UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

የ12 አመቱ ትንሹ ሮናልዶ ፡ አባቱን አይፎን ግዛልኝ ብሎ ጠየቀው ።

የሮናልዶ መልስ ፡ አይ አሁን አይፎን አይገዛልህም የሚል ነበር ። አንተ አሁን የሚያስፈልግህ በትምህርትህ ላይ ማተኮር ፡ ከዛም የኳስ ችሎታህን ማዳበር እንጂ ፡ ስልክ ይዘህ ጊዜህን እንድታባክን አልፈልግም አለው ።

ትንሹ ሮናልዶ ፡ መጠየቁን አላቋረጠም ስልክ የምፈልገው ከአንተ ጋር ለመደዋወል ነው ።

ሮናልዶ ይህን ሲሰማ ok ከኔ ጋር ለመደዋወል ከሆነማ ፡ በርግጥም ስልክ ያስፈልግሀል ብሎ ፡ እናቱ ይይዙት የነበረውንና ፡ ከአመታት በፊት የተቀመጠውን ፡ ስማርት ያልሆነ ትንሽ ስልክ አውጥቶ ፡ ይህን ያዝና ሲምካርድ አስገብተን ትጠቀምበታለህ ብሎ ሰጠው ።

....

ለወላጆች ፡

ለታዳጊዎች ስልክ የምትሰጡ ወላጆች መቸስ በሀብት ብዛት ከሮናልዶ አትበልጡም ። ይህ ሰው ቢፈልግ ለልጁ አደለም አይፎን ሌላም መግዛት ይችላል ። ግን በቃ እንደማይጠቅመው ስላወቀ ሊገዛለት አልፈለገም ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

ውበትን መጠበቅ በትዳር ውስጥ

           አብላጫ ቁጥር ያላቸው ሴቶች ከትዳር በኋላ  ራሳቸውን ይጥላሉ። አንዳንድ ሴቶች ራሳቸውን በመጠበቅ ረገድ ከኒካህ በፊት የነበራቸው እና ከኒካህ በኋላ የሚኖራቸው ሁኔታ የሠማይና የመሬት ያህል ይለያያል። ይህ ከባድ ስህተት ብዙ ትዳሮችን የጦርነት ቀጠና አድርጓቸዋል። ወጣት ሴቶች ከትዳር በኋላ ከትዳር በፊት ከነበራቸው ልምድ በተሻለ ውበታቸውን ለመጠበቅ እና ለባሎቻቸው ዕይታ በመጉላት ላይ ብርቱ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ትዳር ውበታቸውን ከመጠበቅና ከመንከባከብ ጋር የሚለያዩበት የመሰነባበቻ ድንበር አለመሆኑን መረዳት አለባቸው። እንድያውም ትዳር ከመቼውም ግዜ በበለጠ ውበት የሚጠበቅበት፣ ለትዳር አጋር ራስን ውብ አድርጎ ለማሳየት ከፍተኛ ትኩረት የሚሠጥበት የአዲስ ህይወት መክፈቻ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። በዚህ ጉዳይ ላይ አላህን መፍራትና የባሎቻቸውን ሀቅ መጠበቅ አለባቸው። 

መልካም ሚስት ባልዋ አላህን በማይፈቅደው ፈተና ላይ እንዳይወድቅ ዐቅሟ የቻለውን ሁሉ ታደርጋለች። ዘወትር ራሷን ውብ በማድረግ ዓለሙን ሁሉ ረስቶ ዐይኖቹ በርሷ ላይ ብቻ ያጠሩ እንዲሆኑ ትተጋለች። በባልዋ ዐይን አስቃሚና ራሷን ያልጠበቀች ሆና ከመታየት የበለጠ የሚያስጠላትና የሚያስፈራት ነገር አይኖርም።

ትክክል ነው ባለቤትሽ ውብ ሁነሽ አጠገቡ ስትቀርቢ እርካታን ያገኛል። ደስታ ይሠማዋል። አላህ አንቺን ስለሠጠው አመስጋኝ ይሆናል። ይህ ሁሉ እንዳለ ሆኖ ግን ውበትሽን በመጠበቅሽ የመጀመሪያው ተጠቃሚ አንቺው ራስሽ ነሽ። ውበትሽን ስትጠብቂ ስለራስሽ ያለሽ ግምት ከፍ ያለ ይሆናል። ጥሩ ይሠማሻል። ዘወትር ውብ ለመሆን መሞከር ውብ ነገር ነው።

