UMMA TOKEN INVESTOR

Qumuqta qilghuchi yo'q.

🔖 ወደ ተውሒድ የተጣራው ወፍ (ሁድ ሁድ)

⚠️ ሁድ ሁድ የተባለው ገራሚው ወፍ ለተውሒድ በጣም ጊየራ (ቅናት) ያለው ወፍ ነበር። የሚደንቀው ይህ ወፍ ባለ ስልጣናት ያላቸውን ሁሉንም ነገር የተሰጠችውን ንጉስ አግኝቶ በዱንያ ድሎት ፣ የስልጣን ማእረግ ፣ ክብር ወዘተ እሄ ሁሉ ነገር ተመልክቶ ሳይገርመው ለፀሐይ ሲሰግዱ ሲያቸው ተገርሞ አልቻለም ለአሏህ ዲን ለተውሒድ ዘብ ሆነ ።

እስቲ የአሏህ ቃል ከቁርኣን አሏህ ስለዚህ ወፍ የሚናገረውን እንመልከት ።

قال تعالى :-

{ﻭَﻟَﻘَﺪْ ﺁﺗَﻴْﻨَﺎ ﺩَﺍﻭُﻭﺩَ ﻭَﺳُﻠَﻴْﻤَﺎﻥَ ﻋِﻠْﻤًﺎ ۖ ﻭَﻗَﺎﻟَﺎ ﺍﻟْﺤَﻤْﺪُ ﻟِﻠَّﻪِ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻓَﻀَّﻠَﻨَﺎ ﻋَﻠَﻰٰﻛَﺜِﻴﺮٍ ﻣِﻦْ ﻋِﺒَﺎﺩِﻩِ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦ}

"ለዳውድና ለሱለይማንም እውቀትን በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡ አሉም “ምስጋና ለአላህ ይገባው፡፡ ለዚያ ከምእምናን ባሮቹ በብዙዎቹ ላይ ላበለጠን፡፡”

{ﻭَﻭَﺭِﺙَ ﺳُﻠَﻴْﻤَﺎﻥُ ﺩَﺍﻭُﻭﺩَ ۖ ﻭَﻗَﺎﻝَ ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﻋُﻠِّﻤْﻨَﺎ ﻣَﻨْﻄِﻖَ ﺍﻟﻄَّﻴْﺮِ ﻭَﺃُﻭﺗِﻴﻨَﺎ ﻣِﻦْ ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ۖ ﺇِﻥَّ ﻫَٰﺬَﺍ ﻟَﻬُﻮَ ﺍﻟْﻔَﻀْﻞُ ﺍﻟْﻤُﺒِﻴﻦ}

"ሱለይማንም ዳውድን ወረሰ፡፡ አለም “ሰዎች ሆይ የወፍን ቋንቋን ተስተማርን፡፡ ከነገሩ ሁሉም ተሰጠን፡፡ይህ እርሱ በእርግጥ ግልጽ የሆነ ችሮታ ነው”

{ﻭَﺣُﺸِﺮَ ﻟِﺴُﻠَﻴْﻤَﺎﻥَ ﺟُﻨُﻮﺩُﻩُ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺠِﻦِّ ﻭَﺍﻟْﺈِﻧْﺲِ ﻭَﺍﻟﻄَّﻴْﺮِ ﻓَﻬُﻢْ ﻳُﻮﺯَﻋُﻮﻥ}

"ለሱለይማንም ሰራዊቶቹ ከጂን፣ ከሰውም፣ ከወፍም የሆኑት ተሰበሰቡ፡፡ እነሱም በስርኣት ይደራጃሉ"

{ﺣَﺘَّﻰٰ ﺇِﺫَﺍ ﺃَﺗَﻮْﺍ ﻋَﻠَﻰٰ ﻭَﺍﺩِ ﺍﻟﻨَّﻤْﻞِ ﻗَﺎﻟَﺖْ ﻧَﻤْﻠَﺔٌ ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﻤْﻞُ ﺍﺩْﺧُﻠُﻮﺍ ﻣَﺴَﺎﻛِﻨَﻜُﻢْ ﻟَﺎ ﻳَﺤْﻄِﻤَﻨَّﻜُﻢْ ﺳُﻠَﻴْﻤَﺎﻥُ ﻭَﺟُﻨُﻮﺩُﻩُ ﻭَﻫُﻢْ ﻟَﺎ ﻳَﺸْﻌُﺮُﻭﻥ}

"በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን “እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ እንዳይሰባብሩዋችሁ” አለች"

{ﻓَﺘَﺒَﺴَّﻢَ ﺿَﺎﺣِﻜًﺎ ﻣِﻦْ ﻗَﻮْﻟِﻬَﺎ ﻭَﻗَﺎﻝَ ﺭَﺏِّ ﺃَﻭْﺯِﻋْﻨِﻲ ﺃَﻥْ ﺃَﺷْﻜُﺮَ ﻧِﻌْﻤَﺘَﻚَ ﺍﻟَّﺘِﻲ ﺃَﻧْﻌَﻤْﺖَ ﻋَﻠَﻲَّ ﻭَﻋَﻠَﻰٰ ﻭَﺍﻟِﺪَﻱَّ ﻭَﺃَﻥْ ﺃَﻋْﻤَﻞَ ﺻَﺎﻟِﺤًﺎ ﺗَﺮْﺿَﺎﻩُ ﻭَﺃَﺩْﺧِﻠْﻨِﻲ ﺑِﺮَﺣْﻤَﺘِﻚَ ﻓِﻲ ﻋِﺒَﺎﺩِﻙَ ﺍﻟﺼَّﺎﻟِﺤِﻴﻦ}

"(ሱለይማን) ከንግግርዋም እየሳቀ ፈገግ አለ፡፡ “ጌታዬ ሆይ ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን፣ የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሰራ ምራኝ፡፡ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አግባኝ” አለ

{ﻭَﺗَﻔَﻘَّﺪَ ﺍﻟﻄَّﻴْﺮَ ﻓَﻘَﺎﻝَ ﻣَﺎ ﻟِﻲَ ﻟَﺎ ﺃَﺭَﻯ ﺍﻟْﻬُﺪْﻫُﺪَ ﺃَﻡْ ﻛَﺎﻥَ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻐَﺎﺋِﺒِﻴﻦ}

"ወፎቹንም ተመለከተ፤ አለም፡ “ምነው ሁድሁድን አላየውም?! ወይስ (በቦታው) ከሌሉት ሆኗልን?”

{ﻟَﺄُﻋَﺬِّﺑَﻨَّﻪُ ﻋَﺬَﺍﺑًﺎ ﺷَﺪِﻳﺪًﺍ ﺃَﻭْ ﻟَﺄَﺫْﺑَﺤَﻨَّﻪُ ﺃَﻭْ ﻟَﻴَﺄْﺗِﻴَﻨِّﻲ ﺑِﺴُﻠْﻄَﺎﻥٍ ﻣُﺒِﻴﻦ}

“በእርግጥ ብርቱ ቅጣትን እቀጣዋለሁ፡፡ ወይም በእርግጥ አርደዋለሁ። ወይም (ለመጥፋቱ አሳማኝ የሆነ) ግልፅ የሆነን ማስረጃ ያመጣልኛል” (አለ)"

{ﻓَﻤَﻜَﺚَ ﻏَﻴْﺮَ ﺑَﻌِﻴﺪٍ ﻓَﻘَﺎﻝَ ﺃَﺣَﻄْﺖُ ﺑِﻤَﺎ ﻟَﻢْ ﺗُﺤِﻂْ ﺑِﻪِ ﻭَﺟِﺌْﺘُﻚَ ﻣِﻦْ ﺳَﺒَﺈٍ ﺑِﻨَﺒَﺈٍ ﻳَﻘِﻴﻦ}

"(ሁድሁድ ግን) እሩቅ ያልሆነንም ጊዜ ቆዬ፡፡ አለም “ያላወቅከውን ነገር አወቅኩ፡፡ ከሰበእም እርግጠኛን ወሬ አመጣሁልህ፡፡”

