም የእሳት ባልደረቦች ይሆኑ ዘንድ ጥሪ የሚያደርጉ ጠላቶናቻቸውን በማገት አላህ ባሮችን የገዘበት መንገድ ነው፡፡

በዚህ ወር ላይ የሚታየው ከፍተኛ መልካም ስራን ለመፈፀም የሚደረግ ጉጉትና ከመጥፎ ነገር ለመታቀብ የሚደረገው ጥረት የሰይጣናቱ መታሰር ውጤት ነው፡፡

አራተኛው:-አላህ በየቀኑ ጀነትን ያስውባታል

ባሮቼ የሚያስከፋቸውንና የሚያስጠላቸውን ነገር እርግፍ አድርገው ትተው ወዳንቺ መምጣትን ፈልገዋል፣ ቀርበዋል ይላታል፡፡ አላህ ለመልካም ባሮቹ ለማዘጋጀት ያሰማምራታል በየቀኑ ባሮቹ ለእሷ ያላቸው ጉጉት ይጨምር ዘንድ፡፡

እንዲህም ይላታል ባሮቼ የዱንያ ጣጣን ትተው ሲያንገላታቸውና ሲያደክማቸው ሲያስቸግራቸው የነበረን ነገር ሁሉ በመተው በጐ ነገርን በመስራት ላይ ታጥቀው ተነስተዋል፡፡ ወደ ሰላሟና የክብረ ሀገሯ ጀነት የሚያደርሳቸው፣ የዱንያም የአኺራም ብቸኛ የደስታ ምንጭም ይህ መሆኑን አውቀዋል፡፡

አምስተኛው:-አላህ በዚህ በተባረከ ወር ሌሊቶች በተገቢው ሁኔታ ለሚቆሙ እና ለሚፆሙ ለነብዩ ሙሐመድ ሰዐወ ኡመቶች ምህረትን ይለግሳቸዋል

ይህም ሰዎች ስራቸውን በሚደመድሙበት ጊዜ የሚከፍላቸው ትሩፋት ነው፡፡ ሰራተኞች የስራ ዋጋቸው የሚከፈላቸው ሰራቸውን ሲያጠናቅቁ ነውና፡፡

አላህ ለባሮቹ በሶሰት መልኩ ችሮታውን ይለግሳቸዋል፡፡

አንደኛ

ኃጢአትን ለማሰማር ደረጃን ከፍ ለማድረግ የሚያስችልን መልካም ስራ ባሮች እንዲሰሩ መደንገጉ አንደኛው ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ባይኖር ኖሮ አላህን በዚህ መልኩ ማምለክ ባልቻሉ ነበር፡፡ ኢባዳ በራዕዩ መልክ ከአላህ ወደ መልዕክተኛው ሰዐወ የሚተላለፍ ነው፡፡

ለዚያም ነው ከአላህ ውጭ ሸሪዓን ወይም ስርዓተ ህግን የሚደነግጉ ሰዎችን ያወገዘውና የሽርክ ስራ እንደሆነ የገለፀው፡፡

“ከሃይማኖት አላህ በርሱ ያልፈቀደውን ለርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለነርሱ አሏቸውን?”

ሁለተኛ

ብዙዎች ወደኃላ ያሉበትን መልካም ስራ እንዲሰሩ አላህ ገጠማቸው፡፡ የአላህ እርዳታና መገጠም ባይኖር ኖሮ ለዚህ ባልታደሉ ነበር ችሮታው የአላህ ነውና፡፡

“በመስለማቸው በአንተ ላይ ይመፃደቃሉ፤ በእስልምናችሁ በእኔ ላይ አትመፃደቁ፤ ይልቁንም አላህ ወደእምነት ስለመራችሁ ይመፃደቅባችኃል፤ እውነተኞች ብትሆኑ (መመፃደቅ ለአላህ ነው) በላቸው፡፡”

አል ሑጅራት 17

ሶስተኛ

አላህ ለኸይር ስራዎች ከፍተኛ ምንዳን አዘጋጅቷል፡፡ አንድ ሀሰና በአስር፣ በሰባት መቶ፣ በብዙ እጥፍ ድርብ ተባዝቶ ይሰጠዋል፡፡ ይህ ችሮታ የአላህ ነው፡፡ ምስጋና የተገባው ይሁን፡፡

