የተባረከው የፍልስጤም ምድር ክፍል 1
የተባረከው የፍልስጤም ምድር መቼም ቢሆን የአይሁድ ይዞታ ሆኖ አያውቅም፡፡ ለዚህ አንዱ ማስረጃ ለአይሁድ የተለየ አገር (separate homeland) የመፍጠሩ ሀሳብ ሲንሸራሸር በነበረበት ወቅት ከፍልስጤም ውጭ ሌላም ቦታ ታስቦ የነበረ መሆኑ ነው፡፡
ዛሬ ዓለምን ለማደናገር እንደሚሞከረው የፍልስጤም ምድር ከድሮም የአይሁድ ይዞታ የነበረ ቢሆን ኖሮ፣ ለነሱ አገር ቤት በመፍጠሩ ሀሣብ ውስጥ አርጀንቲናና ዑጋንዳ ታሳቢ ባልተደረጉ ነበር፡፡
ለአይሁድ የብቻ አገር ቤት የመፍጠሩ ሀሣብ የአውሮጳን ቡራኬ አግኝቶ በዋናነት ፍልስጤም ተመረጠች፡፡ ዓላማውን እውን የማድረጉ እንቅስቃሴም ተጀመረ፡፡ ጊዜው በ8ኛው መቶ ሂጅሪያ ማብቂያ ላይ ነበር፡፡ ይህ ወቅት ደሞ የምዕራብ የኩ#ፍ..ር ኃይላት የዑስማንያ ቱርክን ኢስላማዊ መንግሥት ለመጣል የተጠናከረ ርብርብ እያደረጉ የነበረበት ወቅት ነው፡፡
አይሁዶችም ይህንኑ ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀምና ገፀ-በረከት በማስያዝ አንድ ከማኅበረ-አይሁድ የተውጣጣ የልዑካን ቡድን በአውሮጳ ድጋፍ ሰጪነት ወደ ወቅቱ የዑስማኒያ ኸሊፋ ሡልጣን ዐብዱልሐሚድ ላኩ፡፡ ልዑኩም በሡልጣኑ ቤተ-መንግሥት ተገኝቶ አይሁዳዊያን በፍልስጥኤም መሬት ላይ መሥፈር እንዲችሉና የመግቢያ ፈቃድም እንዲሰጣቸው ተማጽኖ አቀረበ፡፡
ሡልጣን ዐብዱልሐሚድ ግን በጊዜው መንግሥታቸው ላይ እየተደረገ በነበረው አሉታዊ ጫና ሳይበገሩ፣ በቀረበላቸው ገፀ-በረከትም ሳይደለሉ የአይሁዶችን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ፡፡ አይሁዶች አንዴ እንደምንም ብለው ፍልስጤም መሬት ላይ እግር መትከል ከቻሉ አገሪቱን ከተቀረው ኢስላማዊ ግዛት በቀላሉ በመነጠል የግላቸው ሊያደርጓት ይችላሉ የሚል ስጋት ነበራቸው፡፡ ቀድሞ ከታያቸው ከዚህ ሥጋት በመነሳትም ይመስላል ሡልጣኑ በ1900 እና በ1901 መካከል በነበረው አጭር ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ ደንቦችን በማስረቀቅ ማንኛውም የአይሁድ መንገደኛ ከሶስት ወር ባለፈ ፍልስጥጤም መሬት ላይ ውሎ ማደር እንደሌለበት የደነገጉት፡፡ ከዚህም ሌላ ምንም ዐይነት የመሬት ሽያጭ ከአይሁድ ጋር እንዳይፈፀም ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡
የአይሁዶች ጥረት ግን በቀላሉ የሚቆም አልነበረም፡፡ ሰላሳ አምስት ሚሊዮን የወርቅ ዲናሮችን በከረጢት ቋጥረው እንደገና በ1920 ወደ ሡልጣኑ ቤተ-መንግሥት አመሩ፡፡ በጊዜው የዑስማኒያ ኢስላማዊ መንግሥት ካዝና በብዙ ወጪዎች ተራቁቶ ባዶ እንደነበረም ያውቃሉ፡፡ እንደዛም ሁኖ ግን የኢስላማዊውን መንግሥት ይሁንታ በወርቅ ሳንቲሞች ለመግዛት ያደረጉት ጥረት በሡልጣኑ ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም፡፡ ሡልጣኑ የጉዳዩ ዋና አስተባባሪ ለነበረው ለቴዎዶር ሄርዞል በላኩት ማስታወሻ ግልጽ አደረጉ
“… የግል ንብረቴ አይደለምና ከፍልስጤም መሬት ስንዝር ቆርሼ መስጠት አልችልም፡፡ ባለመብቱ ህዝቡ ነው፡፡ ህዝቦቼ ለዚህ መሬት ሲሉ የህይወት መሥዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ ደማቸውን አፍሰውበታል፡፡ ስለዚህ አይሁዶች የወርቅ ዲናሮቻቸውን ለራሳቸው ያድርጉት፡፡ ምናልባት መንግሥቴ ቢፈርስ ያን ጊዜ ፍልስጤምን በቀላሉ ነጥሎ መያዝ ይቻላቸው ይሆናል፡፡ እኔ በአፀደ ሥጋ እያለሁ ግን ከሰውነቴ ላይ በስለት ተቆርጦ ቢወሰድ ይቀለኛል - ፍልስጤም ከኢስላማዊው መንግሥት ተነጥላ ስትሄድ ከማይ፡፡ ይህ ደሞ ከቶም ሊሆን የማይችል ነው” በማለት ያላቸውን ቁርጠኛ አቋም ግልጽ አደረጉላቸው፡፡
