UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

  ረሱል ﷺ 12 ሚስቶች የነበሯቸው ሲሆን አስራ ሁለቱም የመላው ሙስሊሞች እናት በመባል ይታወቃሉ። እነሱም

1፦ ከዲጃ ቢንቱ ኹወይሊድ

2፦ ሰውዳ ቢንቱ ዘምዓ

3፦ ዓኢሻ ቢንቱ አቢ በክር

4፦ ሓፍሳ ቢንቱ ዑመር

5፦ ዘይነብ ቢንት ኩዘይማ

6፦ ሂንድ ቢንቱ አቢ አመያ

7፦ ዘይነብ ቢንቱ ጃሕሽ

8፦ ጁወይሪያ ቢንቱል ሓሪስ

9፦ ማሪያ ቢንቱ ሸምዑን (አልቂብጢያ)

10፦ ረምላ ቢንቱ አቢ ሱፍያን

11፦ሰፊያ ቢንቱ ሑየይ

12፦ መይሙና ቢንቱል ሓሪስ ሪድዋኑላሂ አለይሂም

ሀቢቡል ሙስጠፋ ነብዩና ሙሀመድ ﷺ ከነዚህ እናቶቻችን መካከል ከኸዲጃ ረ.ዐንሃ እና ከማሪያ ረ.ዐንሃ ብቻ ልጅ ያገኙ ሲሆን ኸዲጃ ረ.ዐንሃ የሚከተሉትን ልጆች ወልዳላቸዋለች።

1፦ ዐብዱላህ

2፦ ቃሲም

3፦ ዘይነብ

4፦ ሩቀያ

5፦ ኡሙ ኩልሱም

6፦ ፋጢማ

ማሪየቱል ቂብጢያ ረ.ዐንሃ ደግሞ 

1፦ ኢብራሂም ወልዳለች

ረሱል ﷺ 8 የልጅ ልጆች የነበሯቸው ሲሆን አምስቱ የፋጢማ ረ.ዐንሃ ሁለቱ የዘይነብ ረ.ዐንሃ እና አንዱ የሩቀያ ረ.ዐንሃ ነው።

የፋጢመቱ ዘህራ ረ.ዐንሃ

1፦ ሀሰን

2፦ ሁሰይን

3፦ ሙህሲን

4፦ ኡሙ ኩልሱም

5፦ ዘይነብ

የዘይነብ ረ.ዐንሃ ልጆች፦

1፦ ዐሊይ

2፦ ኡማማ

የሩቀያ ልጅ፦

1፦ ዐብዱላህ

አብዝኃኛዎቹ የልጅ ልጆቻቸው በጨቅላ እድሜያቸው የሞቱ ሲሆን የረሱል ﷺዝርያዎች በፋጢመቱ ዘህራ ረ.ዐንሃ ልጆች በኩል ሊስፋፋ ችሏል።   عليه  افضل الصلاواة ربي وسلامه عليه

አላህ በጀነት ከነርሱ ጋር ይሰብስበን 🤲

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሴት ልጅ በደደቦች ሸሪዓ እና

በነቢያቶች ሸሪዓ

⚡️በየ መድረኩ መዝፈንን ሀላል አደረጉላት፣

አላህ ግን አዛን፣ ኢቃማና አሚን በማለት ድምጿን ከፍ ከማድረግ ከልክሏታል።

⚡በሲኒማ ቤቶች እና በመድረክ ላይ እንድትሰራ ፈቀዱላት አላህም የጁምአ ሰላት እና የጀመዓ ሰላትን በሷ ላይ ግዴታ እንዳይሆን አድርጓል ።

🩸የኦሎምፒክ እና የማራቶን ሻምፒዮን አደረጓት አላህ ግን በሁለቱ ምልክቶች መካከል በሰፍዋና እና በመርዋ መካከል እንዳትሮጥ የከለከላት ጨዋነቷን እና ንፅህናዋን ለመጠበቅ ነው።

⚡በቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅቶች እና ሌሎችም ደንበኞችን ለመሳብ በድምፅዋ ጥሪን በመመለስ ላይ በኤሌክትሮኒክስ ማስታወቂያ ተጠቅመውባታል።

