UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ነቢያችን عليه الصلاة والسلام እንዲህ ብለዋል

የትም ብትሆን አላህን ፍራ !

በመጥፎዋ (ስራህ ) ላይ መልካሟን አስከትል - (መጥፎዋን ) ታብሳታለችና ።

ሰዎችን በመልካም ባህሪ ተኗኗራቸው

https://t.me/Muhammedsirage

Telegram: Contact @Muhammedsirage

Telegram: Contact @Muhammedsirage

اتق الله حيثما كنت
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ዓሊሟ በዱቤ የሚታከምባት ኡማ!

▪️ ለሸይኽ ዐብዱለጢፍ እስካሁን የተሰበሰበው ብር 499,000 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሽ) ብር ነው። አጠቃላይ የሚፈለገው $8500 (ስምንት ሽ አምስት መቶ የአሜሪካን ዶላር ) ነው። ይህ ማለት 1,037,000 (አንድ ሚሊዮን ሰላሳ ሰባት ሽህ) የኢትዮጲያ ብር ገደማ ነው። ከዚህ ላይ ግማሹን እንኳን መሰብሰብ አልተቻለም!!

▪️ ሸይኻችን ከእስር ቤት ሲወጡ በስጦታ የተበረከተላቸው መኪና ይሸጥ ቢሉም እያሰባሰቡ ያሉ ሽማግሌዎች በጭራሽ እኛ ሙስሊሙን ይዘን አሰባስበን እንከፍላለን እንጅ መኪናው አይሸጥም በማለት የህዝቡን ትብብር እየጠበቁ ነው!

▪️ ጉዳዩ እንዲህ ነው ፦ ህመሙ ወደ ካንሰር የመለወጥ እድል የነበረው እጢ በመሆኑ እናሳክማችሁ ብለው ወደ ቱርክ የወሰዷቸው ወንድምና እህቶች ከህዝቡ ሰብስበን እንከፍላለን በሚል መተማመን ከሰዎች በብድር አንስተው ነበር የከፈሉት።

▪️ መጀመሪያ $4000 የተገመተ ህክምና ኋላ ላይ $7500 ተጨማሪ ተጠየቀበት። ይህ ሁሉ ሲሆን ሸይኻችን አያውቁም ነበር። ከዚያ የተወሰኑ ቅርብ ሰዎች ጉዳዩን ሲነግሯቸው ነበር «መኪናዬ ይሸጥ» የሚል ሀሳብ ያመጡት ።

ይህም ጠቅላላ ህክምናው $11,500 ዶላር ሲሆን $2500ው በወንድሞች ስለተከፈለ ለህዝብ የተጠየቀው $8500ው ብቻ ነው። የአንድ መርፌ ዋጋ $300 (36,600 ብር ) ሆኖ ህክምናው እንደቀጠለ ነው። መርፌውም የሚቆም ሳይሆን በየ3ወሩ የሚቀጥል ነው።

▪️ ወደርሳቸው አካውንት ገቢ እንዳይደረግ የተደረገውም በዚሁ ምክንያት ብቻ ነው። ከአካውንትህ አውጣና ዱቤ ክፈል እንዴት ይባላል? ለሸይኽ አይደለም ለተርታ ሰውስ ነውር አይደለም? ስለሆነም በኮሚቴ አካውንት እንዲሰበሰብ ተወሰነ።

▪️ አሰባሳቢ ኮሚቴዎቹ በእምነታቸው ድፍን የሰንበቴ ከተማ ነዋሪ የሚመስክርላቸው ዓሊሞችና ሽማግሌዎች እንዲሁም የሸይኹ የቅርብ ጓደኞች ናቸው።

ስለሆነም ሙስሊሙ ኡማ ይህንን ተገንዝቦ «ሀብታሞች ገቢ ያደርጋሉ» ብለን ሳንዘናጋ ትንሽም ብትሆን ሁሉም የራሱን ገቢ እያደረገ ሸይኻችንን እናሳክም!

የከሸፍን ትውልዶች ሆነን እንጅ ወላሂ በዚህ መልክ ለሸይኻችን ስፅፍ ክብራቸውን ዝቅ ያደረግኩ እየመሰለኝ ነው!

