UMMA TOKEN INVESTOR

Gobana Hrr shared a
Translation is not possible.

ሙስሊም የቡኻሪ ተማሪ ነው፣

⬇️

ቡኻሪ የኢማሙ አህመድ ተማሪ ነው፣

⬇️

ኢማሙ አህመድ የሻፊዒ ተማሪ ነው፣

⬇️

ሻፊዒ የማሊክ ተማሪ ነው፣

⬇️

ማሊክ የናፊዕ ተማሪ ነው፣

⬇️

ናፊዕ የአዕረጅ ተማሪ ነው፣

⬇️

አዕረጅ የአቡ ሁረይራ ተማሪ ነው፣

⬇️

አቡ ሁረይራ የረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ተማሪ ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

✍ምርጥ_ምክር_ከምርጡ_ነብይ

አንቱ የአላህ መልክተኛ ምከሩኝ አልኳቸው ይላል አቡዘር ረድየሏሁዐንሁ፦

💚የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ አላህን በመፍራት ላይ አደራ ለሁሉም ነገሮችህ ውበት

ይሆንልሀልና ፤

አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ~

💛የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ ቁርአን በማንበብና አላህን በማውሳት ላይ አደራ በሰማይ

እንድትወሳ በምድር ብርሀን ይሆንልሀልና ፤

አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ~

❤️የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ አደራ ዝምታን አብዛ ; ሰይጣንን ማባረሪያ ፣ ለዲንህ

ይረዳሀልና ፤

አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ፤

💚የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ አደራ ሳቅ አታብዛ መሳቅ ልብን ይገድላል ፣ የፊትን ኑር

ይወስዳልና ፤

አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ~

💛የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ እውነትን ተናገር መራራ እንኳን ቢሆን ፤

አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ~

❤️የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ በአላህ ላይ የሰውን ወቀሳ አትፍራ ፤

አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ~

💝የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ የሰዎች ገመና የራስክን ገመና ከማወቅ ( ከመከታተል)

እንዳይከለክልክ ፤

ሶሂሁል ጃሚዕ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ለምን አትሰግድም ወንድሜ?

ለምን አትሰግጂም እህቴ? በዱንያ_ላይ፦

1• እስካልሰግድክ ድረስ ከእድሜህ ላይ በረካ ይነሳል ...

2• እስካልሰገድክ ድረሰ ከፊትህ ላይ ኑር

ይገፈፋል...

3• እስካልሰገድክ ድረስ ምትሰራው ስራ ሁሉ ተቀባይነት የለውም.

4• እስካልሰገድክ ድረስ ዱዓህ ተሰሚነት አያገኝም.

5• እሰካልሰገድክ ድረስ ሌሎች ሚያደርጉልህ ዱዓም አይጠቅምህም. ስትሞት፦

1• እስካለሰገድክ ድረስ እማትረባና የተዋረድክ ሆነህ ትሞታለህ.

2• እስካልሰገድክ ድረስ እንደተራብክ ትሞታለህ.

3• እሰካለሰገድክ ድረስ እንደተጠማህ ትሞታለህ. የባህርን ውሃ እንዳለ ብትጠጣ ጥምህን

አይቆትጥልህም. ቀብር_ውስጥ፦

1• እስካለሰገድክ ድረስ ጎንና ጎንህ እስኪተላልፈ ድረስ ቀብርህን አሏህ ያጠብብሃል.

2• እስካለሰገድክ ድረስ ቀብርህ ውስጥ እሳት ተቀጣጥሎብህ ነጋ ጠባ ትሰቃያለህ.

3• እስካለሰገድክ ድረስ በቀን አምስት ጊዜ ከእባብ ጋር ቀጠሮ ይኖርሃል ! የፈጅርን ሰላት ባለመስገድህ ሲያሰቃይህ ዙሁር ይደረሳል፤የዙሁርን ሰላት ባለመሰገድህ ሲያሰቃይህ አስር ይደርሳል ፤እንደዚህ እያለ ስቃይህ ይቀጥላል (አንድ ጊዜ ምትመታው እሰከ 70 ክንደ ያህለ መሬት ውስጥ ያሰምጠሃል).. የቂያማለት፦

1• እስካለሰገድክ ድረስ ወደ ጀሃነም እሳት . በፊትህ እየተጎተትክ ትወሰዳለህ .

2• እሰካልሰገድክ ድረስ አሏህ ፊት ቆመህ ስትተሳሰብ አሏህ (ሱ,ወ)

በቁጣ አይን ይመለከትህና ፊትህ ላይ ያለ ስጋ ይነሳለ.

3• እስካልሰገድክ ድረስ ከአሏህ (ሱ.ወ) ጋር የምትተሳሰበው ሂሳብ የከፋ ይሆነንና ወደ ጀሃነም እሳት እንደትወረወር ይደረጋል .