ወንድሞቼ! የረመዷን መድረስ ትልቅ ፀጋ ነው ሐቁን መወጣት ለቻለና አላህን ከመወንጀል ትዕዛዛቱን ወደመፈፀም፤ ከዝንጋታ አላህን ወደ ማውሳት፤ ከአላህን መራቅ ወደ እሱ መመለስን ምርጫው ላደረገ ሰው እውነትም ታላቅ ፀጋ ነው፡፡

አንተ በረጅብ ወር ወንጀል ያልበቃህ

ከዚያም በሻዕባን የቀጠልህ

አሁን የፆም ወር መጥቶልሃል

እንደለመድከው

የኃጢአት ወር አታድርገው

ቁርአንን አንብብበት

ተስቢህም አድርግበት

ባለፈው የፆም ነበረ ስንትና ስንት

ከቤተሰብ ከወንድሞች ከጐረቤት

ግና ወሰዳቸው አይቀሬው ሞት

ለአንተ ጊዜ ሰጠህ እንድትማርበት

ጌታችን ሆይ ጠልቀን ከገባንበት ዝንጋታ አንቃን፣ ከሞታችን በፊት የተቅዋን ስንቅ ሰንቀን፣ ጊዜያችንን በከንቱ ከማባከን ጠብቀን፣ ለእኛም፣ ለወላጆቻችንም በጥቅሉ ለሁሉም ሙስሊሞች ምህረትን ለግሰን አንተ የአዛኞች አዛኝ ነህና፡፡

ምንጭ፦ መጃሊሱ ሸህሪ ረመዳን መፅሀፍዝፍጅት፦ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል ኡሰይሚንትርጉም፦ ያሲን አሊ

------------*********-------------

© ዝክረ ረመዳን አፕ ሸዕባን 2010

Ibnu Mas'oud Islamic Center

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት

የእነዚህን አሰርት የረመዳን ቀናት በተለይም ለሊቶችን ታላቅ ደረጃ የሚሰጣቸው ስለመሆኑ የተለያዩ ነጥቦችን ማንሳት ቢቻልም ዋና ዋናዎቹን ለመጠቆም፡

የረመዳን ወር ታላቅ ወር መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ ስለታላቅነቱም ብዙ ሳንሰማ ወይም ሳናነብ አልቀረን ይሆናል፡፡ የረመዳን ወር የላቀ ታላቅ ወር እንደመሆኑ ሁሉ ከቀናቶቹና ከለሊቶቹ የመጨረሻዎቹ አስሩ ለየት ያለ ቦታ ሊሰጣቸው የሚገቡ ናቸው፡፡ እነዚህን አሰርት የረመዳን ቀናት በተለይም ለሊቶች ታላቅ ደረጃ ልንሰጠቸው እንደሚገባ የሚያመለክቱ የተወሰኑ ነጥቦችን በአጭሩ ለመጥቀስ እወዳለሁ፡፡

አንደኛ፡- የአላህ መልዕክተኛ በነዚህ አስርት ቀናት እና ለሊቶች የነበራቸው የአምልኮ ሁኔታ የምዕመናን እናት ዓኢሻ (ረዲየላዑ ዓንሀ) እንዲህ ብለዋል፡፡

‹‹የአላህ መልዕክተኛ ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ (በዒባዳ) ላይ ይተጉ ነበር››

ሙስሊም ዘግበውታል

የአላህ መልዕክተኛው የለሊቱ አብዛኛውን ክፍል ከእንቅልፍ በመራቅ ህያው ያደርጉት ነበር፡፡ አሁንም ዓኢሻ (ረዲየላዑ ዓንሀ) እንዲህ ብለዋል፡፡

‹‹ የአላህ መልዕክተኛ ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አሰርት ቀናት ሲገባ ለሊቱን በዒባዳ ላይ በማሳለፍ ህያው ያደርጉ፣ ቤተሰባቸውን ያነቃቁ (ይቀሰቅሱ) ፣ ቀበቷቸውን በማጥበቅ ይተጉ ነበር፡፡››

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

በሐዲሱ ውሰጥ ‹‹ቀበቷቸውን ያጠብቁ ነበር›› በሚል የተጠቀሰውን ቃል በተመለከተ ብዙ የሐዲስ ተንታኞች እንዳሉት ‘‘አሽሙራዊ አገላለፅ ሲሆን ለማለት የተፈለገውም በከፍተኛ ሁኔታ በዒባዳ ከመጠመዳቸው በመነሳት ከሴቶቻቸው ይርቁ ነበር ለማለት ነው’’ ፡፡