አላህ ግን በሶላት ላይ ኢማሙ ቢሳሳት እንኳ ከማጨብጨብ ውጪ ድምፃን ከፍ አድርጋ" ሱብሃነላህ" በማለት ድምፃን ከማሰማት ከልክሏታል።

🩸በመዝናኛ ጉዞ ላይ ያለ መህራም( ያለ ወንድ ቤተሰብ) እንድትጓዝ አደረጓት።

አላህ ከእርሷ ላይ አንድ መህረም ካላገኘች ከእስልምና ማእዘን ውስጥ የሆነውን ሀጅን እንኳን አውርዶላታል።

⚡️የስፖርት ቡድኖችን ለማበረታታት እና ለመደገፍ ወሰዷት፤ አላህም ለጂሃድ ሃይማኖትን ለመደገፍ እንዳትወጣ ከልክሏታል።

🩸ከቤቷ ሽቶ የተቀባች፣ የተዋበች ውበቷን ለአደባባይ የገለፅች ሆና እንድትወጣ አደረጓት ።

አላህ ግን በእግሮቿ ላይ ያደረገችውን ጌጥ ለሰዎች ይሰማ ዘንድ መሬትን በእግሮቿ እየደበደበች እንዳትሄድ ከልክሏታል።

✍ ከሸይኽ አብድገንይ ገፅ ተወስዶ የተተረጎመ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/AbuEkrima

Telegram: Contact @AbuEkrima

Telegram: Contact @AbuEkrima

ይህ ቻናል የተለያዩ አስተማሪና አነቃቂ የሆኑ ትምህሮችን፣ ሙሃደራዎችን፣ የቀደምት አኢማዎችን ንግግሮች እንዲሁም የተለያዩ በጊዜያችን ያሉትን የሱና ዑለማዎች ፈትዋና ንግግር የምናቀርብበት ቻናል ነው።
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#ዊትር #ሰላት ‼ ❶ ትርጉሙ

➠ ዊትር (وتر) የሚለው ቃል ጎዶሎ ቁጥር (odd) እንደማለት ነው ለምሳሌ 1; 3; 5; 7... የመሳሰሉ ቁጥሮች ዊትር ሲባሉ 2;4 ;6... የመሳሰሉ ቁጥሮች ደግሞ ሸፍእ (شفع) ይባላሉ

➠ በመሆኑም የዊትር ሰላት ማለትበነዚህ ጎዶሎ ቁጥሮች የሚያበቃ ሰላት ማለት ነው።

❷ ግዴታ ነው ወይስ ሱና ?

➠ ሀነፍዮች ዊትር ግዴታ ነው ይላሉ ነገር ግን ከማስረጃ አንፃር ስናየው ዊትር ግዴታ እንዳልሆነና ነገር ግን በጣም የጠነከረ ሱና የተወደደ ተግባር መሆኑን እንረዳለን።የአብዛኛዎቹ ኡለሞች አቋምም ይህ ነው

➠ ግዴታ እንዳልሆነ ከሚጠቁሙ ማስረጃዎች መሀከል የአሏህ መልእክተኛ ﷺ ግዴታ የሆኑ ሰላቶችን በሚያስተምሩባቸው አጋጣሚዎች አምስት ወቅት ሰላትን ሲጠቅሱ ዊትርን ግን አለመጥቀሳቸው ነው።

➠ ግዴታ ባይሆንም ግን በጣም የጠነከረ ሱና ነውና አንድ ሰው ሊተወው አይገባም።

ኢማም አህመድ እንዲህ ይላሉ፦

" ዊትርን ሰላትን የተወ ሰው መጥፎ ሰው ነው ምስክርነቱን ሊቀበሉት አይገባም "

❸ የሚሰገድበት ወቅት

➠ የዊትር ሰላት የሚሰገደው ከኢሻ ሰላት በሗላ ጀምሮ ሱብሒ አዛን እስኪል ድረስ ባለው ወቅት ነው።

ማስረጃውም የአሏህ መልእክተኛﷺ እንዲህ ማለታቸው ነው።

((አሏህ በዊትር ሰላት አቆያቹ አሏህ ከሰላተል ኢሻ ፈጅር እስኪወጣ ድረስ አደረገላችሁ)) 📚ቲርሚዚ 425

❹ በላጩ ማዘግየት ነው ወይስ በጊዜ መስገድ?

