Translation is not possible.

🔖 ወደ ተውሒድ የተጣራው ወፍ (ሁድ ሁድ)

⚠️ ሁድ ሁድ የተባለው ገራሚው ወፍ ለተውሒድ በጣም ጊየራ (ቅናት) ያለው ወፍ ነበር። የሚደንቀው ይህ ወፍ ባለ ስልጣናት ያላቸውን ሁሉንም ነገር የተሰጠችውን ንጉስ አግኝቶ በዱንያ ድሎት ፣ የስልጣን ማእረግ ፣ ክብር ወዘተ እሄ ሁሉ ነገር ተመልክቶ ሳይገርመው ለፀሐይ ሲሰግዱ ሲያቸው ተገርሞ አልቻለም ለአሏህ ዲን ለተውሒድ ዘብ ሆነ ።

እስቲ የአሏህ ቃል ከቁርኣን አሏህ ስለዚህ ወፍ የሚናገረውን እንመልከት ።

قال تعالى :-

{ﻭَﻟَﻘَﺪْ ﺁﺗَﻴْﻨَﺎ ﺩَﺍﻭُﻭﺩَ ﻭَﺳُﻠَﻴْﻤَﺎﻥَ ﻋِﻠْﻤًﺎ ۖ ﻭَﻗَﺎﻟَﺎ ﺍﻟْﺤَﻤْﺪُ ﻟِﻠَّﻪِ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻓَﻀَّﻠَﻨَﺎ ﻋَﻠَﻰٰﻛَﺜِﻴﺮٍ ﻣِﻦْ ﻋِﺒَﺎﺩِﻩِ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦ}

"ለዳውድና ለሱለይማንም እውቀትን በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡ አሉም “ምስጋና ለአላህ ይገባው፡፡ ለዚያ ከምእምናን ባሮቹ በብዙዎቹ ላይ ላበለጠን፡፡”

{ﻭَﻭَﺭِﺙَ ﺳُﻠَﻴْﻤَﺎﻥُ ﺩَﺍﻭُﻭﺩَ ۖ ﻭَﻗَﺎﻝَ ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﻋُﻠِّﻤْﻨَﺎ ﻣَﻨْﻄِﻖَ ﺍﻟﻄَّﻴْﺮِ ﻭَﺃُﻭﺗِﻴﻨَﺎ ﻣِﻦْ ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ۖ ﺇِﻥَّ ﻫَٰﺬَﺍ ﻟَﻬُﻮَ ﺍﻟْﻔَﻀْﻞُ ﺍﻟْﻤُﺒِﻴﻦ}

"ሱለይማንም ዳውድን ወረሰ፡፡ አለም “ሰዎች ሆይ የወፍን ቋንቋን ተስተማርን፡፡ ከነገሩ ሁሉም ተሰጠን፡፡ይህ እርሱ በእርግጥ ግልጽ የሆነ ችሮታ ነው”

{ﻭَﺣُﺸِﺮَ ﻟِﺴُﻠَﻴْﻤَﺎﻥَ ﺟُﻨُﻮﺩُﻩُ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺠِﻦِّ ﻭَﺍﻟْﺈِﻧْﺲِ ﻭَﺍﻟﻄَّﻴْﺮِ ﻓَﻬُﻢْ ﻳُﻮﺯَﻋُﻮﻥ}

"ለሱለይማንም ሰራዊቶቹ ከጂን፣ ከሰውም፣ ከወፍም የሆኑት ተሰበሰቡ፡፡ እነሱም በስርኣት ይደራጃሉ"

{ﺣَﺘَّﻰٰ ﺇِﺫَﺍ ﺃَﺗَﻮْﺍ ﻋَﻠَﻰٰ ﻭَﺍﺩِ ﺍﻟﻨَّﻤْﻞِ ﻗَﺎﻟَﺖْ ﻧَﻤْﻠَﺔٌ ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﻤْﻞُ ﺍﺩْﺧُﻠُﻮﺍ ﻣَﺴَﺎﻛِﻨَﻜُﻢْ ﻟَﺎ ﻳَﺤْﻄِﻤَﻨَّﻜُﻢْ ﺳُﻠَﻴْﻤَﺎﻥُ ﻭَﺟُﻨُﻮﺩُﻩُ ﻭَﻫُﻢْ ﻟَﺎ ﻳَﺸْﻌُﺮُﻭﻥ}

"በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን “እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲሆኑ እንዳይሰባብሩዋችሁ” አለች"