ሁለተኛ፡- የእነዚህን አሰርት ቀናት እና ለሊቶች ታላቅነት የሚያሳየን በውስጣቸው ‹‹ለይለተል ቀድር›› የተባለችው ለሊት መኖር ነው፡፡ ይህች ለሊት ከሌሎች የምትለይበት ብዙ መለያዎች ያላት ስትሆን ከነርሱም መካከል፡-

1.ቁርአን የወረደባት ለሊት መሆኗ

2.ከአንደ ሺህ ወራት የምትበልጥ መሆኗ

3.የተባረከች መሆኗ

4.ጅብሪል በመልዕክት በብዛት የሚወርዱባት መሆኗ

5.ሰዎች በከፍተኛ አምልኮ ውሰጥ የሚገቡ ከመሆኑ አንፃር ከእሳት ሰላም ወይም ነፃ የሚወጡባት ለሊት መሆኗ

5.ሰዎች በከፍተኛ አምልኮ ውሰጥ የሚገቡ ከመሆኑ አንፃር ከእሳት ሰላም ወይም ነፃ የሚወጡባት ለሊት መሆኗ

6.በዚህች ለሊት አላህ ምንዳውን እንደሚከፍለው በእርግጠኝነት በማመን እንዲሁም ከይዩልኝ እና መሰል ዱንያዊ ፍላጐቶች ርቆ ሰላትን መስገድ ያበዛ ወንጀሉ የሚታበስ መሆኑ ነው፡፡

ሶስተኛው፡- በእነዚህ አስር ቀናት ኢዕቲካፍ መግባት የመልዕክተኛው ሱና ነው፡፡ ኢዕቲካፍ ማለት እራስን ለአምልኮ ብቻ በመወሰን በመስጂድ መዘውተር ነው፡፡ እናታችን ዓኢሻ እንዲህ ብለዋል፡፡

‹‹ነብዩ እስኪሞቱ ድረስ ከረመዳን የመጨረሻዎቹን አስርት ቀናት እራሳቸውን ለአምልኮ ብቻ በመወሰን በመስጂድ ይዘወትሩ ነበር፡፡››

ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውተል

ከዚህ በመቀጠል ከኢዕቲካፍ ጋር ተያያዥነት ያለውን ይህንን ፈትዋ ወይም ጥያቄና መልስ እንመለከታለን፡፡

ጥያቄ፡- የኢዕቲካፍ መስፈርቶች የትኞቹ ናቸው? ፆም ከመስፈርቶቹ ይካተታልን? አንድ ሰው በኢዕቲካፍ ላይ እያለ በሽተኛን መጠየቅ፣ በግብዣ ቦታ ላይ መገኘት፣ የቤተሰቦቹን ጉዳይ ማስፈፀም፣ አስክሬን መሸኘት ወይም ወደ ስራው መሄድ ይችላልን?

መልስ፡- ሰላተል ጀመዓ በሚሰገድባቸው መስጂዶች ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ የተደነገገ ነው፡፡ ነገር ግን ኢዕቲካፍ የሚያደርገው ግለሰብ ሰላተል ጁምዓ ግዴታ ከሚሆንባቸው ሰዎች መካከል ከሆነና ከኢዕቲካፍ ቀናት መካከል የጁምዓ ቀን ካለ ሰላተልጁምዓ በሚሰገድበት መስጅድ ውስጥ ኢዕቲካፍን ማድረጉ የተሻለ (በላጭ) ነው፡፡

ፆም የኢዕቲካፍ መስፈርት አይደለም፡፡ እንዲሁም በኢዕቲካፍ ላይ ያለ ሰው በዚያ ወቅት በሽተኛን አለመጠየቁ፣ ጥሪ ቢቀርብለት በጥሪ ቦታ ላይ አለመገኘቱ፣ የቤተሰቦቹን ጉዳዬች አለማስፈፀሙ፣ አስክሬን አለመሸኘቱ፣ ከመስጂድ ውጪ ወደ ስራው አለመሄዱ ሱና ነው፡፡ ይህም እናታች ዓኢሻ በትክክለኛ ሰነድ እንዲህ ማለታቸው የተረጋገጠ በመሆኑ ነው፡፡

‹‹በኢዕቲካፍ ላይ ያለ ሰው በሽተኛን አለመጠየቁ፣ የአስክሬን አሸኛኘት ላይ አለመገኘቱ፣ ግንኙነትን አለመፈፀሙም፣ በስሜት ከተቃራኒ ፆታ ጋር አለመተሻሸቱ፣ አስገዳጅ ለሆነ ጉዳይ ቢሆን እንጂ ከኢዕቲካፍ አለመውጣቱ ሱና ነው፡፡››