ብዙ ሚስቶች ከትዳር ጥቂት ወራት ቆይታ በኋላ ክብደታቸው ይጨምራል። ባል የሠውነት መገጣጠሚያቸው ለመለየት እስኪቸገር ድረስ ያለመጠን ይወፍራሉ። ራሳቸውን ለመጠበቅ የአመጋገብ ስርዓታቸውን ለማስተካከልም ሆነ በኢስላማዊ አዳብ በቤት ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ አይፈቅዱም። በአጭር ግዜ ውስጥ ባል ፍፁም ማየት የማይፈልገውን ገጽታ ይላበሳሉ። ውፍረት ውበትን ከመዋጡም በተጨማሪ ለጤና ችግር ያጋልጣል። ይህን ማወቅና መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ፀጉር የሴት ልጅ ውበት ዋነኛ  መገለጫ ነው። ከትዳር በኋላ ፀጉርሽን ብዙ ግዜ የምትታጠቢበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀርም። ይህም ስለሆነ ለፀጉርሽ የምትሰጪው አንክብካቤ ከትዳር በፊት ከነበረው ሁኔታ በብዙ መጠን መጨመር አለበት። ውሃ የሚነካው ፀጉር ብዙ እንክብካቤ ያስፈልገዋል።

አለባበስ ውበትን ያጎላል። ከባልሽ ጋር በሚኖርሽ ቆይታዎች ሁሉ አቅም በፈቀደ አለባበስሽ ዘናጭና ዓይኖቹን ከአንቺ ላይ የማያስነቅል መሆን አለበት። በቤት ውስጥ ከእርሱ ጋር ካለሽ በፍፁም ያረጁና ቆሻሻ ልብሶችን ከመልበስ ተጠንቀቂ። አዲስና ንፁህ  ልብሶች በባልሽ ፊት ካልለበስሻቸው ትርጉም የላቸውም። በቻልሽው መጠን በየግዜው አለባበስ ስልትሽን ቀያይሪ። አለባበስሽ ዘወትር አዲስ ሠው የሚመለከት ያህል እንዲሠማው የማድረግ ዐቅም ይኑረው።

ጠረን ነፍስን ያናግራል። ትዝታዎችን ይሸከማል። በባልሽ ፊት የሚኖርሽ ጠረን ልብን የሚሠረስር ጣዕም እንዲኖረው ጥረት አድርጊ። ሁልግዜ በጥሩ ሽታ ባልሽን ልትቀርቢው ይገባል። ይህን ለማሳካት በየዕለቱ መታጠብና ሽቶ መታጠን የሚያስፈልግ ከሆነ ከማድረግ ወደ ኋላ አትበይ። ሽቶሽ ግን በፍፁም ተከትሎሽ ከቤት እንዳይወጣ ጥንቃቄ አድርጊ። ውብ ጠረንሽ ማሽተት የሚፈቀድለት በአላህ ቃል የህይወት አጋርሽ የሆነው የባልሽ አፍንጫ ብቻ ነው።

በቤት ውስጥ የሚኖርሽን ጠረን ሁልግዜ ብዙም ሳትቸገሪ ጣፍጭ ሆኖ እንዲቀጥል ወጥ ቤት ስትገቢ የምትለብሺው ተለዋጭ ልብስ ማዘጋጀት ጠቃሚ ይሆናል።

ለህይወት አጋርሽ ውብና ንጹህ ለመሆን የምታደርጊውን ጥረት ሁሉ የአላህን ትዕዛዝ ለመፈጸም እንደምታደርጊው መልካም ስራ አስቢው። በእርግጥም የአላህን ውዴታ የሚያስገኝልሽ መልካም ስራ ነው። በአላህ ፈቃድ ይህ መልካም ስራሽ ጀነትን የሚያወርስሽ ምክንያት ሊሆን ይችላል። የአላህ ቸርነት ሠፊ ነው።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

የአቡ ኡበይዳ ንግግር ይተርጎም ላላችሁ ሙሉ ለሙሉ ለመተርጎም ስለሚረዝም ያነሳቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ልጥቀስላችሁ !