➠ ለሊት እነሳለሁ ብሎ ለሚል ሰው ወደ ለሊቱ ማብቂያ ማዘግየቱ ይወደድለታል።

➠ ለሊት ላይ መነሳት ለሚከብደው ሰው ግን ሳይተኛ በፊት ዊትር መስገዱ ይወደድለታል።

ማስረጃው!

የአሏህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ማለታቸው ነው፦

" በለሊቱ መጨረሻ አልቆምም ብሎ የፈራ ሰው በለሊቱ መጀመሪያ ዊትር ያድርግ በለሊቱ መጨረሻ እቆማለሁ ብሎ ያለሰው በለሊቱ መጨረሻ ይቁም የለሊቱ መጨረሻ ሰላት የሚጣዱበት ነው በላጭም ነው))📚 ሙስሊም 755

❺ ትንሹ የዊትር ቁጥር ስንት ረከአ ነው

➠ አነስተኛው ዊትር አንድ ረከአ ነው

ማስረጃውም

የአሏህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ማለታቸው ነው፦

((ዊትር አንድ ረከአ ነው ከለሊቱ መጨረሻ))📚ሙስሊም 752

➠ በመሆኑም አንድ ሰው ሁለት ሁለት ረከአ እያደረገ የለይል ሰላትን የፈለገውን ያክል ከሰገደ በሗላ በመጨረሻ አንድ ረከአ ዊትር ይሰግዳል።

➠ ወይም ደግሞ ሌላ ምንም የለሊት ሰላት ሳይሰግድ አንድ ረከአ ዊትር ብቻ ቢሰግድም ይችላል።

❻ ሌሎች የዊትር አሰጋገዶች አሉ ?

አዎ እነሱም ፦

➀ ሶስት ረከአ ዊትር መስገድ ይችላል

➠ ሶስት ረከአ ሲሰግድ ሁለት አይነት አሰጋገዶች አሉ

አንደኛው: ሶስቱንም ረከአ አከታትሎ በመሀል ተሸሁድ(አተህያቱ) ሳይቀመጥ በመጨረሻ ላይ ብቻ አንድ ተሸሁድ ቀርቶ ያሰላምታል።

ሁለተኛው: ሁለት ረከአ ሰግዶ ያሰላምትና እንደገና አንድ ረከአ ሰግዶ ያሰላምታል።

➠ ሶስት ረከአ ሲሰግድ ከፍቲሀ በሗላ በመጀመሪያው ረከአ (( ሰቢህ ኢስመረቢከ)) የሚለውን ሱራ በሁለተኛው ደግሞ ((ቁልያ አዩሀል ካፊሩን)) በሶስተኛው ረከአ ደግሞ ((ቁልሁወላሁ አሀድን)) ቢቀራ ይወደድለታል።

➁ አምስት ረከአ ዊትር መስገድ ይችላል

➠ ተሸሁድ ሚቀመጠው በመጨረሻ ላይ አንዴ ብቻ ነው መሀል ላይ ምንም ተሸሁድ አይቀመጥም።

➂ ሰባት ረከአ ዊትር መስገድ ይችላል

➠ በዚህም ግዜ ተሸሁድ ሚቀመጠው በመጨረሻ ላይ አንዴ ብቻ ነው መሀል ላይ ምንም ተሸሁድ አይቀመጥም።

➃ ዘጠኝ ረከአ ዊትር መስገድም ይችላል

➠ በስምንተኛው ረከአ ላይ ተሸሁድ ይቀራና ይነሳል ከዛህም በዘጠነኛው ረከአ ተሸሁድ ብሎ በዛው ያሰላምታል።ሁለት ተሸሁድ ይቀራል ማለት ነው።

➠ በነዚህ ሁሉ የዊትር አሰጋገዶች ላይ ሀዲስ ስለመጣ አንድ ሰው የቀለለውን መርጦ መተግበር ይችላል።

➠ አንዱን አንድ ቀን ሌላውን ደግሞ ሌላቀን ቢጠቀም ይበልጥ ይወደድለታል።

❼ ቁኑት

➠ ቁኑት የሚባለው ዊትር ሰላት ላይ በመጨረሻው ረከአ ከሩኩእ ከተነሳን በሗላ ሱጁድ ሳኖርድ በፊት የሚደረግ ዱአ ነው።

➠ ዊትር ላይ ቁኑት የተወደደ ተግባር ነው ነገር ግን ግዴታ አደለም።

➠ አንዳንዴ እያለው አንዳንዴ ቢተወውም ችግር የለውም ዘወትር ቢለውም ችግር የለውም።

_____________________

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

"ዓቂቃ"