{ﻓَﺘَﺒَﺴَّﻢَ ﺿَﺎﺣِﻜًﺎ ﻣِﻦْ ﻗَﻮْﻟِﻬَﺎ ﻭَﻗَﺎﻝَ ﺭَﺏِّ ﺃَﻭْﺯِﻋْﻨِﻲ ﺃَﻥْ ﺃَﺷْﻜُﺮَ ﻧِﻌْﻤَﺘَﻚَ ﺍﻟَّﺘِﻲ ﺃَﻧْﻌَﻤْﺖَ ﻋَﻠَﻲَّ ﻭَﻋَﻠَﻰٰ ﻭَﺍﻟِﺪَﻱَّ ﻭَﺃَﻥْ ﺃَﻋْﻤَﻞَ ﺻَﺎﻟِﺤًﺎ ﺗَﺮْﺿَﺎﻩُ ﻭَﺃَﺩْﺧِﻠْﻨِﻲ ﺑِﺮَﺣْﻤَﺘِﻚَ ﻓِﻲ ﻋِﺒَﺎﺩِﻙَ ﺍﻟﺼَّﺎﻟِﺤِﻴﻦ}

"(ሱለይማን) ከንግግርዋም እየሳቀ ፈገግ አለ፡፡ “ጌታዬ ሆይ ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን፣ የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሰራ ምራኝ፡፡ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አግባኝ” አለ

{ﻭَﺗَﻔَﻘَّﺪَ ﺍﻟﻄَّﻴْﺮَ ﻓَﻘَﺎﻝَ ﻣَﺎ ﻟِﻲَ ﻟَﺎ ﺃَﺭَﻯ ﺍﻟْﻬُﺪْﻫُﺪَ ﺃَﻡْ ﻛَﺎﻥَ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻐَﺎﺋِﺒِﻴﻦ}

"ወፎቹንም ተመለከተ፤ አለም፡ “ምነው ሁድሁድን አላየውም?! ወይስ (በቦታው) ከሌሉት ሆኗልን?”

{ﻟَﺄُﻋَﺬِّﺑَﻨَّﻪُ ﻋَﺬَﺍﺑًﺎ ﺷَﺪِﻳﺪًﺍ ﺃَﻭْ ﻟَﺄَﺫْﺑَﺤَﻨَّﻪُ ﺃَﻭْ ﻟَﻴَﺄْﺗِﻴَﻨِّﻲ ﺑِﺴُﻠْﻄَﺎﻥٍ ﻣُﺒِﻴﻦ}

“በእርግጥ ብርቱ ቅጣትን እቀጣዋለሁ፡፡ ወይም በእርግጥ አርደዋለሁ። ወይም (ለመጥፋቱ አሳማኝ የሆነ) ግልፅ የሆነን ማስረጃ ያመጣልኛል” (አለ)"

{ﻓَﻤَﻜَﺚَ ﻏَﻴْﺮَ ﺑَﻌِﻴﺪٍ ﻓَﻘَﺎﻝَ ﺃَﺣَﻄْﺖُ ﺑِﻤَﺎ ﻟَﻢْ ﺗُﺤِﻂْ ﺑِﻪِ ﻭَﺟِﺌْﺘُﻚَ ﻣِﻦْ ﺳَﺒَﺈٍ ﺑِﻨَﺒَﺈٍ ﻳَﻘِﻴﻦ}

"(ሁድሁድ ግን) እሩቅ ያልሆነንም ጊዜ ቆዬ፡፡ አለም “ያላወቅከውን ነገር አወቅኩ፡፡ ከሰበእም እርግጠኛን ወሬ አመጣሁልህ፡፡”

{ﺇِﻧِّﻲ ﻭَﺟَﺪْﺕُ ﺍﻣْﺮَﺃَﺓً ﺗَﻤْﻠِﻜُﻬُﻢْ ﻭَﺃُﻭﺗِﻴَﺖْ ﻣِﻦْ ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻭَﻟَﻬَﺎ ﻋَﺮْﺵٌ ﻋَﻈِﻴﻢ}

“እኔ የምትገዛቸው (ሰዎች ያሏት) የሆነችን፣ ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን ሴት አገኘሁ፡፡ ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አልላት፡፡