(አቡዳውድ እና ዳረቁጥኒ ዘግበውታል)

የሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሳሊህ አል-ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ስራዎችን መሰረት ያደረገዝግጅት፡- ኡስታዝ ጣሃ አህመድ

------------*********-------------

© ዝክረ ረመዳን አፕ ሸዕባን 2010

Ibnu Mas'oud Islamic Center

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ምስጋና ለሰው ልጆች ሁሉ በየዘመናቱ ወደ እርሱ ብቸኛ ተመላኪነት እንዲጣሩና በእርሱ ላይ ሌላን አካል ማጋራትን እንዲያስጠነቅቁ መልእክተኞችን ለላከው አምላክ አላህ ተገባው፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ በተወዳጁ ነብያችን በባልደረቦቻቸው እንዲሁም የእርሳቸውን ፈለግ በመልካም በተከተሉ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

እንደሚታወቀው እያንዳንዱ ሙስሊም ሊያውቀውና ሊገነዘበው ከሚገባ ወሳኝ ቁም ነገሮች መካከል ዋነኛው የተፈጠረበትን አላማ ነው። አላህ የሰው ልጆችን ፈጥሮ እንዲሁ በልቅ ለዛዛታና ጨዋታ አልተወም። ይልቁኑ ለታላቅ አላማና ግብ በየጊዜው መልዕክተኞችን እየላከ ወደ ተፈጠሩበት እርሱን በብቸኝነት ማምለክ ተውሒድ ይጠራ ፣ በአምልኮ ላይ በእርሱ ላይ ሌላን ከማጋራት ሽርክ ያስጠነቅቅ ነበር። ከመጀመሪያው ረሱል ኑሕ ጀምሮ እስከ ነብያት መደምደሚያና የሰው ልጆች አለቃ የሆኑት ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ድረስ ሁሉም ነቢያት አንግበው የተላኩት ዋና አላማ ይህ ነበር፡፡

وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِى كُلِّ أُمَّةٍۢ رَّسُولًا أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلطَّـٰغُوتَ “በየህዝቡም ሁሉ ዉስጥ አላህን አምልኩ ጣዖታትንም ራቁ በማለት መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል (ነሕል :36)

ተወዳጁ አርዓያችንና ነብያችን (ﷺ) ወደ ተውሒድ ለ23 አመታት ተጣሩ። በተለይም ደግሞ በመጀመሪያዎቹ የነብይነት 10 አመታት በዋነኝነት እርሱን ሰበኩ። አላህ ብቻ ተነጥሎ እንዲመለክ ጣሩ፤ በዚህም ሳቢያ በመካ ላይ ግፍና በደሉ ሲያይል ወደ መዲና ተሰደዱ። በዚያም ቆይታቸው ተውሒድንና ሌሎች የእስልምና ድንጋጌዎችን አስተማሩ።

ሶሐቦቻቸውን ለዳዕዋ ሲልኩ የሚያስጨብጧቸው ቀዳሚና ዋነኛው ተልዕኮ ተውሒድ ነበር። ኢብኑ አባስ እንዳወሩት ነቢዩ (ﷺ) ሙዐዝን ወደ የመን በላኩት ግዜ እንዲህ አሉት፦

“አንተ የምትሄድባቸው ሰዎች የመጽሀፍ ባለቤቶች ናቸው። መጀመሪያ የምትጠራቸው ወደ “ላኢላሀ ኢለላህ” (ከአላህ ውጪ በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ) መመስከር ይሁን። ይህን ከተቀበሉክ አላህ አምስት ወቅት ሶላት ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው……”[አል ቡኻሪይ (1497) ፣ሙስሊም (19) ፣ አቡ ዳውድ (1587) ፣ቲርሚዚይ (625) ፣ነሳኢይ (2434) ፣ኢብኑ ማጃህ (1783) ፣አሕመድ (1/233) ዘግበውታል።]

አንገብጋቢ ከሆኑ ጉዳዮች ሁሉ ቅድሚያ የሚሰጠው ለዐቂዳ ነው። ምክንያቱም የአንድ ሰው እስልምና መሰረቱ ዐቂዳ ስለሆነ ነው። ዐቂዳው ወይም እምነቱ የተስተካከለ ሰው መላ ስራው ይስተካከላል። መሰረቱ ከተበላሸ ግን ግንቡ ያምራል ተብሎ አይጠበቅም። የሰራውም ስራ ከሽርክ ጋር ከተነካካ ዋጋ የለውም። አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል፡-

