Umu Asya Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Umu Asya shared a
Translation is not possible.

ሁሉም ያልፋል ‼

  ሁሉም ያልፋል ሲባል ደግሞ

ችግር ብቻ አይደለም 

ምቾትም ያልፋል።

ሀዘን ብቻ አይደለም

ደስታም ያልፋል።

ድህነት ብቻ አይደለም

ሀብትም ያልፋል።

በሽታ ብቻ አይደለም

ጤንነትም ያልፋል።

    ከእኛ የሚጠበቀው በደጉ ሰዓት አመስጋኝ። በመጥፎው ሰዓት ደግሞ ታጋሽ መሆን ነው። የዚህን ጊዜ ሁሉም ቢያልፍም ለእኛ ጥሩ ስንቅ ሆኖ አለፈ ማለት ነው።     

                    ⇩

╭┅━━•🍃⚘🍃•━━━┅

⚘  ⚘ https://t.me/mesjidalteqwawenabo

╰┅━━•🍃⚘🍃•━━━┅

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Umu Asya shared a
Translation is not possible.

✍ እነዚህን 10 የሰውነት ምልክቶች ካስተዋሉ ችላ አይበሏቸው!

🔵#ሰውነታችን እያንዳንዱ ክፍል ተግባሩን የሚያከናውንበት የራሱ ሂደት አለው፡፡እነዚህ ሂደቶች በሚታወኩ ጊዜ ሰውነታችን እንድናውቅ የሚረዱ ምልክቶችን ይልካል፤ ስለሆነም እነዚህን ምልክቶች ማወቅ እና በቶሎ እርምጃ መውሰድ ተባብሰው የሚያስከትሉትን የከፋ ችግር መግታት ያስችላል፡፡

1. #የድድ መድማት፡- ይህ የቫይታሚን ሲ (Vitamin C) እጥረት ነው ስለዚህ ሻይ ይጠጡ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ይመገቡ፡፡

2. #የቆዳ መድረቅ፡- የቫይታሚን ኢ (Vitamin E) እጥረት ሲሆን የአሳ ዘይት፣ ለውዝ እና የአትክልት ዘይት ይመገቡ፡፡

3. #ጨው የበዛበት ምግብ አብዝቶ ለመጠቀም መፈለግ፡- ይህ የሰውነት መጉረብረብ (መመረዝ) ወይም የመራቢያ አካል ኢንፌክሽን አመላካች ሊሆን ይችላል፡፡

4. #ጣፋጭ ነገሮችን መውደድ ወይም መፈለግ፡- ይህ የሚያሳየው መጨነቅ (ስጋት) እና ድካም ነው፡፡ ስለዚህ ግሉኮስ ፈጣን እረፍት ይሰጠናል ብለን እናስባለን ነገር ግን በምትኩ ማር እና ደረቅ ቸኮሌት ይውሰዱ፡፡

5. #የእንቅልፍ ችግር፣ የሀሃፍረት ስሜት እና ግልፍተኝነት፡- ይህ ምልክት ማለት የማግኒዢየም እና ፖታሲየም እጥረት በሰውነታችን ውስጥ ተከስቷል ማለት ነው፡፡ ለማግኒዚም እጥረት ለውዝ፣ ሱፍ እና ተልባ ይመገቡ ለፖታሲየም ደግሞ ሙዝ፣ ስኳር ድንች፣ አረንጓዴ እና ቅጠል ያላቸው አትክልቶች፣ ስፒናች ጎመን፣ የስዊዝ ቆስጣ ይመገቡ።

6. #ጥሬ ምግቦችን መውደድ/ መፈለግ፡- ከጨጓራ ወይም ከየጉበት ጋር የተያያዘ ሲሆን ጥሬ ምግቦች የሆድ መነፋት እና ቁርጠትን ያስታግሳሉ፡፡

7. #የክርን ቆዳ መድረቅ፡- የቫይታሚን ኤ እና ሲ (Vitamin A & C) እጥረት ሲሆን ካሮት፣ ብርቱካን፣ አትክልትና ፍራፍሬ ይመገቡ፡፡

8. #የባህር ውስጥ ምግቦችን በጉጉት መፈለግ፡- የባህር ውስጥ ምግቦችን ለመመገብ በጣም የሚጓጉ ከሆነ የአዮዲን እጥረት እንዳለ ያመላክትዎታል።

9. #ለመራራ ምግቦች ከፍ ያለ ጉጉት መኖር፡- መራራ ምግቦችን ለጉበት እና የሃሞት ከረጢት ተግባር/ ሥራ ያስፈልገናል ስለዚህ ሎሚና ክሬይንቤሪ ይመገቡ፡፡

10. #የፀጉር እና ጥፍር መሰባበር፡- ሰውነትዎ የካልሲየም እና ቫይታሚን ቢ (Calcium & Vitamin b) እጥረት አለ ማለት ነው ስለዚህ ወተት፣ ድንች፣ ጥራጥሬ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንብራ እና ስንዴ ይመገቡ፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Umu Asya shared a
1 year Translate
Translation is not possible.