ወንድሜ አሁንም አትሰግድም ?? እህቴ አሁንም አትሰግጂም ??

ያአሏህ ይህንን ፁሁፍ ላዘጋጀውም ላነበብነውም ወንጀላችንን ማረን… በሂወት ያሉና የሌሉትንም ወንድምና እህቶቻችንንም ወንጀል ማርልን!!!

#ሼር እናርገው በዚህች ሰበብ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሂዳያ ያገኙና እኛም በጭንቁ የቂያማ ቀን ይጠቅመን ይሆናል፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

→ የትንሹ ዚና አደገኝነት

#የምላስ_ዚና_አደገኛነት

ሁሉም የሰውነት ክፍሎች እያንዳንዱ አዲስ ቀን በመጣ ቁጥር ምላስን ይገስፃሉ፤ ያስጠነቅቁታልም፤ አላህን እንዲፈራ፡፡ ዕጣ ፋንታቸው የሚወሰነው በምላስ ላይ ተመሥርቶ መሆኑን በመግለጽ ምላስ አላህን እንዲፈራ ይገስጹታል፡፡ ↝ይህንኑ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ በማለት ገልጸዋል፡- «በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ሁሉም የአካል ክፍሎች አላህን ፍራ ዕጣ ፋንታችን የሚወሰነው ባንተ ሁኔታ ላይ ነውና እንተ ከተስተካከልክ እኛም እንስተካከላለን አንተ ከጠመምክ እኛም እንጠማለን በማለት ምላስን ይገስፃሉ፤ያስጠነቅቃሉም፡፡» (ቲርሚዚ)

  ለመንቀሳቀስ እጅግ ቀላሉ የሰው ልጅ አካል ምላስ ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ ልቅ ከሆነ ብዙ ወለምታ የሚያገጥመው የሰውነት አካልም ቢኖር ይኸው ቁራሽ ሥጋ (ምላስ) ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ለባለቤቱ እጅጉን ጎጂው ነገርም ምላስ ይሆናል፡፡ ወደ ዚናም ስንመጣ ብዙውን ጊዜ ዚና በአንዴ ስለማይከሰት በጅማሮውና በፍፃሜው መካከል የምላስ አስተዋጽኦ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ስለዚህ ከሞላ ጎደል የትልቁን ዚና መንገድ የሚያመቻቸው ምላስ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የምላስ ወለምታና መዘዝ ዝሙት ላይ ይጥላል፡፡ ለዚህም ነው መልዕክተኛው(ﷺ)ምላሱንና ብልቱን ከሐራም ነገር ለሚቆጣጠር ሰው ጀነት ሊገባ ዘንዳ ዋስትናን የሰጡት፡፡!

↝ ነብዩ(ﷺ)እንዲህ ብለዋል፡- «እርሱ ያ በሁለት መንጋጋዎቹ መካከል ያለውን (ምላሱን) እና በሁለት ጭኖቹ መካከል ያለውን(ብልቱን) ለሚጠብቅ (ለሚቆጣጠር)ሰው እኔ ለርሱ ለጀነት ዋስ እሆነዋለሁ፡፡»(ሙስሊም)

  በተጨማሪም ነብዩ(ﷺ)ለጀነት ዋስትናን ከሰጧቸው ስድስት ዓይነት ሰዎች መካከል አንዱ በሚናገርበት ጊዜ እውነትን የሚናገርና ብልቱን ከሐራም የሚጠብቅ ሰው ነው፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ ዑባዳ ቢን ሣቢት(ረድየላሁ

ዐንሁማ) እንዳስተላለፉት ↝ነብዩ(ﷺ)እንዲህ ብለዋል፡- «እናንተ ለስድስት ሥራዎች ዋስትና ስጡኝ፣እኔም በጀነት ዋስትና እሰጣችኋለሁና፡

①ኛ አማና በተሰጣቸሁ ጊዜ(እማናውን ለባለቤቱ) መልሱ፤

②ኛ ቃል ኪዳን በተጋባችሁ ጊዜ ቃል ኪዳናቸሁን ሙሉት፤

③ኛ በምትናገሩበት ጊዜ እውነታውን ተናገሩ፤

④ኛ ብልቶቻችሁን(ከሐራም ነገር)ጠብቁ፣

⑤ኛ ዓይኖቻቸሁን(ዕይታችሁን)ዝቅ አድርጉ፤

⑥ኛ እጆቻቸሁን(ሌሎችን ከመጐዳትና ኃጢአትን ከመፈጸም)ጠብቁ፡፡»

(በይሀቂ)በተጨማሪም ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፡- «በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው መልካም ነገርን ይናገር አልያም ዝም ይበል፡፡»(ቡኻሪና ሙስሊም)

☞ «ብዙ ሰዎች እሳት የሚገቡት በአፋቸውና በብልታቸው ምክንያት ነው፡፡!»(ቲርሚዚ)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group