وَلَقَدْ أُوحِىَ إِلَيْكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلْخَـٰسِرِينَ“ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሳሪዎች ትሆናለህ በማለት ወደ አንተም ወደ እነዚያም ካንተ በፊት ወደ ነበሩት በእርግጥ ተወርዷል፡፡”(ዙመር:65)

------------*********-------------

ሐይደር ኸድር ዐብደላህ (አቡ ሐማድ)

ረጀብ 13/ 1438

ሚያዝያ 2/ 2009

haiderr02@gmail.com

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሰዎች ከፆም አንፃር

1. ጾም ለአቅመ አዳም (ሄዋን) በደረሰ (በደረሰች) ጤነኛ አእምሮ ባለው መፆም በሚችል እና መንገደኛ ባልሆነ ማንኛውም ሙስሊም ወንድና ሴት ላይ ግዴታ (ዋጂብ) ነው፡፡

2. ሙስሊም ያልሆነ ሰው አይፆምም፡፡ ከሰለመ በኋላም ድሮ ያለፈውን ፆም እንዲከፍልም አይጠየቅም፡፡

3. ለአቅመ አዳም (ሄዋን) ያልደረሰ (ያልደረሰች) ትንሽ ልጅ የመፆም ግዴታ የማይፀናበት ቢሆንም ለማለማመድ እንዲፆም ይታዘዛል፡፡

4. አእምሮውን በሳተ ሰው ፆም ግዴታ አይሆንም በፈታው ቀን ልክ ማካካሻ ምግብ እንዲከፈልለትም አይጠየቅም፡፡ ጥሩና መጥፎውን ለይቶ ማወቅ በማይችል የጃጀ ሽማግሌ እንደዚሁ፡፡

5. በእድሜ መግፋት እና የመዳን ተስፋ በሌለው በሽታ መያዝን በመሳሰሉ ሊወገዱ በማይችሉ ምክንያቶች መፆም ያልቻሉት በያንዳንዱ የፆም ቀን አንድ ደሀ ያበላሉ፡፡

6. ታሞ መዳን የሚቻል በሽታ የታመመ ሰው ግን መፆም ካቃተው ፈቶ ሲድን ፆሞ ይከፍላል፡፡

7. እርጉዝ እና ጡት የምታጠባ ሴት መፆም ከከበዳት ወይም ከፆመች በጸነሰቸው ወይም በምታጠባው ህፃን ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከሰጋች ፆሙን ፈታ ችግሩ ሲወገድላት ፆማ ትከፍላለች፡፡

8. ሴት በወር አበባ ሰሞን ወላድም በመጫትነት ጊዜዋ ውስጥ አይፆም፡፡ በዚህ ጊዜ ያመለጣቸውን ፆም ሌላ ጊዜ ፆመው ይከፍላሉ፡፡

9. ለአደጋ የተጋለጠ የሌሎች ሰዎችን ህይወት(በውሀ ማጥለቅለቅ ወይም በእሳት ምክንያት ለማዳን የተሰማራ ሰው ህይወትን ለማዳን ብሎ ፆሙን ለመግደፍ ከተገደደ ገድፎ ሌላ ጊዜ ፆሞ ይከፍላል፡፡

10. መንገደኛ ሰው(ሙሳፊር) ከፈለገ ይፆማል ካልፈለገም ፈቶ ወደ አገሩ ሲመለስ ይከፍላል፡፡ መንገደኝነቱ እንደ ዑምራ ፀሎት ጉዞ ያለ ጊዜያዊ መንገደኝነት ወይም እንደ ህዝብ ማመላለሻ ሹፌሮች ቋሚ መንገደኝነት ሊሆን ይችላል፡፡ እንደዚህ ያሉት ሰዎች አገራቸው ውስጥ እስካልሆኑ ድረስ ከፈለጉ ፆሙን ፈተው ሲመለሱ ሊከፍሉ ይችላሉ፡፡

ምንጭ፦የሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሳሊህ አል-ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ስራዎችን መሰረት ያደረገ

------------*********-------------

© ዝክረ ረመዳን አፕ ሸዕባን 2010

Ibnu Mas'oud Islamic Center

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ፆምን የማያበላሹ ነገሮች

1. አንድ ሰው ፆመኛ መሆኑን ረስቶ ወይም ተገዶ ወይም ፆም የሚያበላሽ መሆኑን ስለማያውቅ ፆም የሚያፈርስ ነገር ከፈፀመ(ቢበላ፣ቢጠጣ…) ፆሙ አይበላሽም፡፡ ይህም ቀጥሎ በተመለከተው የአላህ ቃል መሰረት ነው፡-