{ﺇِﻧِّﻲ ﻭَﺟَﺪْﺕُ ﺍﻣْﺮَﺃَﺓً ﺗَﻤْﻠِﻜُﻬُﻢْ ﻭَﺃُﻭﺗِﻴَﺖْ ﻣِﻦْ ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻭَﻟَﻬَﺎ ﻋَﺮْﺵٌ ﻋَﻈِﻴﻢ}

“እኔ የምትገዛቸው (ሰዎች ያሏት) የሆነችን፣ ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን ሴት አገኘሁ፡፡ ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አልላት፡፡

{ﻭَﺟَﺪْﺗُﻬَﺎ ﻭَﻗَﻮْﻣَﻬَﺎ ﻳَﺴْﺠُﺪُﻭﻥَ ﻟِﻠﺸَّﻤْﺲِ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺯَﻳَّﻦَ ﻟَﻬُﻢُ ﺍﻟﺸَّﻴْﻄَﺎﻥُ ﺃَﻋْﻤَﺎﻟَﻬُﻢْ ﻓَﺼَﺪَّﻫُﻢْ ﻋَﻦِ ﺍﻟﺴَّﺒِﻴﻞِ ﻓَﻬُﻢْ ﻟَﺎ ﻳَﻬْﺘَﺪُﻭﻥ}

“እርሷንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለፀሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው፡፡ ሰይጣንም ለእነሱ (መጥፎ) ስራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል። ከእውነተኛውም መንገድ አግዷቸዋል፡፡ ስለዚህ እነሱ (ወደ እውነት) አይምመሩም”

{ﺃَﻟَّﺎ ﻳَﺴْﺠُﺪُﻭﺍ ﻟِﻠَّﻪِ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻳُﺨْﺮِﺝُ ﺍﻟْﺨَﺐْﺀَ ﻓِﻲ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻭَﻳَﻌْﻠَﻢُ ﻣَﺎ ﺗُﺨْﻔُﻮﻥَ ﻭَﻣَﺎ ﺗُﻌْﻠِﻨُﻮﻥ}

“ለዚያ በሰማያትና በምድር የተደበቀውን ለሚያወጣው፣ የምትሸሽጉትንና የምትገልፁትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ (ሰይጣን አግዷቸዋል)”

{ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟَﺎ ﺇِﻟَٰﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﻫُﻮَ ﺭَﺏُّ ﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﻟْﻌَﻈِﻴﻢِ ۩}

“አላህ ከርሱ ሌላ (የእውነት) አምላክ የለም፡፡ የታላቁ ዐርሽ (ዙፋን) ጌታ ነው”

{ﻗَﺎﻝَ ﺳَﻨَﻨْﻈُﺮُ ﺃَﺻَﺪَﻗْﺖَ ﺃَﻡْ ﻛُﻨْﺖَ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻜَﺎﺫِﺑِﻴﻦ}

"(ሱለይማንም) አለ፡- “እውነት እንደ ተናገርክ ወይም ከውሸታሞቹ እንደ ሆንክ ወደፊት እናያለን”

{ﺍﺫْﻫَﺐْ ﺑِﻜِﺘَﺎﺑِﻲ ﻫَٰﺬَﺍ ﻓَﺄَﻟْﻘِﻪْ ﺇِﻟَﻴْﻬِﻢْ ﺛُﻢَّ ﺗَﻮَﻝَّ ﻋَﻨْﻬُﻢْ ﻓَﺎﻧْﻈُﺮْ ﻣَﺎﺫَﺍ ﻳَﺮْﺟِﻌُﻮﻥ}

“ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ሂድ፡፡ ወደ እነርሱም ጣለው፡፡ ከዚያም ከእነሱ ዘወር በል፡፡ምን አንደሚመልሱም ተመልከት”

ሁድሁድ የታዘዘውን ፈፀመ ደብዳቤውንም ከሱለይማን ወስዶ የመን ደርሶ የሰበእ ንግስት ከምትገኝበት ስፍራ ጣለው፡፡ ደብዳቤው ከንግስቲቷ እጅ ገባ፡፡

{ﻗَﺎﻟَﺖْ ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟْﻤَﻠَﺄُ ﺇِﻧِّﻲ ﺃُﻟْﻘِﻲَ ﺇِﻟَﻲَّ ﻛِﺘَﺎﺏٌ ﻛَﺮِﻳﻢ}