እንደሚታወቀው ቴዎዶር ሄርዞል ዋነኛ የአይሁድ አገር ቤት ምሥረታ አቀንቃኝ የነበረ ሰው ነው፡፡ ሠፈራን መሠረት ያደረገ ቅኝ ግዛት እንዴት ሊቋቋም እንደሚችል ቀድም ሲል ጀምሮ ከሮዲዚያ የዛሬዋ ዚምባውቤና መሠል ሀገራት ልምድ በመውሰድ የአይሁድ አገር ቤት ምሥረታም በተመሳሳይ መንገድ ሊከናወን እንደሚችል የፀና እምነት ነበረው፡፡
ከዚህ በኋላ አይሁዶች በቀጥታ ወደ ፍልስጤም ለመግባት ያደረጉት ሙከራ እንዳልተሳካ እየገባቸው ሲመጣ አሳቻ መንገዶችን መጠቀም ጀመሩ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜም ተሳክቶላቸው ´Union & progress society’ የተሰኘ ቱርካዊ ሥያሜ በመያዝ ሙስሊም ነን በሚሉ አንድ የአይሁድ ጎሣ ድርጅት በኩል ቀስ በቀስ ወደ ፍልስጤም መግባት ቻሉ፡፡ ይህን ያህል መግቢያና እግር መትከያ ክፍተት ካገኙም በኋላ ወደ ፍልስጤም የሚያደርጉትን ንቅናቄ በድርጅቱ አባላት በኩል የበለጠ በማጠናከር እስከ 1924 የኸሊፋው ይፋ ውድቀት ድረስ ቀጠሉ፡፡
ከ1917 ጀምሮ ኢየሩሣሌም የገባውና ቁጥጥሩን የዘረጋው የእንግሊዝ ጦር በሚሰጣቸው ከለላ አንዳንድ እያሉ በፍልስጤም መሥፈር የጀመሩት አይሁዶችም ዋል አደር እያሉ ድንበር እየገፉ አጥር ማጠራቸውን ተያያዙት፡፡ ድርጊቱ ነዋሪዎቹን ዐረቦች እያስቆጣ ሲመጣ የእንግሊዝ ጦር ከሠፋሪ አይሁዶች በስተጀርባ በመሆን ይተኮስባቸው ጀመር፡፡ በዚህ ዐይነት ሤራ የአይሁድ በፍልስጤም ምድር ላይ መሥፈርና ብሎም መስፋፋት ከእንግሊዞች በኩል ያልተቆጠበ ድጋፍ እየተቸረው የብረት ሽፋንም እየተደረገለት ቀጠለ።
በምዕራባዊያን በኩል ፍልስጤምን ቅኝ የማድረጉ ፍላጎትና የአይሁድ የአገር ቤት ምሥረታ ጥያቄ አንድ ላይ መገጣጠሙ የራሱ ድርሻ ነበረው፡፡ ምዕራባዊያን የዑስማንያን ኢስላማዊ መንገሥት ካሸነፉ በኋላ ለዘመናት በሥሩ የቆየውን ሰፊ ኢስላማዊ ግዛት ለመቀራመት ሲከጅሉ ዐይናቸውን ከጣሉባቸው መሬቶች አንዷ ፍልስጤም ነበረች፡፡ የምዕራባዊያኑን ክጃሎት የሳበችው በታሪካዊነቷ ብቻ ግን አልነበረም፡፡ በመልክዐ-ምድራዊ አቀማመጧ በአፍሪካዊት ዐረባዊት ግብጽና በኢስያ ዐረቦች መካከል እንደ አገናኝ ድልድይ ስለሆነች በዚህ ጊዜና ከዚህም በኋላ ሊኖር በሚችለው የሙስሊሞች ድንበር ዘለል ትብብር ላይ ሣንካ ለመፍጠር ከመሀል ፍልስጤምን ነጥሎ መያዙ በምዕራባዊያን ዘንድ እንደ አዋጭ መንገድ ሆኖ ታሰበበት፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጊዜው የግብፅ አገረ-ገዢ የነበረው ሙሐመድ ባሻ ወደ ሻም ጉዞ አደረገ፡፡ የሱ ጉዞ ግብፅና ሶሪያን ሊያስተባብር ይችላል በሚል ግምት እንግሊዞች ስጋት ገባቸው፡፡ ቀደም ሲል ጀምሮ ሲቀነቀን በነበረው መሠረት ግብጽና ሻም በሚገናኙበት ማዕከላዊ ግዛት ላይ የአይሁድን የሠፈራ ፕሮግራም መቀበልና ማጠናከር እንዳለባቸው ተማመኑ፡፡ እንቅስቃሴም ጀመሩ፡፡ ይህ ደሞ ለምዕራባዊያን ሌላ ድብቅ በረከት ነበረው፡፡ ራስ ምታት ከሆኑባቸው አይሁዶች መገላገል፡፡ እናም ፍልስጤም በእንግሊዞች እጅ ለአይሁዶች ተበረከተች፡፡ መርዛሙን እሾህ ፍልስጤም ምድር ላይ በመትከልና ተንከባክቦ በማሳደግም አውሮጳ በተለይም ኢንግልተራ (እንግሊዝ) የአንበሻውን ድርሻ ያዙ
ይቀጥላል.......
ፔጁን follow ማድረግ አየይዘንጉ