‹‹(በሉ)፡- ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን (አትቅጣን)››

(2፡286)

‹‹ልብ በእምነት የረካ ሆኖ(በክህደት በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር፤…››

(16፡ 106)

‹‹በርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በናንተ ላይ ኃጢያት የለባችሁም ነገርግን ልቦቻችሁ አውቀው በሰሩት ኃጢያት አለባችሁ››

(33፡5)

2.ጾመኛ ሰው ረስቶ ቢበላ ወይም ቢጠጣ ሳያውቅ ዘንግቶ ነውና ጾሙ አይበላሽም፡፡

3.ጸሐይ የጠለቀች መስሎት ወይም ጎህ ያልቀደደ መስሎት ቢበላ ወይም ቢጠጣም ሳያውቅ ነውና ጾሙ አይበላሽም፡፡

4.ሲግሞጠሞጥ ውሀ ከጉሮሮው ቢደርስ ሆን ብሎ ፍልጎ እና በእቅድ እስካላደረገ ድረስ ፆሙ አይበላሽም፡፡

5. በሕልሙ ሩካቤ ስጋ ቢፈፅም በራሱ ምርጫ አይደለም እና ፆሙ አይበላሽም፡፡

ፆም የሚያበላሹ ነገሮች ስምንት ናቸው

1.ሩካቤ ስጋ፡- አንድ የፆም ግዴታ የሚፀናበት ፆመኛ በረመዷን ቀን ወሲባዊ ተራክቦ ከፈጸመ ጾሙን ጹሞ ከመክፈል ጋር ከፍተኛው የመካካሻ ክፍያ(ኩፍፋራ) ይጸናበታል፡፡ ከፍፋራውም አንድን የጫንቃ ተገዥ(ባሪያ) ነጻ ማውጣት ሲሆን ካልተገኘ ሁለት ተከታታይ ወራት መጾም ነው፡፡ ጾሙን ካልቻለ ደግሞ 60 ድሆችን (ሚስኪኖችን) መመገብ ነው፡፡

2.የዘር ፈሳሽ ከእንቅልፍ ውጭ ብልትን በመነካካት ከተቃራኒ ጾታ ጋር በመተሻሸት በመተቃቀፍ በመሳሳምና በመሳሰሉት መንገዶች መፍሰስ፡፡

3.ጠቃሚም ይሁን ጎጂ ነገር እንደ ሲጋራ ያለ ቢሆንም መብላትና መጠጣት ጾም ያስፈታል፡፡

4.በምግብ ፋንታ ሊያገለግል የሚችል የሕክምና መርፌ መወጋት ጾም ያበላሻል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ መርፌ ቀለብ ሆኖ ምግብና መጠጥን መተካት ይችላል፡፡ የምግብነት ባህሪ የሌላቸው የህክምና መርፌዎች በጡንቻዎችም ሆኑ በጅማቶች በኩል ቢወሰዱ ጣዕሙ አፉ ውስጥ ቢሰማውም ባይሰማውም ጾም አይበላሽም፡፡

5.ጾመኛው ለምሳሌ ብዙ ደም ፈሶት ሌላ ደም እንዲሰጠው ካስፈለገ ይህም ጾሙን ያበላሻል፡፡

6.የወር አበባ እና የወሊድ ደም መምጣትም ፆም ያፈርሳል፡፡

7.ደምን በዋግምት እና በመሳሰሉት ከሰውነት ሆን ብሎ እንዲወጣ ማድረግ ፆም ያበላሻል፡፡ ሆን ተብሎ ሳይሆን እንደ ነስር እና ጥርስ ነቀላ በመሳሰሉት ምክንያቶች እንዲሁ የሚወጣ ከሆነ ግን ፆም አይበላሽም፡፡

8.ሆን ብሎ ፈልጎ ማስታወክም ፆም ያበላሻል፡፡ ያለፍላጎት ካስታወከው ግን ፆም አያበላሽም፡፡

የሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሳሊህ አል-ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ስራዎችን መሰረት ያደረገ

------------*********-------------

© ዝክረ ረመዳን አፕ ሸዕባን 2010

Ibnu Mas'oud Islamic Center

Send as a message
Share on my page
Share in the group