Translation is not possible.
◾️ጀነተል ፊርደውስ የሚወርሱ ሙእሚኖች
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
 
✅ قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ
➡️ ሙእሚኖች ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡
 
✅ الَّذِينَ هُمْ فِي صَلَاتِهِمْ خَاشِعُونَ
➡️ እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች፡፡
 
✅ وَالَّذِينَ هُمْ عَنِ اللَّغْوِ مُعْرِضُونَ
➡️ እነዚያም እነርሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች፡፡
 
✅ وَالَّذِينَ هُمْ لِلزَّكَاةِ فَاعِلُونَ
➡️ እነዚያም እነርሱ ዘካን ሰጭዎች፡፡
 
✅ وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ
➡️ እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት፡፡
 
✅ إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ
➡️ በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ ላይ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡
 
✅ فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ
➡️ ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው፡፡
 
✅ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
➡️ እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውና ቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች፡፡
 
✅ وَالَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَوَاتِهِمْ يُحَافِظُونَ
➡️ እነዚያም እነሱ በስግደቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁ የኸኑት፡፡
 
✅ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْوَارِثُونَ
➡️ እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው፡፡
 
✅ الَّذِينَ يَرِثُونَ الْفِرْدَوْسَ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ
➡️ እነዚያ (ጀነተል) ፊርደውስን የሚወርሱ ናቸው፡፡ እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
 
📚(ሱረቱ አል-ሙእሚኑን 1 - 11)
                    
Send as a message
Share on my page
Share in the group