አቂቃ ማለት አዲስ ለተወለደ ህፃን ልጅ የሚታረድ መስዋእት

የሚደረግ እርድ ነው። የተወደደ እና የተፀና የተከበደ ነቢያዊ ፈለግ

እርድ ነው።

“ዐቂቃ ማረድ በጣም የጠበቀ እና የተወደደ ሱና (ሱና ሙአከዳ)

ነው።

ምክንያቱም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል

"ማንኛውም ልጅ በ7ኛው ቀን በሚታረድለት ዐቂቃ የተያዘ ነው ።

ይህም ማለት ዐቂቃ የሚታረድለት ሕፃን ለወላጆቹ በቂያማ ቀን

ሸፈዐ ይሆናል ።ስሙ የሚወጣለትም ራሱንም (ፀጉሩን)

የሚላጨው በዛን ዕለት ነው።" ሲሉ መናገራቸውን ነው

(አቡዳውድ እና ነሳኢ) ዘግበውታል።

የዐቂቃ ዓላማው (የተደነገገበት) ምክንያት ለአላህ ሱብሃነሁ

ወተዓላ ምስጋና ለማድረስ ነው። ይህም አንድ ሰው ልጅ

ስለተወለደለት በመደሰት በ 7ኛው ቀን ደስታውን ለመግለፅ እና

ይህንንም ደስታውን ሰዎች እንዲያውቁት ለማድረግ እና

የተወለደውም ልጅ የማን እንደሆነ ለማሣወቅ ነውና አላህ ደግሞ

ልጁን እንደሚጠብቀው፣ሷሊህ ልጅ እንዲሆንለት ምክንያትም

እንዲሆነው የሚደረግ አርዶ ሰውን የማብላት ስርኣት # አቂቃ

ይባላል።

በአብዛኞቹ ሙስሊም ምሁራን እንዳሉት ዐቂቃ መደረግ ያለበት

ትልቅ ሱና (ሱና ሙአከዳ) ነው። እንደ አንዳንድ ምሁራን ደግሞ

ዐቂቃ ማድረግ ዋጅብ (ግዴታ) ነው የሚሉ ዑለማዎችም አሉ።

በላጩና የተመረጠው የዐቂቃ ማውጫ ጊዜም ልጅ በተወለደ

በሰባተኛው (7ኛው) ቀን ነው የሚሆነው።

☞ ወላጆች (እናትና አባት) አሊያም አያቶች ማለትም የወላጅ

አባት እና እናት ለልጃቸው አሊያም ለልጅ ልጃቸው ዐቂቃ

ማውጣት አለባቸው፣ይችላሉም።

የተወለደው ልጅ ወንድ ከሆነ ሁለት በግ(ፍየል) ሴት ከሆነች

ደግሞ 1 በግ(ፍየል) ሊታረድ ይወደዳል ።

ምክንያቱም ነብዩ ሙሐመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የአሊይ(ረዐ)

ልጅ ሐሰን በተወለደበት ጊዜ ሁለት በግ አርደዋል ።

(ቲርሚዚ ዘግበውታል)