ስጁድ

#ስጁድ በምናደርግበት ጊዜ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ

ማግኔቲክ ጨረሮች ወደ መሬት ውስጥ ወዳለው ማግኔት

ይገባሉ፡፡ እነዚህ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ #ማግኔቲክ

ጨረሮች ለብስጭት፣ ለድብርት፣ለራስ ህመም እና ሌሎች

አሉታዊ ስሜቶች እንደሚያጋልጡን ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

ነገር ግን አንድ ሰው ስጁድ በሚያደርግበት ጊዜ በውስጡ ያሉት

ጨረሮች መሬት ውስጥ በተጋደመው ማግኔት ስለሚሳቡ

ከሰውየው ለቀው ይወጣሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ሰውየው እፎይታ

ይሰማዋል (ቅልል ይለዋል)፡፡ ሳይንስ # የምድር መሀል

(የመሬት እምብርት) ለንደን ሳትሆን መካ መሆኗን

አረጋግጧል፡፡ በመሆኑም በመካ የማግኔቲክ ስበቱ ከፍተኛ

ነው፡፡ ስለዚህ ለሐጅ ሄዶ በመካ ስጁድ የሚያደርግ ሰው

በሰውነቱ ውስጥ ዜሮ የማግኔቲክ ጨረሮች ይኖሩታል ማለት

ነው፡፡ ይህም ሰውየው እንደገና ተወለደ ወደሚለው የእስልምና

አስተምህሮ ይወስደናል፡፡

......ሱብሃን አላህ.........

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Umu Asya shared a
Translation is not possible.

በአንድ ወቅት በአውሮፓ አየር መንገድ የመጀመሪያ ደረጃ ክፍል

(Buisness Class) ውስጥ የተቀመጠ አንድ ሙስሊም ወጣት

ተሳፋሪ ነበር፡፡

በጉዞ ላይ ሳለ ከአውሮፕላኑ አስተናጋጆች አንዷ ለዚህ ሙስሊም

ወጣት የነፃ መጠጥ ይዛለት መጣች፡፡

መጠጡ የአልኮል መጠጥ ስለነበረ ሙስሊሙ ወጣት

አልተቀበለም፡፡

አስተናጋጇም ከመጠጫው ችግር ይሆን በሚል በሚስብና

በሚያምር ዲዛይን በተሰራ የመጠጥ ማቅረቢያ በድጋሚ ይዛለት

መጣች፡፡

ሙስሊሙ ወጣት የአልኮል መጠጥ እንደማይጠጣ በመናገር

አሁንም አልተቀበለም፡፡

አስተናጋጇ ጉዳዩ አሳሰባትና ለአውሮፕላኑ ማናጀር አሳወቀች፡፡

ማናጀሩ ይበልጥ ባሸበረቀ እቃ መጠጡን ይዞ መጣና ቀርቦ

ያናግረው ጀመር

“ወንድም በአገልግሎታችን ላይ ችግር አለ ወይ ሲል ጠየቀውና

ይህ ነፃና የጉዞ መክፈቻ መጠጥ ነው፤ እባክህ ጠጣ እንጂ” ሲል

ጠየቀው

ወጣቱ ሙስሊም “እኔ ሙስሊም ነኝ አልኮል መጠጥ አልጠጣም”

በማለት መለሰ፡፡

ማናጀሩ መጠጡን እንዲወስድ አሁንም መወትወቱን ቀጠለ. . .

ወጣቱ ሙስሊም “ማናጀር መጠጡን መጀመሪያ ለአውሮፕላን

አብራሪው ስጡት” አለ፡፡

ማናጀሩ “እንዴት አብራሪ እያበረረ አልኮል ይጠጣል? እሱኮ

ተልዕኮ ላይ ነው፡፡ አውሮፕላኑ እንዲከሰከስ ትፈልጋለህ ወይ ሲል

ጠየቀው ?” ወጣቱ ሙስሊም ረጋ ባለ አነጋገር “እኔ ሙስሊም ነኝ

ሁሌም ተልዕኮ ላይ ነኝ፡፡

ኢማኔን የመጠበቅ የሁልጊዜም ተልዕኮዬ ነው፡፡ ከጠጣሁ

የዚህንም የመጪውንም ሀገሬን ነው ማበላሸው” የሚል

የማያዳግም ምላሽ ሰጠው፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group