የንግድ ባንክ አካውንት ፦

1000392652788

የአካውንት ስም ፦

YEJILE TIMUGA W/COMMUNITY SUPPORT

(የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚዩኒቲ ሰፖርት)

አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ፦

1) ሸኽ ጡሃ ሸኽ መሀመድ

2) ሸኽ ሁሴን ሀሰን ሱሩር

3) ሸኽ አህመድ አሊ ሃሰን

ሼር ማድረግም ትብብር መሆኑ አይዘንጋ!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

➫አንድ ሂጃብ ማሟላት ያለባቸው ነገሮች 👇

ወፍራም መሆን አለበት ስስ መሆን የለበትም።

ሙሉ ሰውነቷን መሸፈን አለባት ።

ሰፊ መሆን አለበት ጠባብ መሆን የለበትም።

የተጋጌጠና የተሸበራረቀ መሆን የለበትም።

የ Non Muslims ልብስ መምሰል የለበትም።

የታጠነና ሽቶ የተቀባ መሆን የለበትም።

ለመታወቅ(ፋሽን መሆን) የለበትም።

የወንድ ልብስ መምሰል የለበትም።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አንድ አባት ሴት ልጁን ውድ በሆነ ሆቴል ራት ጋበዛት....

ከሆቴሉ ባልተቤት ጋር በመነጋገር  ከፊት ለፊታቸው የተለያዩ  ያማሩና ጣፍጭ ምግቦች እንዲያስቀምጥ ነገረው ።

ከትንሽ ደይቃ ብኋላ የሆቴሉ ባልተቤት የተለያዩ ጣፍጭ ምግቦችንና

የተሸፈነ ምግብ ይዞ መጣ..

ልጂቱም ከፊት ለፊቶ የተቀመጡትን ምግቦች

መመልከት ጀመረች  በእቃ የተሸፈነው  ምግብ

ይበልጥ ሳባትና ልትከፍተው ስትል አባቷ ከለከላት ....!

አባቷም ከፊት ለፊትሽ በርካታ ጣፍጭና የሚያማምሩ ምግቦች እያሉ የተሸፈነውን ለምን መክፈት ፈለግሽ ሲል ጠየቃት...?

ልጂቱም የተሸፈነ ስለሆነ በውስጥ ያለው ያማረና የተሻለ ጥፍጥና ይኖረዋል  ብየ ስላሰብኩ ነው ስትል መለሰች ...

አባቷም ፈገግ አለና እንዲህ አላት

በሒጃብ ለምን እንደምሸፍንሽ አወቅሽ!

ልጂቱም ወደ መሬት እየተመለከተች አባቷ ያላት ገባት !

ከዛ ብኋላ ምርጥ የተሸፈነ ምግብ ሆነች!

ሒጃብ ነገራቶች ለማክበድ ሳይሆን በአጭሩ

መደበቅ ያለበት ተደብቆ ማየት ያለበት እንዲያይ ነው ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የተዋለልህን ፀጋ እንድታመሰግን…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿انْظُرُوا إِلَى مَنْ أَسْفَلَ مِنْكُمْ، وَلَا تَنْظُرُوا إِلَى مَنْ هُوَ فَوْقَكُمْ ؛ فَهُوَ أَجْدَرُ أَنْ لَا تَزْدَرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ﴾

“በዱኒያ ጉዳይ ከበታቻችሁ ያሉትን ተመልከቱ። ከበላያችሁ ያሉትን አትመልከቱ። ከበታቻችሁ ያሉትን መመልከት የተሻለ ነው። ያን ግዜ አላህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ ለመመልከት ያግዛችኋልና።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2963

ኢብኑ ሀዝም (رحمه ﷲ) እንዲህ ይላሉ፦

“በገንዘብ በሀብት በጤንነት ነገሮች ላይ ከበታችህ ያሉትን ተመልከት። በዲን፣ በእውቀትና በመልካም ስራ ከበላይህ ያሉትን ተመልከት።”

📚 አልአኽላቅ ወልየሲር: 23

✅ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

🌐፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

😔፦ https://bit.ly/486xnrS

🌐፦ https://bit.ly/41zEZkk

🌐፦ https://bit.ly/4arMbTx

🌐፦ https://bit.ly/41tIUPv

🌐፦ https://bit.ly/41yPkNg

Telegram: Contact @BuhariMuslimAmharic

Telegram: Contact @BuhariMuslimAmharic

በቡኻሪና ሙስሊም ሳይገደብ በሌሎች የሐዲስ ሊቃውንቶች የተዘገቡ ነቢያዊ ሀዲሶችም ይቀርቡበታል። ጆይን፦ https://t.me/BuhariMuslimAmharic
Send as a message
Share on my page
Share in the group