አቡ ኡበይዳ አላህ ስለ ጅሀድ ስለ ሶብር የሚናገረውን ካወሳ በሗላ አሏህ ታጋሾችን ይወዳልና ! በማለት ስለፅናት ካወሳ አላህንም "የሙጃሂዶችን የታጋሾችንና የፅኑዎችን ምስጋና አመሰግንሀለሁ ! " አለ ከዚያም " የአላህ ሶላትና ሰላም ሙጃሂድና ሸሂድ በሆኑት በውዱ ነብይ ላይ በቤቸሰባቸውም ላይ በባልደረቦቻቼውን የእርሳቸውን ፈለግ ተግትለው በሚታገሉ ሙጃሂዶች ላይ ሁሉ ይውረድ " በሗላ ጀግኖቹን የፍልስጤም ህዝቦች አሞገሳቸው ! አመሰገናቸው ! " እና የፅኑ የጀግና ህዝቦቻችን ልጆች ሆይ ! እናንተ በክብር በልቅና ሆናችሁ የምትታገሉ ጀግኖቻችን ሆይ ! እናንተ ተጋዳይ ፅኑዎች ሆይ ! እናንተ ግፍን አሽቀንጥራችሁ ጥላችሁ ከሀቅ ጎን የተሰለፋሁችሁ ሆይ የአላህ ሰላም ራህመቱና በረከቱም በናንተ ላይ ይስፈን አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ !! በማለት ሞቅ ያለ ኹጥባውን ጀመረ !

በመቀጠል ስላለው እልህ አስጨራሽ ትግልና ትንቅንቅ አነሳ ። የፍልስጤም ሙጃሂዶች ጠላትን ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀው እየተፋለሙት መሆኑን አሳወቀ !

በአላህ ሀይልም አንሰበርም እስከመጨረሻውም ኦንፋለማለን ወይ ከሸሂድነት ወይንም ከድል አላህ ከሁለቱ አንዱ አያሳጣንም አለ !!!

ባለፉት 3 ቀናት ብቻ 60 የወራሪዋን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች አውድመናል ! ከነዚህም ውስጥ አስሩ ብረት ለበስ የወታደር ማመላለሻዎች ናቸው ብሏል !

ሙጃሂዶቻችን የጠላትን ኢላማ እያጋዩ ነው ! ጠላቶቻችን ሲጮሁና ሲያለቅሱ የድረሱልን ጥሪ ሲያስተጋቡም እየሰማናቸው ነው ! በፍረሀት ሲርዱም እያየናቸው ነው !

ሙጃሂዶቻችን በጠላት ላይ ኦፕሬሽን እያካሔዱ ነው ። ጠላትን እያጠመዱ እየደመሰሱ መድረሻ እያሳጡት ነው ። ቅዳሜ እለት በፈፀምነው ወጥመዳዊ ጥቃት በርካታ የጠላት ሀይል ደምስሰናል ! ጠላቶቻችን ሲያለቅሱ ድረሱልን እያሉ በፍረሀት ሲጮሁ ነበር !

ጠላቶቻችን እኛን አይሰብሩንም ! በአላህ ፈቃድ ጎን እኛ እንሰባብረራቸዋለን !

ሙጃሂዶቻችን ጠላትን አደባይተው በሰላም ወደ ምሽጋቸው ይመለሳሉ ! አለረንታሲ ሆስፒታል ውስጥ መሽጎ የነበረውን የጠላት ሀይል ሲዋጋ አንድ ወንድማችን ሸሂድ ሆኗል !

በዚህ በተቀደሰው ምድር ለሚኖረው ለጀግናው ህዝባችን የምንለው ይሄ ጠላት ይሰበራል የእኛ ፍላጎት ግን አይሰበርም !

ለአላህ ብቻ እንጅ ለማንም አንበረከክም ! በህዝባችን ላይ የበረታው መከራና በደል ህዝባችንን አይጠነክረዋል ትግላችንን ያበረታዋል ! ይህ ግፍ የጠላታችን የውድቀቱ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው !

አላህም እንደዚህ ባለ ጊዜ እውነትን ተናገረ " ማስከፋትን እንጅ ፈፅሞ አይጎዷችሁም ቢዋጉዋችሁም ጀርባቸውን ያዞራሉ ከዚያም እነርሱ አይርረዱም !!

እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ ታገሱ ፅኑ በትግስትም ላይ ተረዳዱ ! አላህንም ፍሩት ነፃ ትወጡ ዘንድ ይከጀላልና ! "

በማለት የሙጃሂዶቹ ቃል አቀባይ የዛሬውን መግለጫ ቋጭቷል !

ቴሌግራም

t.me/Seidsocial

Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

መመለስ እንደምናስበው ቀላል አይደለም

የምናስበው ከባድ እንኳ ቢሆን . . .