{ﻭَﺟَﺪْﺗُﻬَﺎ ﻭَﻗَﻮْﻣَﻬَﺎ ﻳَﺴْﺠُﺪُﻭﻥَ ﻟِﻠﺸَّﻤْﺲِ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺯَﻳَّﻦَ ﻟَﻬُﻢُ ﺍﻟﺸَّﻴْﻄَﺎﻥُ ﺃَﻋْﻤَﺎﻟَﻬُﻢْ ﻓَﺼَﺪَّﻫُﻢْ ﻋَﻦِ ﺍﻟﺴَّﺒِﻴﻞِ ﻓَﻬُﻢْ ﻟَﺎ ﻳَﻬْﺘَﺪُﻭﻥ}

“እርሷንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለፀሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው፡፡ ሰይጣንም ለእነሱ (መጥፎ) ስራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል። ከእውነተኛውም መንገድ አግዷቸዋል፡፡ ስለዚህ እነሱ (ወደ እውነት) አይምመሩም”

{ﺃَﻟَّﺎ ﻳَﺴْﺠُﺪُﻭﺍ ﻟِﻠَّﻪِ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﻳُﺨْﺮِﺝُ ﺍﻟْﺨَﺐْﺀَ ﻓِﻲ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻭَﻳَﻌْﻠَﻢُ ﻣَﺎ ﺗُﺨْﻔُﻮﻥَ ﻭَﻣَﺎ ﺗُﻌْﻠِﻨُﻮﻥ}

“ለዚያ በሰማያትና በምድር የተደበቀውን ለሚያወጣው፣ የምትሸሽጉትንና የምትገልፁትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ (ሰይጣን አግዷቸዋል)”

{ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻟَﺎ ﺇِﻟَٰﻪَ ﺇِﻟَّﺎ ﻫُﻮَ ﺭَﺏُّ ﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﻟْﻌَﻈِﻴﻢِ ۩}

“አላህ ከርሱ ሌላ (የእውነት) አምላክ የለም፡፡ የታላቁ ዐርሽ (ዙፋን) ጌታ ነው”

{ﻗَﺎﻝَ ﺳَﻨَﻨْﻈُﺮُ ﺃَﺻَﺪَﻗْﺖَ ﺃَﻡْ ﻛُﻨْﺖَ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻜَﺎﺫِﺑِﻴﻦ}

"(ሱለይማንም) አለ፡- “እውነት እንደ ተናገርክ ወይም ከውሸታሞቹ እንደ ሆንክ ወደፊት እናያለን”

{ﺍﺫْﻫَﺐْ ﺑِﻜِﺘَﺎﺑِﻲ ﻫَٰﺬَﺍ ﻓَﺄَﻟْﻘِﻪْ ﺇِﻟَﻴْﻬِﻢْ ﺛُﻢَّ ﺗَﻮَﻝَّ ﻋَﻨْﻬُﻢْ ﻓَﺎﻧْﻈُﺮْ ﻣَﺎﺫَﺍ ﻳَﺮْﺟِﻌُﻮﻥ}

“ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ሂድ፡፡ ወደ እነርሱም ጣለው፡፡ ከዚያም ከእነሱ ዘወር በል፡፡ምን አንደሚመልሱም ተመልከት”

ሁድሁድ የታዘዘውን ፈፀመ ደብዳቤውንም ከሱለይማን ወስዶ የመን ደርሶ የሰበእ ንግስት ከምትገኝበት ስፍራ ጣለው፡፡ ደብዳቤው ከንግስቲቷ እጅ ገባ፡፡

{ﻗَﺎﻟَﺖْ ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟْﻤَﻠَﺄُ ﺇِﻧِّﻲ ﺃُﻟْﻘِﻲَ ﺇِﻟَﻲَّ ﻛِﺘَﺎﺏٌ ﻛَﺮِﻳﻢ}

አለች፡ “እናንተ መማክርቶች ሆይ እኔ የተከበረ ደብዳቤ ወደኔ ተጣለ፡፡”

{ﺇِﻧَّﻪُ ﻣِﻦْ ﺳُﻠَﻴْﻤَﺎﻥَ ﻭَﺇِﻧَّﻪُ ﺑِﺴْﻢِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَٰﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢ}

“እነሆ እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (የሚል መክፈቻ አለው"

{ﺃَﻟَّﺎ ﺗَﻌْﻠُﻮﺍ ﻋَﻠَﻲَّ ﻭَﺃْﺗُﻮﻧِﻲ ﻣُﺴْﻠِﻤِﻴﻦ}النمل ١٥-٣١

“በእኔ ላይ አትኩሩ፡፡ ታዛዦችም ሆናችሁ ወደኔ ኑ (የሚል ነው)፡፡"

አሏሁ አክበር!! الله أكبر

✍️ አብ ኒሐል አዩብ

Send as a message
Share on my page
Share in the group