Translation is not possible.

ዐብዱላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱም «ዐይነበሲር» የሆነ ሰሃባ ነበር ። የእናታችን ኸዲጃ  (ረዐ) የየሹማዋ ልጅ ነው።በኢስላም ትልቅ ደረጃ ካላቸው ሰሃቦች ውስጥ ሲሆን ማየት የማይችል በመሆኑ የጂሃድ ግዳጅ የተነሳለት ነበር።

የአላህ መልእክተኛ( ሰዐወ) ለዘመቻ ሲወጡ እርሱን መዲናን እንዲያስተዳድር ወክለውት ይሄዱ ነበር።

በዑመር ኢብኑልኸጣብ ዘመን ፋርሳውያንን ለመዝመት ዑመር አወጁ።ሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስንም አሚር አደረጉት። ኢብኑ ኡሚ መክቱም ዑዝር ያለው ሰው ሆኖ ሳለ ነገር ግን ከመዲና ወደ ዒራቅ ቃዲሲያ ላይ ለመሳተፍ ተጓዘ።

አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዐ)እንዲህ ይላል፦ የቃዲሲያ ጦርነት ላይ ማየት የተሳነውን ዐብዱላህ ኢብኑ ኡሚ መክቱምን ተመለከትኩት።የጦር ልብስ ለብሶ ጫፎቹ ይጎተታሉ።በእጁም ጥቁር ባንድራ ይዟል ።

«አላህ ያንተን ዑዝር አንቀፅ አውርዶበት የለ?» ተብሎ ተጠየቀ።እሱም «አዎ!  ነገር ግን እኔ ራሴን በማስገኘት የሙስሊሞችን ቁጥር ለማብዛት አስቤ ነው !አላቸው።»

(ተፍሲሩል ቁርጡቢይ)

ኢማሙ ዘሀቢይ ይህ ታላቅ ሰሃባ በዚሁ ቃዲሲያ ላይ ሸሂድ እንደሆነ ያትታሉ። የሙስሊሞች ቁጥር በዛ ከተባለ ከ7000 በላይ ሲሆን የካሀዲያን ቁጥር ደግሞ 40,000 ወይም 60,000 ነበር ተብሏል።

የረሱል ሙአዚን ረዲየላሁ ዐንሁ ወአርዳሁ!

የቴሌግራም ቻናል ፦ ismaiilnuru!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group