Tarjima qilib boʻlmadi.

በአንድ ወቅት በአውሮፓ አየር መንገድ የመጀመሪያ ደረጃ ክፍል

(Buisness Class) ውስጥ የተቀመጠ አንድ ሙስሊም ወጣት

ተሳፋሪ ነበር፡፡

በጉዞ ላይ ሳለ ከአውሮፕላኑ አስተናጋጆች አንዷ ለዚህ ሙስሊም

ወጣት የነፃ መጠጥ ይዛለት መጣች፡፡

መጠጡ የአልኮል መጠጥ ስለነበረ ሙስሊሙ ወጣት

አልተቀበለም፡፡

አስተናጋጇም ከመጠጫው ችግር ይሆን በሚል በሚስብና

በሚያምር ዲዛይን በተሰራ የመጠጥ ማቅረቢያ በድጋሚ ይዛለት

መጣች፡፡

ሙስሊሙ ወጣት የአልኮል መጠጥ እንደማይጠጣ በመናገር

አሁንም አልተቀበለም፡፡

አስተናጋጇ ጉዳዩ አሳሰባትና ለአውሮፕላኑ ማናጀር አሳወቀች፡፡

ማናጀሩ ይበልጥ ባሸበረቀ እቃ መጠጡን ይዞ መጣና ቀርቦ

ያናግረው ጀመር

“ወንድም በአገልግሎታችን ላይ ችግር አለ ወይ ሲል ጠየቀውና

ይህ ነፃና የጉዞ መክፈቻ መጠጥ ነው፤ እባክህ ጠጣ እንጂ” ሲል

ጠየቀው

ወጣቱ ሙስሊም “እኔ ሙስሊም ነኝ አልኮል መጠጥ አልጠጣም”

በማለት መለሰ፡፡

ማናጀሩ መጠጡን እንዲወስድ አሁንም መወትወቱን ቀጠለ. . .

ወጣቱ ሙስሊም “ማናጀር መጠጡን መጀመሪያ ለአውሮፕላን

አብራሪው ስጡት” አለ፡፡

ማናጀሩ “እንዴት አብራሪ እያበረረ አልኮል ይጠጣል? እሱኮ

ተልዕኮ ላይ ነው፡፡ አውሮፕላኑ እንዲከሰከስ ትፈልጋለህ ወይ ሲል

ጠየቀው ?” ወጣቱ ሙስሊም ረጋ ባለ አነጋገር “እኔ ሙስሊም ነኝ

ሁሌም ተልዕኮ ላይ ነኝ፡፡

ኢማኔን የመጠበቅ የሁልጊዜም ተልዕኮዬ ነው፡፡ ከጠጣሁ

የዚህንም የመጪውንም ሀገሬን ነው ማበላሸው” የሚል

የማያዳግም ምላሽ ሰጠው፡፡

image
Xabar sifatida yuborish
Sahifamda baham ko'rish
Guruhda ulashish