ቀድሞ የሞተው ዶክተሩ ወይስ ታካሚው ???

የሚከተለውን ክስተት የተረከው በዚህ ዘመን ታዋቂው ሰባኪ ኮሎኔል ሰይድ አምሩዲን በተባለው በአሁኑ ጊዜ የካናዳ ነዋሪ ነው። ከ6,000 በላይ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች እስልምናን በሱ በኩል ተቀብለዋል።

እንዲህ ሲል ይተርካል፡- አንድ ጓደኛዬ በከፍተኛ የካንሰር ደረጃ ታሞ ለመጠየቅ ሆስፒታል ሄድኩኝ ። እዛ እያለሁ አንድ ዶክተር መጥቶ ለአንድ ሳምንት ብቻ እንደሚቆይ መጥፎ ዜና ነገረው። ከዚያም ሐኪሙ አንዳንድ መድኃኒቶችን ለተካሚው አዞ (order) ሄደ።

ዶክተሩ ደረጃውን ሲወርድ ተንሸራቶ ደረጃው ላይ ወደቀ።

ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ስለነበር በዕለቱ ህይወቱ ልታልፍ ቻለች ።

በሌላ በኩል፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ይሞታል ተብሎ ሲገመት የነበረዉ ጓደኛዬ ለተጨማሪ ሶስት ዓመታት ኖሯል!

ይህ ክስተት ሞታችን መቼ እንደሆነ የማይታወቅ መሆኑን ያሳያል።ዛሬ በዙሪያችን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ ሰምተናል ነገር ግን ሰይጣን እኔን እና አንተን/አንቺን ረጅም እድሜ የቀረን ከዚህ በኋላም ብዙ አመታትን የምንኖር አድርጎ ያዘናጋናል።

image
Mesaj olarak gönder
Sayfamda paylaş
Grupta paylaş