እንዲሁም ስሙን ደህና ኢስላማዊ ስም በመምረጥ ሊጠራው

ይገባል።

ለምሳሌ ወንድ ከሆነ አብዱረህማን, አብዱላህ፣ሙሀመድ ወዘተ

....... ሴት ከሆነችም ደግሞ አሲያ፣ መሪየም፣ ኸዲጃ፣ ፈጢማ

ወዘተ......ብሎ ስም ቢያወጣላቸው ይወደዳል።

ሰባተኛው ቀን ያልታረደ እንደሆነ በ14ኛው ቀን ሊታረድ ይችላል

ያም ካልሆነ በ 21ኛው ቀን ቢያወጣ ችግር የለውም ይላሉ

ኡለማዎች፣

በአጠቃላይ አንድ ልጅ እስኪጎረምስ ድረስ አቂቃ ማውጣት

ይችላል የሚሉ ኡለማዎችም አሉ፣ እናም ቀኑ አልፎዋል ብለን

ይህን የጠበቀና የተወደደ የረሱል(ሰአወ) ሱና ከመተግበር

አንዘናጋ።

ምን አልባት ህፃኑ ሰባት ቀን ሳይሞላው የሞተ እንደሆነ ዐቂቃ

ማረዱ አስፈላጊ አይሆንም ብለዋል ኡለማዎች።

አንድ ሰው በህፃንነቱ ወላጆቹ አቂቃ ካላወጡለትና ትልቅ ሰው

ከሆነ በሁዋላ ና አቅሙ ካለው ጓደኞቹን ሰብስቦ አላማውን

ነግሯቸው(ዐቂቃ እንደሆነ ነግሯቸው) አቂቃ ማውጣት ይችላል

ብለዋል።( ኢብን ባዝ ረሂመሁላህ)

ስለዚህ እድሜያችን የፈለገ ያህል ቢሆንም አቂቃን ነይተን

ማውጣት እንችላለንና አንዘናጋ

የታረደው እንሠሣ ሥጋው በዒድ አል-አድሃ በዓል እንደሚደረገው

ሁሉ ሦስት ቦታ መከፈል አለበት። አንድ ሦስተኛው- ለድሃ፣ አንድ

ሦስተኛው- ለጓደኞች እና አንድ ሦስተኛው ደግሞ ለቤተሰብ

ይሠጣል።

አንድ ሰው የታረደውን ሥጋ ሁሉንም ለድሆችና ችግረኛ ሰዎች

መስጠት ይችላል።

ልጆች የአላህ ስጦታ ናቸው። እናም ይህን ታላቅ ፀጋ የሠጠንን

አላህን ማመስገን ይኖርብናል። ልጆችንም ገና ከህፃንነታቸው

ጀምሮ ልንንከባከባቸውና በኢስላማዊ አስተዳደግ እና ትምህርት

ያድጉ ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ልናደርግላቸው ይገባል።

አላህ (ሱወ) ሷሊህ ልጆችን ይወፍቀን 🤲

#ሼር #share በማድረግ ለሌሎች ያሳውቁ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከቀሳም ሙጃሂዶች ቃል አቀባይ ከአቡዑበይዳ ለዐረብ መሪዎች የተላለፈ መልዕክት:-

  "የጋዛን ከበባና ፍልሚያ በስክሪን ላይ የምትመለከቱ የአረብ መሪዎች ሆይ! ሰራዊታችሁን ልካችሁ ለመስጂደል አቅሳ ክብር እንድትከላከሉ ጦራችሁን ሰብቃችሁ ስለ ወንድሞቻችሁ አፀፋዊ ምላሽ እንድትወስዱ አንጠይቃችሁም።

ሐቢቢ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሠለም) በመሰደባቸው እንድትቆጡ፣ ወደ ሰማይ ኢስራዕ ያደረጉበት ክቡር ስፍራ በደም ሲጨቀይና ሲረክስ ሰይፍ ይዛችሁ እንድትወጡ አንጠይቃችሁም። ይህንን ለኛ ተውት። ስለ መስጂደል አቅሳ ስለ ኢስላምና ስለሀገራችን ከወዳደቁ ነገሮች በእጃችን በሰራነው መሳርያ በአቅማችን ለመታገል እኛ ወስነን በመንገዱ ላይ ነን።

ነገር ግን ከፈንና ምግብ የጫኑ ተሽከርካሪዎችን ለወንድሞቻችሁ እንዴት መላክ አቃታችሁ?! ሰብአዊ እርዳታዎችን ወደ ኢስላማዊቷ ምድር ማጓጓዝ ከቶ እንዴት ተሳናችሁ?! ይህ ልንረዳው ብንሞክር ያቃተን ተፍሲር ብንፈልግለትም ያጣንለት ጉዳይ ሆኗል"

አቡ ኡበይዳ በእርግጥም እውነት ተናገረ። በጦርነት ወቅት የሴቶች ስራ ስንቅ ማቀበልና ቁስለኛ ማከም ነውና የአረብ መሪዎችን ውሃና መድኃኒት መጠየቁ ልክ ነበር።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group