seid Abu Ayub Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

seid Abu Ayub shared a
Translation is not possible.

ያሳዝናል‼

========

✍ ጋዛን ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ያገናኝ የነበረው ብቸኛው የጀዋል ካምፓኒ ዓለም አቀፉ የኢንተርኔት ገመድ በጽዮናዊያኑ ቦምብ መመታቱን ተከትሎ ጋዛዊያን ድምፃቸው ታፍኖ ያለ ማቋረጥ ከ3 ሰዓታት በላይ የቆዬ እጅግ ዘግናኝ የቦምብ ጥቃት እየዘነበባቸው ነው።

በተጨማሪም በባህርም፣ በአየርም፣ በምድርም እሳት እየዘነበባቸው ነው።

ጠብቃ ጠብቃ እስራኤል ከሰሞኑ የከፋውን ጭፍጨፋ ዛሬ በጨለማ ጀምራለች።

ከ40 ሺህ በላይ ታማሚዎች የሚገኙበትን ዋነኛውን አልሺፋ ሆስፒታልንም አጋይታለች።

አንድም ፈለስጢናዊ በህይዎት ማየት አትፈልግም።

አምቡላንሶች እንኳ ወደ ሟቾችና ቁስለኞች ዘንድ በማምራት ማንሳት አልቻሉም።

እስራኤል ወንጀሏና የምትፈጽመው ዘግናኝ ጥቃት ተቀርፆ በሚዲያ እንዳይወጣባት ድምጿን አጥፍታ ወገኖቻችንን እየጨረሰች ነው።

በጘ-ዝ'ዛ ታሪክ ይቀር የማይለው የጦር ወንጀልና የዘር ማፅዳት ጭፍጨፈሰ እየተፈጸመ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሁንም በዝምታ ላይ ነው።

ሐስቡነ-ል'ሏህ ወ ኒዕመል ወኪል!

በጣም ነው የሚያሳዝነው! አላሁልሙስተዓን!

ቢያንስ በመልካም ዱዓችን አንርሳቸው።

||

t.me/MuradTadesse

Send as a message
Share on my page
Share in the group
seid Abu Ayub shared a
Translation is not possible.

ስለ ፈለስጢን ምን አዲስ ነገር አለ⁉️

========================

✍ የፈለስጢን (የጋዛ ሙስሊሞች) ጉዳይ በየቀኑ አሳዛኝነቱ ቀጥሏል። በየቀኑ የንጹሐን ህይዎት እየተቀጠፈ ነው፣ በርካታ መሠረት ልማቶች እየወደሙ ነው።

ዛሬ ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት እስካሁን 5087 ሙስሊሞች በጽዮናዊቷ ያላባራ የቦምብ ዝናብ ተገድለዋል፣ ከነዚህ መካከል 2055 የሚሆኑት ህፃናት ሲሆኑ 1119 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። 217ቱ አዛውንቶች ነበሩ። 1500 የሚሆኑት በፍርስራሽ ስር እንደጠፉ ናቸው፤ ከመካከላቸው 800 የሚሆኑት ህፃናት አሉ። እስካሁን ድረስ ጀናዛቸው እንኳ አልተገኘም። 15,273 የሚሆኑት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አጠቃላይ የተፈናቀሉት 1 ሚሊዮን 400 ሺህ አካባቢ ሲሆኑ፤ 685 ሺህ የሚሆኑት ከሌሎች ቤተሰቦቻቸው ጋር ተፈናቅለዋል፣ 565 ሺህ የሚሆኑት ከተባበሩት መንግስታት የስደተኞችና የእርዳታ ሥራ ኤጀንሲ (UNRWA) ጋር ግንኙነት ወዳላቸው ት/ቤቶች ተፈናቅለዋል፣ 101 ሺህ የሚሆኑት በመስጂዶች፣ በቤተ ክርስቲናትና በህዝባዊ ቦታዎች ተጠልለዋል፣ 70 የሚሆኑት በ67 ት/ቤቶች ተፈናቅለው ይገኛሉ።

ሆስፒታሎች፣ ት/ቤቶችና መጠለያ ካምፖች ሳይቀሩ ከእስራኤል የቦምብ ጥቃት ለማምለጥ ዋስትና የላቸውም። ጽዮናዊቷ የማገናዘብና የርኅራኄ ጭላንጭል ስለሌላት በየመኖሪያ ቤቱ ያለውን ስትጨርስ ወደተጠለሉበት ቦታ መሸጋገሯ የሚቀር አይመስልም። አንዳንድ አጀማመሯ ይህን ስለሚያሳይ። የምድር ጦር ልጀምር ነው እያለች በተደጋጋሚ ብትዝትም ወዳጆቿ እነ አሜሪካ ሳይቀሩ የጋዛ ሰርጥ መቀበሪያዋ እንዳይሆን ስለሰጉና ምን እንደተዘጋጀላቸው ማወቅ ስላልቻሉ እስካሁን ፈራ ተባ እያለች ነው።

የተለያዩ ሃገራት መንግስታት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ቢጠይቁም፤ አሜሪካ በጸጥታው ም/ቤት ያላትን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ተጠቅማ የፈለስጢናዊያን ጭፍጨፋ እንዲቀጥል አድርጋለች።

ምን ያክል የፈለስጢን ህፃናትና ሴቶች ተጨፍጭፈው ሲያልቁ እንደምትረካ አይታወቅም።

ሌላውም ዓለም በሰልፍ ድጋፉ እያሳዬ ቢሆንም ከዚያ የዘለለ ማድረግ አልቻለም።

በጋዛ አሁንም ቢሆን የውሃ፣ የመብራት፣ የምግብና የነዳጅ ማዕቀብ እንደተጣለ ነው። ባለፈ ብቻ 20 የሚሆኑ የጭነት መኪኖች ገብተው ነበር። ግን ለ2+ ሚሊዮን ህዝብ ምንም ማለት አይደለም። የጋዛን ሰብዓዊ ቀውስ ለመመከት በየቀኑ መቶ የጭነት መኪኖች መግባት አለባቸው።

አላህ በጥበቡ ከላይ ፈረጃውን አውርዶ ካሉበት በላእ ይገላግላቸው እንጂ እየተካሄደ ያለው ይፋዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ታሪክ የማይረሳው እጅግ አሰቃቂ እልቂት ነው።

ከዱዓእ ውጭ አቅም የለንምና ሁሌም ወንድሞቻችንን እናስታውሳቸው።

||

Send as a message
Share on my page
Share in the group