UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

🌹ሶብር🌹

👉ትግስት የዚህ አለም ሀብት የመጭው አለም ስኬት ናት። አላህ ለታጋሾች ትልቅ ስጦታን ሰጣቸዋ በገነትም አበሰራቸው።

وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَيْءٍ مِّنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنفُسِ وَالثَّمَرَاتِ ۗ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ

ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር፡፡

'👉'ትግስት ከኢባዳዎች አንዱና ምንዳውም የላቀ ነው። አላህ ትእግስትን ከሶላት ጋር አብሮ በማቆራኘት ጠቅሶታል።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡ አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡

الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَالصَّابِرِينَ عَلَىٰ مَا أَصَابَهُمْ وَالْمُقِيمِي الصَّلَاةِ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ

እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን፣ በደረሰባቸውም (መከራ) ላይ ታጋሾችን፣ ሶላትንም አስተካክለው ሰጋጆችን፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱትን (አብስር)፡፡

'👉'ሳትፈተንና መከራን ሳትቀምስ ጀነትን የምታገኝ መሰለህን? አስታውስ! ጀነት ለነዚያ መከራና ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ እንዲህ ለሚሉት ናት፦

👉''ብልህ ሰው ከችግርና መከራ ትምህርት ይወስዳል፣ ነገሮች ቢከብዱም ጌታውን  ያመሰግናል።

👉ታላቁ የትዕግስት መምህር ነብያችን ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም ከፍ ባለ ድምፅ እዲህ ነበር ያሉት፦ "አዋጅ! የአላህ ሸቀጥ እጅግ ውድ ናት፣ የአላህ ሸቀጥ እርሷ ጀነት ናት። "

👉*እናም ችግርና መከራ ቢደራረብብህ አትዘን ተስፋ አትቁረጥም.... አላህ ምን እዳዘጋጀልህ አታውቅምና ታጋሽና አመስጋኝም ሁን

🌹وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ 🌹

👉ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡

'' አላህ ከታጋሾች ጋር መሆኑን አትርሳ።

إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

👉 አላህ (በእርዳታው) ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የቱንም ያክል የተመቻቸ ህይወት እኖራለሁ ብለህ ብትገምት ዱንያ ግን ለማንም ቢሆን ሙሉ ምቾትን አትሰጥም።

የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዳሉት “ትክክለኛ ኑሮ ማለት የአኼራ ኑሮ ነው።” ስለዚህ ሙሉውን እና እውነተኛውን ምቾት የሚሻ ሁሉ ለጀነት ይታገል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🇵🇸🇵🇸🇵🇸ሩቅ አይደለም!!🇵🇸🇵🇸🇵🇸

💫ነብዩ ኢብራሂምﷺ እጅ እና እግራቸው ጠፍረው እሳት ውስጥ የወረወሯቸው ሰዎች በዝያች ቅፅበት አላህ አላጠፋቸውም?!

💫ፊርዓውን "እኔ ጌታችሁ ነኝ" እያለ ያልተቀበሉት ሰዎች ሰውነታቸው ቆራርጦ ሰቅሎ እየገደለ ሲያሰቃያቸው በዝያች ቅፅበት አላህ አላጠፋውም?!

💫አላህ ከሰማይ መልእክት እያወረደላቸው "ጌታችሁ አላህ ነው, ተገዙት" ያሉ ነብያቶች የገደሉ ሙጅሪሞች አላህ በዝያች ቅፅበት አላጠፋቸውም?!

💫"ጌታችን አላህ ነው, በእሱም አምነናል።" በማለታቸው ብቻ ጎድጓድ ቆፍረው እሳት አንድደው ያቃጠሏቸው “አስሀብ አል_ኡኽዱድ” አላህ በዝያች ቅፅበት አላጠፋቸውም?!

💫ለዓለማት እዝነት ተደርገው የተላኩት ውዱ ነብይﷺ ጀርባ ላይ ፈርስ እየጣሉ፣ በተደጋጋሚም የግድያ ሙከራ ያደረጉ ሙጅሪሞች አላህ በዝያች ቅፅበት አላጠፋቸውም?!

💫አላህ ከፈጠረው ሁሉ በላጭና ክቡር የሆኑት ነብዩﷺን ጦር ሜዳ ላይ ገጥመው ጭንቅላታቸው እስኪደማ የተዋጉዋቸው ሙጅሪሞች አላህ በዝያች ቅፅበት አላጠፋቸውም?!

💫ቀራሚጣዎች ጀናዛ የያዙ አስመስለው ሰይፋቸው በከፈን ሸፍነው ወደ ኻረም ካስገቡ በኋላ በአንድ ጀምበር ብቻ ከሶስት ሺህ (3000) በላይ ሑጃጆች ገድለው፣ የዘምዘም ውሃ በሑጃጆች ጀናዛ ደፍነው፣ የተከበረው የካዕባ ሽፋን በጣጥሰው፣ መሪያቸው ከፍታ ላይ ቆሞ “የዛሬው ንግስና ለማን ነው?” እያለ ሲፎክር፣ “ጠይረል አባቢል የት አሉ? ሂጃራ ሚን ሲጂል የት አለች?” እያለ ሲፎክር፣ ሱረቱል ቁረይሽ እየቀራ “ከፍራቻ ሰላም ሰጣቸው ይላል ከእኛ ፍራቻ ግን ሰላም አልሰጣቸውም” እያለ ሲያላግጥ፣  ሀጀረል አስወድን ቀምተው ወደ ሀገራቸው ወስደው ሲጫወቱበት አላህ በዝያች ቅፅበት አላጠፋቸውም?!

   ከጌታህ ሊያመልጥ የሚችል የለም ወዳጄ……

   የቁድስን ክብር አዋርደው፣ የሙስሊሞች ሀገር ቀምተው፣ ሴቶችና ህፃናት ጨፍጭፈው...........እንዲሁ የሚተዉ ይመስልሀል!?

ወላሂ አይተዋቸውም‼️

ቅጣታቸው የበለጠ አሳማሚ እንዲሆን አመፃቸው እንዲበዛ፣አላህ የያዘላቸው ቀጠሮ እስከ ሚደርስ አላህ የፈለገው ጥበብ እስኪሟላ ያቆያቸዋል እንጂ ቅርብ ነው ሩቅ እንዳይመስልህ!!

 

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አሠላሙ አሊኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
ام ريان ام ريان Changed her profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group