ወይም መጀምሪያ የሆነ ያልተስተካከለ ወይም ደግሞ ልኩን ያለፈ ፍራቻ ነበረኝ ውስጤ ላይ . . .  እኔ አላውቅም ብቻ ግን ይሄ በተደጋጋሚ ወንጀል ላይ መሆኔን አውቄ  ልመለስ ስል ያለውን ስሜት ወሏሂ በምን ቋንቋ እንደምገልጸው አላውቅም በቃ ቃላት የለኝም . . . በ አንድ በኩል ከወንጀሌ   ለመመለስ ማደርገው እያንዳንዷን ጥረት እወደዋለሁ በቃ ሄደቱን ራሱ ዱአ ለማድረግ እጄን ማንሳቴ ፥መስገዴን   ። . . . በሌላ በኩል ልክ የሰራሁትን ወንጀል ማሰብና ማስተንተን ስጀመር በአለም ላይ ያሉ ሰዎች በሙሉ ንጹህ ሆነው እኔ ብቻ አሏህን እያመጽኩ  እንደሆነ ይሰማኛል በቃ የአሏህ ቁጣ በእኔ ወንጀል ምክንያት በሌሎች ላይ እንዳይወርድ እሰጋለሁ ፥

አሏህ በዚህች ምድር ላይ  ከፈጠራቸው ባሮች ከዚህ በፊትም ከነበሩ ህዝቦች እንደኔ የታገሰው ሰው በምድር ላይ ያለ አይመስለኝም ። በጥበቡ ብቻ ወንጀሌን ከዛሬ ነገ ትመለሳለች ብሎ ይመለከተኛል ።ምንም አያረገኝም ። በቃ ልክ ጌታየ ይቅር በለኝ ብየ እጄን ሳነሳ ሚታየኝ የኔ ወንጀል ክብደት ነው አሏህን በቀን በለሊት ያመጽኩት ነው ሚመጣብኝ ፡ምንም ሳያጎልብኝ ባበላኝ ባጠጣኝ እኔ እሱን ያለገደብ ድንበሩን መጣሴ ነው ትዝ ሚለኝ . . . አእምሮየ ላይ ሚመላለሰው እስካሁን በዚህ ወንጀሌ አሏህ እንዴት አላጠፋኝም ሚለው ነው ። የምር የአሏህ ቻይነት ግርም ይለኛል ።

. . . እጄን ሳነሳ እንባየም ብን ብሎ ይጠፋል ።አላውቅም የታባቱ እንደሚሄድ አእምሮየ ውስጥ ተደብቆ የኔን ደካማነትና የማልረባ መሆኔን እንደኔ በወንጀል የተጨማለቀ ሰው እንደሌለ ይነግረኛል ። ልቤም ይህንኑ ነው ሚለኝ ማይሆን ስሜት ይሰማኛል

ጌታየን ሚያስደስቱ ለይል እየሰገዱ ቀን ሚጾሙና በኢባዳ ሚያሳልፉ ምርጥ ሰዎች ስለመኖራቸው ዛሬም አልጠራጠርም ። ታዲያ እኒህ የአሏህ ባርያዎች ባሉበት ምድር እነዛ ነብያችንን የተከተሉ ሰሀቦችን ባሳለፈች መሬት . . . ዛሬ እኔ ተፈጥሬ ምድርን በኔ ወንጀል ብቻ አብቃቃታለው የኔ ወንጀል ለሁሉም፡ሰዎች ቢከፋፈል ሚያብቃቃቸው ይመስለኛል ።

ያቺ በነብዩ ዘመን ዚና ሰርታ ነብያችንን ተቀጥቅጬ ይግደሉኝ ስትል የነበረችና ልጇን ከወደለች ቡሃላ ተቀጥቅጣ ስትገደል ደሟ ኻሊድን ሲነካው ኻሊድም በወንጀሏ ሲያነውራት  ነብያችን እንዲህ ነበር ያሉት "ኻሊድ ሆይ የእሷ ተውበት እኮ ለሁሉም ቢከፋፈል ለሁሉም ያብቃቃዋል" (hadisun ketesasatku armign )

እንደተባለላት ሴት እኔ ደግሞ ዛሬ የእሷን ተቃራኒ ሆኜ

የ እሷ ተውበት ሁሉንም ሲያብቃቃ

የኔ ወንጀል ለሁሉም ይተርፋል ፤

ከወንጀል ያብቃቃቸዋል ።

ታዲያ ይሄን ያህል ልዩነት ኖሮን ጌታየ ይቅር ይለኝ ይሆን ?

