→ የትንሹ ዚና አደገኝነት
#የምላስ_ዚና_አደገኛነት ⇩
ሁሉም የሰውነት ክፍሎች እያንዳንዱ አዲስ ቀን በመጣ ቁጥር ምላስን ይገስፃሉ፤ ያስጠነቅቁታልም፤ አላህን እንዲፈራ፡፡ ዕጣ ፋንታቸው የሚወሰነው በምላስ ላይ ተመሥርቶ መሆኑን በመግለጽ ምላስ አላህን እንዲፈራ ይገስጹታል፡፡ ↝ይህንኑ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ በማለት ገልጸዋል፡- «በየቀኑ ጠዋት ጠዋት ሁሉም የአካል ክፍሎች አላህን ፍራ ዕጣ ፋንታችን የሚወሰነው ባንተ ሁኔታ ላይ ነውና እንተ ከተስተካከልክ እኛም እንስተካከላለን አንተ ከጠመምክ እኛም እንጠማለን በማለት ምላስን ይገስፃሉ፤ያስጠነቅቃሉም፡፡» (ቲርሚዚ)
ለመንቀሳቀስ እጅግ ቀላሉ የሰው ልጅ አካል ምላስ ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ ልቅ ከሆነ ብዙ ወለምታ የሚያገጥመው የሰውነት አካልም ቢኖር ይኸው ቁራሽ ሥጋ (ምላስ) ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ለባለቤቱ እጅጉን ጎጂው ነገርም ምላስ ይሆናል፡፡ ወደ ዚናም ስንመጣ ብዙውን ጊዜ ዚና በአንዴ ስለማይከሰት በጅማሮውና በፍፃሜው መካከል የምላስ አስተዋጽኦ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ስለዚህ ከሞላ ጎደል የትልቁን ዚና መንገድ የሚያመቻቸው ምላስ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የምላስ ወለምታና መዘዝ ዝሙት ላይ ይጥላል፡፡ ለዚህም ነው መልዕክተኛው(ﷺ)ምላሱንና ብልቱን ከሐራም ነገር ለሚቆጣጠር ሰው ጀነት ሊገባ ዘንዳ ዋስትናን የሰጡት፡፡!
↝ ነብዩ(ﷺ)እንዲህ ብለዋል፡- «እርሱ ያ በሁለት መንጋጋዎቹ መካከል ያለውን (ምላሱን) እና በሁለት ጭኖቹ መካከል ያለውን(ብልቱን) ለሚጠብቅ (ለሚቆጣጠር)ሰው እኔ ለርሱ ለጀነት ዋስ እሆነዋለሁ፡፡»(ሙስሊም)
በተጨማሪም ነብዩ(ﷺ)ለጀነት ዋስትናን ከሰጧቸው ስድስት ዓይነት ሰዎች መካከል አንዱ በሚናገርበት ጊዜ እውነትን የሚናገርና ብልቱን ከሐራም የሚጠብቅ ሰው ነው፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ ዑባዳ ቢን ሣቢት(ረድየላሁ
ዐንሁማ) እንዳስተላለፉት ↝ነብዩ(ﷺ)እንዲህ ብለዋል፡- «እናንተ ለስድስት ሥራዎች ዋስትና ስጡኝ፣እኔም በጀነት ዋስትና እሰጣችኋለሁና፡
①ኛ አማና በተሰጣቸሁ ጊዜ(እማናውን ለባለቤቱ) መልሱ፤
②ኛ ቃል ኪዳን በተጋባችሁ ጊዜ ቃል ኪዳናቸሁን ሙሉት፤
③ኛ በምትናገሩበት ጊዜ እውነታውን ተናገሩ፤
④ኛ ብልቶቻችሁን(ከሐራም ነገር)ጠብቁ፣
⑤ኛ ዓይኖቻቸሁን(ዕይታችሁን)ዝቅ አድርጉ፤
⑥ኛ እጆቻቸሁን(ሌሎችን ከመጐዳትና ኃጢአትን ከመፈጸም)ጠብቁ፡፡»
(በይሀቂ)በተጨማሪም ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፡- «በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው መልካም ነገርን ይናገር አልያም ዝም ይበል፡፡»(ቡኻሪና ሙስሊም)
☞ «ብዙ ሰዎች እሳት የሚገቡት በአፋቸውና በብልታቸው ምክንያት ነው፡፡!»(ቲርሚዚ)