UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ሁሉም ሰው በህይወት መንገድ

ወደ ሞት ይሄዳል ...

⇨ ለዲኑ ታጋይ የሆነና በዛም የተሰዋ ግን

በሞት መንገድ ወደ ህይወት ይሄዳል ።

( وَلَا تَحْسَبَنَّ ٱلَّذِينَ قُتِلُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ أَمْوَٰتًۢا ۚ بَلْ أَحْيَآءٌ عِندَ رَبِّهِمْ يُرْزَقُونَ )

" እነዚያን በአላህ መንገድ የተገደሉትን

ሙታን አድርገህ አትገምታቸው

በእርግጥ እነርሱ ጌታቸው ዘንድ

ሕያዋን ናቸው ይመገባሉ ፡፡"

[አል~ ዒምራን 169]   

                   

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

◾️ጀነተል ፊርደውስ የሚወርሱ ሙእሚኖች

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

✅ قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ

➡️ ሙእሚኖች ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡

✅ الَّذِينَ هُمْ فِي صَلَاتِهِمْ خَاشِعُونَ

➡️ እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች፡፡

✅ وَالَّذِينَ هُمْ عَنِ اللَّغْوِ مُعْرِضُونَ

➡️ እነዚያም እነርሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች፡፡

✅ وَالَّذِينَ هُمْ لِلزَّكَاةِ فَاعِلُونَ

➡️ እነዚያም እነርሱ ዘካን ሰጭዎች፡፡

✅ وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ

➡️ እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፡፡

✅ إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ

➡️ በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ ላይ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡

✅ فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ

➡️ ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው፡፡

✅ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ

➡️ እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውና ቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች፡፡

✅ وَالَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَوَاتِهِمْ يُحَافِظُونَ

➡️ እነዚያም እነሱ በስግደቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁ የኸኑት፡፡

✅ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْوَارِثُونَ

➡️ እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው፡፡

✅ الَّذِينَ يَرِثُونَ الْفِرْدَوْسَ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

➡️ እነዚያ (ጀነተል) ፊርደውስን የሚወርሱ ናቸው፡፡ እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡

📚(ሱረቱ አል-ሙእሚኑን 1 - 11)

                    

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

━┈የጥበብ ጫፍ ┅━

አንድ የሁዳዊ ወደ ሩቅ ሀገር እይተጓዘ ሳለ በመሀል የሙስሊሞች ሀገር ይደርሳል።

ያው እንደምታውቁት ይሁዳ ሁሌም ሸር እንዳሰበ ነው።

እናም፦"እዚህ ከተማ ገብቼ ዑለማኦችን ማደናገር አለብኝ" ብሎ ያስባል።

ከዚያም ከተማዋን ሊገባ ሲል አንድ እረኛ ያጋጥመውና በሱ ሊጀምር ወሰነ እና እንዲህ በማለት ጨወታ ጀመረ፦"እኛ ሙስሊሞች እኮ ቁርአን ለመሀፈዝ በጣም እየተቸገርን ነው።

አንደኛ፦30 ጁዝ ነው በዝቷል።

ሁለተኛ፦አንቀፆችም በጣም ብዙ ናቸው።

ሶስተኛው እና አስቸጋሪው ፦ ቁርአን ውስጥ ድግምግሞሽ አለ።

ስለዚህ ለምን የተደጋገሙ አንቀፆችን አንሰርዝም? ምክንያቱም የቃላት መደጋገም ነው እንጂ ምንም አይደለም።

ድግምግሞሹን ከሰረዝን መሀፈዙም ይቀለናል።"

የሁዳው ይሄን ሁሉ ሲያወራ እረኛው በፅሞና ያዳምጠው ነበር።

ከዚያም እረኛው ቀና አለና፦"ንግግርህ በጣም ደስ ይላል አሪፍ ሀሳብ ነው።" አለው።

የሁዳው ደስታው ወደር አጣ ነገር ግን ድብቅ ሴራው እንዳይታወቅበት ደስታውን ደበቀው።

እረኛውም እንዲህ በማለት ንግግሩን ቀጠለ፦

"አንድ ጥያቄ አለኝ።

ባንተ የሰውነት አካል ውስጥ ድግምግሞሽ የለም?

ለምሳሌ፦ ሁለት እጅ

☞ሁለት አይን

☞ሁለት እግር

☞ሁለት ጆሮ.....

ታዲያ ሰውነትህ ቀለል እንዲልልህ አንድ አንዱን ለምን አትቆርጥም? ያው ድግምግሞሽ ነው እንጂ እኮ ምንም አይደለም"

ይሄን ሲለው የሁዳው ደነገጠ።ፊቱን አጨፍግጎ፦ "የእረኛዎቻቸው መልስ እንዲህ ከሆነ የዑለማኦቻቸው መልስ እንዴት ሊሆን ነው?" እያለ ከተማዋን ትቶ አለፈ።

✍️አቡ ኒሀል አዩብ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ጌታችን ሆይ

በዚህ ሰዓት በፍልስጢን እና በመላው አለም በጭንቀት ላይ ያሉ ባሮችህን ፈርጃቸው:: ጋዛን ሰላም አድርግልን:: ለዲናችን ጠላት የሆኑትን ሁሉ አንተ መክትልን::

ያረቢ 🇵🇸ከወንድሞቻችን መልካም  አሰማን።

                

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

                 

             ዉለታ አንርሳ

ትንሽ ሆና ብትታየንም እንኳ መልካም ያደረገልንን ሰው ውለታ አንርሳ፡፡ ውለታውን መመለስ ባንችል እንኳ በዱዓእ እናግዘው፡፡ አስቦልን የሚመክረንን ሰው እናዳምጥ፡፡ ለኛ ባይገባንም እንኳ ስለኛ ማንነት ሳያውቅ ተከታትሎ ለሚያከብረን ሰው ቦታ እንስጥ፡፡ ችግሩን ለመፍታት አቅሙ ባይኖረንም እንኳ ቀርቦ ለሚያማክረን በቻልነው ያህል መፍትሄ እንጠቁም፡፡ የሚያስቡልንና በስስት ዐይን ለሚያዩን ሰዎች እኛም እናስብላቸው፡፡

                  

✍️አብ ኒሐል አዩብ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group