የወንጀሌ ክፋት  ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ከቶኝ የመመለሻ በሩን እንዳላይ እንዳልደርስበት አርጎኛል ። እና ደግሞ ወደጌታየ መመለስን ሳስብ በፊት ላይ የነበርኩበትን ትንሽየ የኢማን ጥፍትና ያስታውሰኛል ግን መመለስ አለመቻሌ ደግሞ እንደ እግር እሳት ያቃጥለኛል . . . አንዳንዴ ሳስበው ያቺን ትንሿን ጥፍጥና ሁሌም እንደናፈኳት ምኖር ይመስለኛል  ወይም ደግሞ ምን አልባት ከዚህ የባሰ ሀል ውስጥ ገብቼ ጭራሽ ምንም እንዳላስታውስም እሆን ይሆናል ።

ልቤ ግን ሁሌም መመለስን ይፈልጋል የምር የሆነ የቀልብ ሰኪናን . . .  አሏህ ግን ለምንድነው የሰዎችን የኢማን ደረጃ ሚለያየው ? ሁሉንም ባሮቹን ለእሱ ተገዢ ማረግ ሲችል ለምን ግን ? ሚያምጹትንም ፈጠረ ?

ለምን እንደሆነ እኔም አይገባኝም

ምልሹን ለእናንተ ትቻለው

እኔኮ ሚገርመኝ ሶሀቦች የነበሩበት ዘመን እና የእኛ ዘመን ይሄን ያህል ልዩነት መፍጠሩ ነው ።

ግን ለኸይሩ ነው?

.

.

.

ወደ መጀምሪያየ ስመለስ

የዱአየ መጀመሪያ

እጄን ስዘረጋ እኒህ ያልኳችሁ ሁሉ ይመጡብኛል ።

የዱአየ መካከል

ዝብርቅርቅ ያለ የጥፋተኝነት ፥ የወንጀለኝነት . . . ስሜት ይሰማኛል ። ከዛ ደግሞ ትንሽ ወደኋላ ተመልሼ ከወንጀላቸው የተመለሱ እነዚያ ድንቅ ባሮችን አስታውሳለው . . . ከሁሉም ተመላሾች ግን ሚገርመኝ 100 ሰዎችን ገድሎ ከዛም ወደ አሏህ ተመልሶ ጌታው ተውበትን የተቀበለውን ባርያ

እኔ ምለው ግን ምን አይነት ተውበትን ቢያደርግ ነው ? ምን ያህል አሏህን ፈርቶ ቢጸጸት ነው ጀነትን ያገኘው ?

የዚህን ባርያ ተውበት ሳይ ትንሽ ልቤ ትረጋጋለች ጌታየ ምንም ወንጀል ብሰራ እስከተመለስኩ ድረስ ይቅር እንደሚለኝ ይሰማኛል ።እሱን ይቅር ያለ ጌታ እኔን ይለኛል ሚል ተስፋ ይኖረኛል ።

ተስፋየ ግን እንዳለ ሆኖ እንዴት ነው መመለስ ምችለው ነው ትልቁ ጥያቄ ? ? 

የዱአየ መዝጊያ

የሰውየውን ታሪክ አስታውስሼ ጌታየን ማረኝ ብየ በትንሽ ተስፋ ዱአየን እቋጫለው ። ከዛም ልቤ ትንሽ መረጋጋትን ታገኛለች

. . . . . . . . . . . . . . . . . . . .

እና ግን ሚያናድድነውና ድጋሚ ራሴን ምወቅሰው እዛ ወንጀል ላይ ስመለስ እንደውም ከነበረኝ ብሶብኝ ራሴን አገኘዋለው ።

ይሄ ቆይ ምን ይባላል e

እያሾፍኩ ? 

ብሞትስ ?

ብሞትስ ብየም አስባለው ሚገርመው ሁሌም ወንጀል ስሰራ ብሞትስ ብየ ማስበው  ግን ምንም አይነት ስሜት አይሰማኝም ብሞትም ሞትኩ ነው ብየ አቀለዋለው እናም ይሄን ማሰቤ ወንጀልን ከመስርት አይገድበኝም ። ይልቁንም አሏህ ባለ ቀን ለመመለስ እጄን ስዘረጋ ያኔ ወንጀል ውስጥ እያለሁ ብሞት ኖሮስ ንየ አስብና ፍርሃት ሀዘን ይወረኛል እዛ ወንጀል ላይ ድጋሚ እንዳልገኝ ልቤ ይነግረኛል

በመጨረሻም

ይሄንኑ ሂደት እየደጋገምኩ እቀጥላለው. . .

ወይ አልመለስ ወይ ወንጀለኛ አልሆን  ወጣ ገባ እላለው

Send as a message
Share on my page
Share in the group