አለች፡ “እናንተ መማክርቶች ሆይ እኔ የተከበረ ደብዳቤ ወደኔ ተጣለ፡፡”

{ﺇِﻧَّﻪُ ﻣِﻦْ ﺳُﻠَﻴْﻤَﺎﻥَ ﻭَﺇِﻧَّﻪُ ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَٰﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢ}

“እነሆ እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (የሚል መክፈቻ አለው"

{ﺃَﻟَّﺎ ﺗَﻌْﻠُﻮﺍ ﻋَﻠَﻲَّ ﻭَﺃْﺗُﻮﻧِﻲ ﻣُﺴْﻠِﻤِﻴﻦ}النمل ١٥-٣١

“በእኔ ላይ አትኩሩ፡፡ ታዛዦችም ሆናችሁ ወደኔ ኑ (የሚል ነው)፡፡"

አሏሁ አክበር!! الله أكبر

✍️ አብ ኒሐል አዩብ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
7 month Translate
Qumuqta qilghuchi yo'q.

የሂጃብ ፅንስ ሃሳብ  በልብስ ላይ ብቻ  የሚወሰን አይደለም። ሂጃብ ኒቃብ  ለሴት ልጅ  የክብር ዘውድ ከለካፊዎች መጠበቂያ  ወንዶችን እዳትፈትን ግዴታ ያደረገባት ልዩ ስጦታ ነው። ስለዚህ እህቴ ራስሺን በሂጃብ ለኒቃብ ልትሰትሪ ግድ ይልሻል። የአንቺ መስተካከል የማህበረሰቡ መስተካከል ነውና  ራስሽን አስተካክሊ የተፈና በሮች ይዘጉ ዘንድ  ‼️

ሸኽ ሷሊህ አልፈውዛን ሀፊዘሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

       እህቴ ሆይ ልብ በይ

➘ ሂጃብ እኮ መርዛማ ከሆኑ እይታዎች ይጠብቅሻል!!

➘ከበሽተኛ ልብ እና ከሰው ውሾች  የመነጨ እይታ ይከላከልልሻል!

የአሳዳጆችን ክጀላ ካንቺ ላይ ይቆርጣል

☞ ስለዚህ ሂጃብሽ እንዳይለይሽ!

☞ ለአዘናጊዎች ጥሪ ጆሮሽን አትስጪ!

☞ሂጃብን የሚዋጉ የሆኑትን ጥሪ (አትስሚ)!

☞ ወይም ጉዳዩን የሚያቃልሉትን ጥሪ (አትስሚ)!

☞ እነሱ ላንቺ መጥፎን ይፈልጉልሻልና!

አላህ እንዲህ እንዳለው

﴿ وَيُرِيدُ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الشَّهَوَاتِ أَنْ تَمِيلُوا مَيْلًا عَظِيمًا ﴾ .“

﴾እነዚያ ስሜታቸውን የሚከተሉት ደግሞ ከባድ የሆነን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ! ﴿

አንድት ሴት በቤቷ ስትቀመጥ  ወይም  አንድ ወንድ አይኑን  ከመቀላወጥ  ሲያግድም  የሂጃብ እሳቤ ይስተዋላል። ሴቶች ወደ አደባባይ ሲወጡ  ከባሎቻቸው  ወይም ከጠባቂዎቻቸው ጋር  እንድሆን  ያዛል

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Qumuqta qilghuchi yo'q.

[የጁሙዓ ቀን በላጭነት]

ኢብኑ ቀይም አልጀውዚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-

" ጁሙዓ የአምልኮ ቀን ነው።በቀናቶች ውስጥ ጁሙዓ ያለው ደረጃ የረመዷን ወር በወራት ውስጥ እንዳለው ደረጃ ነው።በውስጡም ያለው የምላሿ ሰዓት ረመዷን ውስጥ እንዳለው የለይለተል ቀድር ሌሊት ነው።"

📚زاد المعاد في هدي خير العباد (۳۸۷/۱)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
فاطيماة 97466408892 Сhanged his profile picture
7 month
Qumuqta qilghuchi yo'q.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group