UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ያ የቁጭት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬን እንጠቀምበት

~

ሶደቃ የብዙ በላእ መመከቻ ሰበብ ነው። ለዱንያም፣ ለአኺራም፣ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ... የሚሻገር ብዙ ፋይዳዎች አሉት። መታከሚያ ያጡ ህመምተኞች፣ ዱንያ ጨልማባቸው ጎዳና ላይ የወደቁ ጎስቋሎች፣ የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሞት ሸሽተው ሜዳ ላይ የፈሰሱ ተፈናቃዮች፣ ተዘርፈው አገራቸው መግቢያ ያጡ መንገደኞች፣ ገቢ የሚያስገኝ ስራ አጥተው ሃሳብና ጭንቀት የወረሳቸው ምስኪኖች፣ ለያዙት ጨቅላ ጡት የሚሆን ነገር ያጡ አራሶች፣... በየጥጋጥጉ አሉ። በመሰል ቦታዎች ላይ ትንሽም ብትሆን የሶደቃ ድርሻ ይኑረን።

* ይህ ሲሆን ለወገን የመቆርቆር ስሜት እናዳብራለን። ይህንን ስሜትኮ ብዙዎቻችን አጥተነዋል።

* የአእምሮ ሰላም እናገኛለን። ይህንን አላህ ያደለው ብቻ ነው የሚያውቀው።

* የመስጠትን ባህሪ እያዳበርን እንሄዳለን። ሰውነት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚጎለብተው ልብም ኸይር ስራን በማዘወተር ይጎለብታል። መስጠትን ስናዘወትር መስጠት ባህሪያችን ይሆናል። ስንርቅ ከልባችን ይርቃል። ልባችንም ይደርቃል። ስለዚህ በሶደቃ ልባችንን እናክም።

* ከነገ ፀፀት ለመትረፍ ሶደቃ እናብዛ። ሰዎች በፀፀት እሳት ከሚቃጠሉባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ "ምነው ጥቂት እድሜ አግኝቼ ሶደቃ ባደረግኩ?!" የሚል ነው። ሁሉን አዋቂው ጌታ እንዲህ ይላል፦

{ وَأَنفِقُوا۟ مِن مَّا رَزَقۡنَـٰكُم مِّن قَبۡلِ أَن یَأۡتِیَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ فَیَقُولَ رَبِّ لَوۡلَاۤ أَخَّرۡتَنِیۤ إِلَىٰۤ أَجَلࣲ قَرِیبࣲ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ ٱلصَّـٰلِحِینَ }

"አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና 'ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድሆን ዘንድ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ' ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።" [አልሙናፊቁን፡ 10]

Ibnu Munewor

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ጥበበኛው ሉቅማን ረሒመሁላህ ልጃቸውን እንዲህ በማለት መከሩት፡-

‹ልጄ ሆይ! ባንተና በተስፋህ መካከል ግርዶ እስኪፈጠር ድረስ አላህን ለመፍራት ተጣጣር፡፡ ባንተና በአላህ ፍራቻ መካከል ግርዶ እስኪሆን ድረስ በአላህ ላይ ተስፋ አድርግ፡፡›

ልጅም ‹አባቴ ሆይ! እኔ ያለኝ ቀልብ አንድ ነው፡፡ በአላህ ፍራቻ ያጠመድኩት እንደሆነ ከአላህ እዝነት ተስፋ ይቆርጣል፡፡ በአላህ የእዝነት ስፋት ከጠመድኩት ደግሞ አላህን መፍራት ይተዋል፡፡› አላቸው፡፡ እርሳቸውም እንዲህ አሉት ‹አማኝ ሁለት ቀልብ እንዳለው ሆኖ ነው የሚኖረው፡፡ በአንደኛው በተከበረውና በላቀው አላህ ላይ ተስፋ ያደርጋል፤ በሌላኛው ደግሞ ይፈራዋል፡፡›

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Muhaba Ahmed shared a
Translation is not possible.

•ሞባይልና ኢንተርኔት ስንቱን ከጨዋታ ዉጪ አደረገ፣ ስንቱን አባረረ፣ ስንቱንስ ገደለ!!

