Translation is not possible.
✍ምርጥ_ምክር_ከምርጡ_ነብይ
 
አንቱ የአላህ መልክተኛ ምከሩኝ አልኳቸው ይላል አቡዘር ረድየሏሁዐንሁ፦
 
💚የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ አላህን በመፍራት ላይ አደራ ለሁሉም ነገሮችህ ውበት
ይሆንልሀልና ፤
አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ~
 
💛የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ ቁርአን በማንበብና አላህን በማውሳት ላይ አደራ በሰማይ
እንድትወሳ በምድር ብርሀን ይሆንልሀልና ፤
አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ~
 
❤️የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ አደራ ዝምታን አብዛ ; ሰይጣንን ማባረሪያ ፣ ለዲንህ
ይረዳሀልና ፤
አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ፤
 
💚የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ አደራ ሳቅ አታብዛ መሳቅ ልብን ይገድላል ፣ የፊትን ኑር
ይወስዳልና ፤
አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ~
 
💛የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ እውነትን ተናገር መራራ እንኳን ቢሆን ፤
አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ~
 
❤️የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ በአላህ ላይ የሰውን ወቀሳ አትፍራ ፤
አቡዘር ፦ አንቱ የአላህ መልክተኛ ይጨምሩኝ ~
 
💝የአላህ መልክተኛ ﷺ ፦ የሰዎች ገመና የራስክን ገመና ከማወቅ ( ከመከታተል)
እንዳይከለክልክ ፤
 
ሶሂሁል ጃሚዕ
Send as a message
Share on my page
Share in the group