~የቤት ስልክን ገደለ፣ ቴሌቭዥንን ገደለ፣ ሬዲዮን ገደለ፣ ደብዳቤን ገደለ፣ ካሜራን ገደለ፣ ሰዓትን ገደለ፣ ካሌንደርን ገደለ፣ የእጅ ባትሪን ገደለ፣ ኮምፒዩተርን ገደለ፣ ማስታወሻን ገደለ፣ እስክሪብቶ ደብተርን ገደለ፣ ጋዜጦችንና መፃሕፍትን እና መጽሄቶችን ገደለ፣

~ከዚህም በላይ ደግሞ እኛን ገደለ …ቤተሰብን ገደለ፣ ልጆችን ገደለ፣ ትምህርትን ገደለ፣ ስብሰባችንን ገደለ፣ ሹራችንን ገደለ፣ማህበራዊ ኑሯችንን ገደለ፣ ፍቅርን ገደለ፣ ትዳርን ገደለ፣ ባህል እሴታችንን ገደለ፣

~መንፈሳዊታችንን ገደለ፣ሞራላችን ገደለ፣ ሥነ-ምግባራችንን ገደለ፣ የቤተሰብ ክብርን ገደለ፡፡ ከዚያም አልፎ ዐይናችንን ገደለ፣ እንቅልፋችንን ገደለ፣ አዕምሯችንን ገደለ፣ የፊት ቆዳችንን ገደለ፣ ጀርባችንን ገደለ፣ አንገታችንን ገደለ፣ ትኩረታችንን ገደለ።

~ከሁሉ በላይ ደግሞ ጊዜያችንን ገደለ በሥርዓትና በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ገና ብዙ ነገራችንን ይገድላል፣ መጪዉን ትውልድ እርባና ቢስ ሊያደርገው ሁሉ ይችላል፡፡ ያስፈራል፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Muhaba Ahmed shared a
Translation is not possible.

ቀድሞ የሞተው ዶክተሩ ወይስ ታካሚው ???

የሚከተለውን ክስተት የተረከው በዚህ ዘመን ታዋቂው ሰባኪ ኮሎኔል ሰይድ አምሩዲን በተባለው በአሁኑ ጊዜ የካናዳ ነዋሪ ነው። ከ6,000 በላይ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች እስልምናን በሱ በኩል ተቀብለዋል።

እንዲህ ሲል ይተርካል፡- አንድ ጓደኛዬ በከፍተኛ የካንሰር ደረጃ ታሞ ለመጠየቅ ሆስፒታል ሄድኩኝ ። እዛ እያለሁ አንድ ዶክተር መጥቶ ለአንድ ሳምንት ብቻ እንደሚቆይ መጥፎ ዜና ነገረው። ከዚያም ሐኪሙ አንዳንድ መድኃኒቶችን ለተካሚው አዞ (order) ሄደ።

ዶክተሩ ደረጃውን ሲወርድ ተንሸራቶ ደረጃው ላይ ወደቀ።

ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ስለነበር በዕለቱ ህይወቱ ልታልፍ ቻለች ።

በሌላ በኩል፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ይሞታል ተብሎ ሲገመት የነበረዉ ጓደኛዬ ለተጨማሪ ሶስት ዓመታት ኖሯል!

ይህ ክስተት ሞታችን መቼ እንደሆነ የማይታወቅ መሆኑን ያሳያል።ዛሬ በዙሪያችን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ ሰምተናል ነገር ግን ሰይጣን እኔን እና አንተን/አንቺን ረጅም እድሜ የቀረን ከዚህ በኋላም ብዙ አመታትን የምንኖር አድርጎ ያዘናጋናል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Muhaba Ahmed shared a
Translation is not possible.

አላህ ሆይ! የጋዛ ነፍሶችን በችሎታህ ጠብቃቸው! አንተው በራህመትህ አውጣቸው! !!

ኃይልህንም በበደለኞች ላይ አሳርፍ!

በአይናችንም አሳየን! !!

ያ አሏሁ!!!!!! ያ አሏሁ!!!!! ያ አሏሁ!!!!

ፍልስጤም አዳሯ ይሄንን ይመስል ነበር እኛ ግን ያለ ምንም ሃሳብና ጭንቀት እያነጋን ነዉ

ቢያንስ በ ዱዓ እናግዛቸው

Send as a message
Share on my page
Share in the group